Monday, 30 November 2015

በምህራብ ኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው



በምዕራብ ወለጋ በመንዲ እና ጉሊሶ “መንግሥት አድማ በታኞችንና የአግዓዚ ጦርን አሠማርቶ ብዙ ተማሪዎችንና የከተማዪቱን ነዋሪዎች በቁጥጥር ሼር አውሏል” ሲል አንድ ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀ ነዋሪ ከቪኦኤ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገልጿል።

“በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሰው ዞን ውስጥ ጉሊሶ በተባለ ከተማም እንዲሁ ዛሬው ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንደተሰባሰቡ ፖሊስ በአድማ በታኝ ጢስ ሠልፉን በትኗል” ስትል አንዲት ተማሪ ገልፃለች።

በጉሊሶ ወረዳ የሰላም እና መረጋጋት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍቅሩ ሙለታ “ተማሪዎቹ ሠላማዊ ሰልፍ የማካሄድ ፈቃድ ሳይሰጣቸው የወጡ በመሆኑ እንዲበተን አድርገናል” ብለዋል፡፡

በምሥራቅ ሸዋ ጊንጪ ከተማ ባለፈው ሣምንት የተካሄደውን የተማሪዎች ተቃውሞ ተከትሎ “ሰባ ሰዎች ታስረዋል፤ ብዙዎች ተደብድበዋል” ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎችና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ፀሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
“ጊንጪ ከተማ የሚገኘው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሬት ተቆርሶ ለግለሰብ ተሸጧል። የጊንጪ ከተማ ስታዲየም ላልታወቀ አካል ተሸጧል። የጪሊሞ ደንም እንዲሁ ለግለሰብ ተሸጦ የዛፍ ቆረጣ ተጀምሯል። ይህን ሁሉ እንቃወማለን” ብሏል አንድ የከተማው ነዋሪ።

ነዋሪው አክሎም “የመንግሥት አካላት ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ይልቅ ልጆቹን በዱላ ተቀብለዋቸዋል። ዕለቱ የገበያ ቀን ስለነበረ የከተማው ነዋሪ እና ገበያተኛም ተማሪዎች በአድማ በታኝ ፖሊስ ሲደበደቡ ሲያዩ በመቃወማቸው እነርሱም ተደብድበዋል። አድማ በታኞቹ ሁሉም ዱላ ይዘዋል። ዱላውንም ተጠቅመውበታል” ብለዋል፡፡ ተማሪዎቹ በወቅቱ በመንገድ ላይ ሲያልፍ የነበረው ሰላም ባስ ላይ ድንጋይ በመወርወራቸው ድብደባው ተባብሶ እንደነበርም ገልጸዋል።

ተቃውሞውን አስመልክቶ የተናገሩት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ “የተቃውሞው መንስዔ የመንግሥት አካላት የትምህርት ቤት መሬት ቦታ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው ሲሆን ለተማሪዎች በሃገሪቱ ሕግ መሠረት መልስ ከመስጠት ይልቅ የመንግሥት አካላት ተማሪዎችን በመደብደብና በማሰር ላይ ናቸው” ብለዋል። በነጆ ከተማ ብቻ የአሥራ አራት ቤተሰቦች ቤት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መፈተሹን ገልፀዋል።
“የሚደረጉት ነገሮች የሀገሪቱን ሕግ የሚሰብሩ ናቸው። ለምሳሌ ያህል ከምርጫ በፊት የታሰሩ ሦስት አባሎቻችንን በዱላ ደብድበዋል፤ መዝገቡ ደበላ እና መምህር ዘላለም ሚስማ ‘ምንም ጥፋት አልተገኘባቸውም’ ተብሎ ከአንድ ዓመት ከሦስት ወር በኋላ ተለቅቀዋል። ለዚህ የሚጠየቅ አካልም የለም” ብለዋል አቶ በቀለ ነጋ።

አቶ በቀለ እንደሚሉት በአምቦው ሠልፍ ላይ ተማሪዎች “የኦሮሞ መብት ይከበር፤ ማስተር ፕላኑን ጨምሮ የመሬት ዝርፊያ ይቁም” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። ሠልፉም በሰላም ተጠናቅቋል።
በመንዲ ከተማም እንዲሁ የተማሪዎች ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን እዚያም የገበያ ቀን ስለነበር ህዝቡም አብሮ ሲቃወም ውሏል ሲሉ አንድ የከተማዪቱ ነዋሪ ገልፀውልናል።

“ቡራዩ የኦሮሞ ነው፤ ሰበታ የኦሮሞ ነው፤ ገላን የኦሮሞ ነው” “ የሚሉ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን የቪኦኤው ነሞ ደንዲ ነዋሪዎቹን እያነጋገረ በነበረበት ወቅት ሲያነጋግር በነበረበት ወቅት ተኩስ ይሰማ ስለነበር ሁኔታውን ሲጠይቀው ነዋሪው “ተኩሱ እንደዝናብ እየወረደ ነው፤ የሚተኩሱት ግን ወደ ሰማይ ነው፤ ፈጥኖዎች ተማሪዎችና ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ እያደረሱ ነው፡፡ አቶ ሄኖክ ዳግም የተባለ ነጋዴ ቤቱ ፊት ለፊት እንደቆመ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበታል” ብሏል፡፡

በተለያዩ ከተሞች ተካሄዱ የተባሉትን የተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፎች አስመልክቶ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሺን የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰሎሞን ታደሰ በሀገሪቱ የተረጋጋ ሕይወትና ሰላም መኖሩን ገልፀው ማንም ‘አለ’ የሚለውን ችግር ከሚመለከተው አካል ጋር በውይይት መፍታት እንጂ ጥቂት ተማሪዎች በሚያነሱት ብጥብጥ የህዝቡን ሰላም ማደፍረስ የለበትም” ብለዋል።
ባለሥልጣኑ አቶ ሰሎሞን “ሰባ ሰዎች ታስረዋል የሚባለው ውሸት ነው። አሥራ አራት ተማሪዎች በኅብረተሰቡ ሰላም ላይ ችግር ሲያደርሱ ሕግ በሚፈቅደው መንገድ ቁጥጥር ሼር ውለዋል። ይህ ፍርድ ቤት የያዘው ጉዳይ ነው ። የተደበደበ ተማሪ የለም” ብለዋል።

“በመንዲ፣ ቂልጡ፣ ካራ፣ አምቦ፣ ነጆና ሌሎች ከተሞች ውስጥ ተቃውሞ ቀጥሏል፤ ድብደባም ይፈፀማል ይባላል፤ ሰዎች ሳነጋግር እኔው ራሴም ተኩስ ሰምቻለሁ” ብሎ ነሞ ላቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሰሎሞን መልስ ሲሰጡ “የደረሰን ሪፖርት የለም። ነገር ግን ችግር ካለ፣ በመንግሥት በኩል ስህተት ካለ በሰላማዊ መንገድ መጠየቅና መፍትኄ መፈለግ እንጂ ረብሻ መፍትኄ አይሆንም፤ በጀልዱ ማስተር ፕላኑን አስመልክቶ ተማሪዎች ጥያቄ አንስተዋል ከመንግሥት አካላት ጋር ውይይት ለማድረግ ተስማምተው ሠልፉ በሰላም ተጠናቅቋል፤ ማስተር ፕላኑን በደንብ ያለመረዳት ችግሮች ይታያሉ” ሲሉም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሺኑ የከምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ታደሰ አስረድተዋል።

Saturday, 28 November 2015

“ረሃቡና ኢህአዴጋዊ እውነታዎች!” (ኤርሚያስ ለገሰ)

ህወሃት መልሚ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ በተከሰተ ቁጥር የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ “የአየር ንብረት መዛባት” በሚል ውጫዊ ምክንያት ማላከኩ የተለመደ ሆኗል። ለአብነት ያህል የዛሬ ዘጠኝ አመት በኢትዮጵያ ረሃብ በተነሳ ወቅት “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” በሚል ረዕስ የውስጥ ድርጀት ሰነድ ተዘጋጅቶ ነበር ደራሲው ጓድ መለሾ ዜናዊ ነበሩ። በማስከተልም የፓርቲው ከፍተኛ ካድሬዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት ውይይት እንዲያደርጉበት ተደረገ። በዚህ ሰነድ ገፅ 6 ላይ የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ እንደሚከተለው ይገልጻል።

 Ermias Legesse of ESAT

“ረሃቡ ከምን እንደሚመነጭ በትክክል ማስቀመጥ መፍትሄውን ለማስቀመጥ ወሳኝ ነው። የረሃቡ ቀጥተኛ ምንጭ ከአየር ንብረት መዛባት ጋር ተያይዞ የተከሰተው ድርቅ ነው። የአየር ንብረቱ መዛባትና ድርቁ እኛ ያልፈጠርነው ልናስተካክለው የማንችለው ነባራዊ ሃቅ ነው። በዚህ ነባራዊ ሁኔታ ማዕቀፍ ድርቁን ተቋቁመን ረሃቡን ለማስወገድ ያስቀመጥነው ስትራቴጂ ተዓምር ሰሪነቱ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባር ተረጋግጧል። የረሃቡ ዋነና ምንጭም የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ ነባራዊ ሁኔታን መቋቋም ረሃብን ለማጥፋት የቀየስነው ስትራቴጂ በሚፈለገው ፍጥነት በሁሉም አካባቢዎችን ስላልተፈጸመ ነው” ይላል።

እስኪ ይታያችሁ! ከዛሬ ዘጠኝ አመት በፊት (በ 1999 ዓም) የድርቁ መንስዔ የአየር ንብረት መዛባት እንደሆነ ተነገረን። ከዚያ በፊትም ምንጩ ተመሳሳይ ነበር። አሁንማ ልማድ ሆኖብን በኢትዮጵያ ምድር በየሁለት አመቱ ረሃብ የሚከሰት ሲሆን ምንጩ የአየር ንብረት ለውጥ ሆኗል። በነገራችን ላይ በሃገራችን ላይ በተጠቀሰው አመት ድርቁ ወደረሃብ በመቀየሩ ምክንያት በርካታ ህጻናት እና እናቶች ሞተዋል። በአራቱም ማዕዘናት ዜጎች ቀዬአቸውን ለቀው ተሰደዋል። የተፈጠረው አስደንጋጭ ሁኔታ ከህሊና የሚጠፋ አልነበረም።

በዛን ወቅት “በምጥቁ መሪ!” አብዮታዊ አመራር ሰጪነት የተሰራው ወንጀል ዘመን ተሻጋሪና ነገ ከነገ ወዲያ ተጠያቂነትን የሚያመጣ ነው።

እንዲህ ነበር የሆነው፥
በኢትዮጵያ አዲስ ሚሊኒየም ዋዜማ የተከሰተው ድርቅ ወደረሃብ መሸገገሩን የሚያሳይ ረፖርቶች ከመላው ሃገሪቱ መሰማት ጀመሩ። የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ ማሽን ከዛ አመት በፊት በነበሩት አራት አመታት ኢኮኖሚያችን በሁለት አህዝ አድጓል፥ ሚሊየነር አርሶ አደሮች መፍጠር ችለናል በሚል ቅኝት የሚመራ ስለነበረ ይህን መርዶ ለመቀበል አስቸጋሪ ሆነ። ረሃብን አስወግደናል ብለን ባወጅን ማግስት በረሃብ ተጠቅተን መገኘት በእርግጥም አሳፋሪ ነበር። የአመራርና የማስፈፀም አቅማችን፣ ምርጥ ልምዶች የማስፋት ስትራቴጂያችን ለአለም ተምሳሌት ሆኗል ባልን ጥቂት ቀናት ህዝቡ ረሃቡን መቋቋም አቅቶት እየተሰደደ መሆኑ መመልከት ፕሮፓጋንዳችን “ቢወቅጡት እምቦጭ” እንደሆነ የሚያመላክት ሆነ።

እንደ ተፈራው በዕልፍ አመቱ ዋዜማ የሰው ህይወት በየቦታው መውደቅ ጀመረ፥ ረሃቡን መቋቋም የማንችልበት ሁኔታ ግልፅ ሆኖ ወጣ። የመጀመሪያ ሰሞን እውነታውን አውገርግሮ ከማቅረብ ይልቅ ትክክለኛው መረጃ ተሰብስቦ ወደኢህእዴግ ቢሮ እንዲመጣ ልዩ ውሳኔ ተላለፈ። ለማመን በሚቸግር ሁኔታ የረሃቡ ዋነኛ ሰለባ ከሆኑት አካባቢዎች የሚመጣው መረጃ እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ሆነ። ከሶማሊያ ጫፍ እስከ አብርሃ አጽብሃ የሚባል የትግራይ ቀበሌ ድረስ ህዝቡ የሚላስ የሚቀመስ ማጣቱ ታወቀ። የከፋ ረሃብ ያጋጠማቸው አካባቢዎች ልጆቻቸውን እየቀበሩ ቀዬአቸውን እየለቀቁ መሰደድ መጀመራቸው እሙን ሆነ።

በሚሊኒየሙ ዋዜማ የችጋሩ ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት አካባቢዎች የመጀመሪያው የሱማሌ ክልል ነበር። የሱማሌ ክልል ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ለስርዓቱ ተገዢ እንዳልሆነ በገሃድ የሚታወቅ እውነታ ነው። በዛ ላይ አካባቢው በጦርነት የሚታመስ መሆኑ የረሃብ አደጋው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አደረገው። በወቅቱ የተፈጠረው ረሃብ በ10ሺዎች የሚጠጉ የቀንድ እና የጋማ ከብቶች መሞታቸው ታወቀ። ከ80 -100 የሚሆኑ ህጻናት በረሃቡ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ የሚያሳይ መረጃ የስም ዝርዝር ረፖርት ቀረበ።

ይህንን የሱማሊያ የረሃብ ሁኔታ የተቀበለው ጓድ በረከት ከ “ባለራዕዩ መሪ!” ጋር በመነጋገር አንድ ጠንካራ ትዕዛዝ ሰጠ። ጥብቁ ትዕዛዝ “ማንኛውም የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ጋዜጠኛ፣ በመንግስት ክትትል የማይደረግበት በጎ አድርጎት ድርጀት (NGO) ወደሶማሊያ ዝር እንዳይል!” የሚል ነበር። እነሆ ላለፉት 10 አመታት የትኛውም የነጻ ፕሬስ ሆነ የውጭ ጋዜጠኛ ወደሶማሊያ ክልል ልሂድ ብሎ ጥያቄ ቢያቀርብ ኣይፈቀድለትም። ከጓድ በረከት ጋር የቅርብ ወዳጅነት የመሰረቱትም ቢሆን ፍቃድ አያገኙም። የተለያዩ ምክንያቶች እየተሰጣቸው ጥያቄዎች እንዲጥሉ ይደረጋል። በዚህ ምክንያት በሱማሊያ በረሃቡ የሞቱት ህጻናት ከሪፖርቱ ውጪ እንዲሆኑ ተደረገ። እስከ 100 የሚደርሱት ህውየታቸው ያለፉት ህጻናት ማህደር በኢህአዴግ ቢሮ ተቆለፈበት።

በሚሊኒየሙ ዋዜማ ሌላኛው የረሃቡ ተጠቂ አካባቢ ደቡብ ኢትዮጵያ ነበር። ረሃብ ታሪክ ተደርጎበታል የተባለው የደቡብ ኢትዮጵያ በሚሊዮኖች እየረገፉ መሆኑን አስቀድመው መረጃ የመጡት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የውጭ ጋዜጠኞች በመሆናቸው መደበቅ የሚቻል አልነበረም። ከዚህም በተጨማሪ የውጭ ጋዜጠኞች የተፈናቀሉ እና የሞቱ ሰዎች የሚያሳዩት ዘገባዎችን ለዓለም ህዝብ በማስተላለፋቸው ምክንያት መነጋገሪያነቱ ከጫፍ ጫፍ ናኘ። በመሆኑም ነባራዊ ሁኔታውን እንደቅቡል መውሰድ፣ ግን ደግሞ እውነታውን አውረግርጎ ማቅረብ የአቶ መለሾ መልሚ የመንግስት የፕሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ሆኖ እንዲቀረፅ ተደረገ።

በዚህም ምክንያት የተራበው ህዝብ ከ 14 ሚሊዮን በላይ ቢሆንም ጓድ! መለሾ ባዘጋጀው “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” የውስጠ-ድርጅት ሰነድ ጨምሮ የመንግስት ሚዲያ ተቋማት 6.4 ሚሊዮን ብቻ ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸው አሳወቁ። በሱማሊያ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ከ500 ያላነሱ ህጻናት በረሃብ ቢሞቱም የፕሮፓጋንዳ ማሽን ከ30 እንደማይበልጡ ይፋ አደረገ። ይህንን አውነታ በማስረጃ ለማስደገፍ ያህል “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” በሚለው የፓርቲ ሰነድ ከገፅ 7-8 የሚከተለውን ይላል፥

“በአንዳንድ የደቡብ አካባቢዎች አደጋውን በወቅቱ ካለማየት ጋር ተያይዞ ባለፈው አመት 26 ያህል ህጻናት ለሞት የተዳረጉበት ሁኔታ ተከስቷል። ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ በረሃብ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች የሉም። አልፎ አልፎ በአፈጻጸም ጉድለት ምክንያት እንደተጠቀሰው የሟች ዜጎች ቢኖሩም በአጠቃላይ በመቶ ሺዎች ቀርቶ በመቶዎች የማይሞቱበት ተፈጥሯል። በተወሰኑ አካባቢዎች የሚታየው የአፈጻጸም ጉድለት ካስተካከልን ምንም ዜጋ የማይሞትበት ሁኔታ መፍጠር እንደምንችልም ጥርጥር የለውም” ይላል።

እንዲህ እውነቱ ተቀናንሶ እና በብዕር ቆንጨራ ተከታትፎ ቢቀርብም በአደባባይ ያለው ሚስጥር ሃቁን መሸፋፈን አልቻለም። ዛሬም ዜጎች በረሃብ ሰቆቃ ውስጥ እየኖሩ ነው። ህይወታቸው እየተቀጠፈ እየተመለከትን “የምጥቁ መሪ!” ተከታዮች ረሃብ የለም ይሉናል። ችግር የተከሰተው “ምናምንቴ” የሚል ስያሜ በተሰጠው አየር መዛባት ምክንያት ድርቅ ስለተከሰተ እንደሆነ ይሰብኩናል። ፍቱን መድሃኒቱም በተግባር የተረጋገጠው “ኪራይ የሚሰበስበው” ስትራቴጂያቸው እንደሆነ ይነግሩናል። ርግጥ ሃቁን በትክክል ቢያስቀምጡ ከትናንትናው ምላሳቸው ጋር ስለሚጣሉ አጣሞ ማቅረብ ግዴታቸው ይሆናል። ምንም እንኳን ያሳምንልናል ብለው የሚያቀርቡት መከራከሪያ ከተጨባጭ ሃቁና መሬት ላይ ካላው እውነታ የትየለሌ በመሆኑ በህዝቡ ትዝብት ላይ ቢወድቁም!….
እዚህ ላይ ማንም አእምሮ ያለውና የአለምን ፖለቲካል ኢኮኖሚ የሚከታተል ሰው የአየር መዛባት፣ የዝናብ እጥረት አልተከሰተም አይልም። ከአገዛዙ ከበለጠ የድርቅ ባህሪያና ትርጉም መረዳት የሚያቅተውም አይደለም። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የምግብ ምርት ወይም የውሃ አቅርቦት በመቀነሱ ከፍተኛ ጫና የሚያስከትሉ የእርጥበት እጥረት መከሰቱን የሚክድ የለም። የድርቅ መነሻ ምክንያቱ ከመደበኛ እና ከሚጠበቀው በታች በአየር ጠባይ መለያየት የተነሳ የዝናብ እጥረት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። በአለም አቀፍ ደረጃም በአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት በተለያዩ ዘመናት ሃገሮች በድርቅ ሲጠቁ ተመልክተናል።

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ባለፈው ክረምት ጓድ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከውጭ የመጡ የሃገሬ ሰዎች በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስቦ ያሰማው “ኢህአዴጋዊ አውነታ” የኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በተለይ በካሊፎርኒያ የአሜሪካ ዜጋ በድርቅ እየተሰቃየ መሆኑ አስረግጦ ሲናገር የተሰማው ጭብጨባ እስከዛሬም ጆሮዬን ይሰቀጥጠናል። የሆነው ሆኖ “ካሊፎርኒያ በድርቅ ተሰቃየች” የሚለው አባባል የትኛውን ግብ ለማሳካት በጭብጨባ እንደታጀበ የሚያውቁት አጨብጫቢዎች ብቻ ቢሆንም የገባንበትን የሰብዕና መላሸቅ አጉልቶ የሚያሳይ ነበር። የአውስትራሊያ አሊያም የካሊፎርኒያ ህዝብ በድርቅ ቢጠቃ ደስ ይለናል ማለት ነው?
የአገጣሚ ነገር ሆኖ የዛሬ ሳምንት እኔና ተወልደ በየነ (ተቦርነ) ለኢሳት የገቢ ማስገኛ ዝግጅት የካሊፎርኒያ እምብርት ወደሆነችው ሎስ አንጀለስ (LA) (ተቦርነ “ላይ አርማጭሆ” ይላታል) ሄደን ነበር። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኮሚቴ የእንኳን ደህና መጣችሁ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ “እንኳን በድርቅ ምክንያት እየተሰቃየች ያለችውን ካሊፎርኒያ በሰላም መጣችሁ!” በሚል ነበር የጀመሩት።

ይህንን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በአርምሞ ሲያዳምጡ የነበሩት ተሰብሳቢዎች በጭበ አስከትሎም የማያባራ ሳቅ አጀቡት። መቼስ! ተንኮል ካልሆነ በስተቀር ጭብጨባና ሳቅ ምን አመጣው? እንኳንም ጓድ! ሃይለማርያም በስብሰባው አልኖረ! እንኳንም በሚሊኒየም አዳራሽ የተገኙ የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች አልሆኑ።

እናማ የስብሰባው አዘጋጆች ፕሮግራም ከተጠናቀቀ በኋላ በያዙልን ዕለታዊ መርሃግብር መሰረት ካሊፎርኒያን ያስጎበኙ ነበር። የድሮ ካድሬ ነገር ሆኖብኝ የምንሄድበት መኪና በቆመ ቁጥር ነጩን፣ ጥቁሩን፣ ስፓኒሹን፣ አፍሪካዊውን ካሊፎርኒያ “ ድርቁ እንዴት ነው? ምን ጉዳት አስከተለ?” የሚል ጥያቄ አነሳ ነበር። ያለማጋነን ጥያቄ ከመለሱልኝ ሰዎች ውስጥ ዘጠና በመቶው ድርቅ መኖሩን አያውቁም። የተቀሩት ውሃ ለመቆጠብ የሻወር ቤታቸውን የውሃ ወንፊት እንዳጠበቡ ነግረውናል። ከፊሎቹ ለውሃ ቁጠባ ሲባል መኪናቸውን በሁለት ሳምንት አንዴ እያጠቡ መሆኑን እያዘኑ አጫውተውናል። ሃዘናቸውንም ተጋርተነዋል። የሻወር ቤት ወንፊት ከማጥበብ፣ መኪናን በሳምንት ሁለት ጊዜ ከማጠብ በላይ ምን ስቃይ አለ? አትክልትን ከሳምንት አምስት ቀን ሁለት ቀን ውሃ እንዲጠጡ ከማድረግ በላይ ምን የሚያበሳጭ ነገር አለ?

የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በግዛቱ የመንግስት ተቋም ውስጥ የሚሰራ ሙያተኛ ከአስጎብኚዎች አንዱ ነበር። ግለሰቡ ካሊፎርኒያ ያጋጠማት ችግር ጓድ ሃይለማሪያም ከጠቀሱት በተቃራኒ፣ ከልክ በላይ መብላት የሚመጣ ውፍረት (Obesity) መሆኑን ነገረን። ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ እንዲሉ ወዳጃችን የካሊፎርኒያ ችግር ከመጠን በላይ ምግብ በመብላት እና የአካል እንቅስቃሴ ባለማድረግ የሚመጣ የሰውነት ውፍረት እንደሆነ አጫወተን። በመፍትሄ ደረጃም በግዛቱ በሚገኙ ት/ቤቶች “Child obesity school program” ቀርጸው ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ነገረን። በየመቶ ሜትሩ የምናያቸው የተዘረጠጡ ህጻናት ለፕሮግራሙ ተገቢነት የሚያረጋግጡ ነበር። እርግጥም ካሊፎርኒያን ጨምሮ በመላው አሜሪካ ጭንቀትና ስቃዩ የዜጎች የስብ ክምችት መሆኑን ለማወቅ ብዙ መልፋት አይጠበቅም። ለጥቂት ደቂቃዎች ወደኢንተርኔት ጎራ ያለ ሰው ከአሜሪካ አጠቃላይ ህዝብ 78 ሚሊዮኑ (ከዚሁም 12 ሚሊዮን ህጻናት) በውፍረት ግዝፈት መጠቃቱን ይመለከታል። ዘለግ አድርጎ ለተመለከተ ደግሞ የሰውነት ግዝፈት መጠን (obesity rate) በውፍረት በሽታ የግዛቶቹ ተደርድሮ ያያል። ለምሳሌ ካሊፎርኒያ 24.1%፣ ሚሲሲፒ 35%፣ ቨርጂኒያ 35.1% ወዘተ እያለ ይቀጥላል።

እነዚህን የመሳሰሉ ሀገሮች በአየር መዛባት ምክንያት ድርቅ ሲከሰትባቸው ትክክለኛ ፖሊሲ በመቅረፅ ዜጎቻቸውን ታድገዋል። የረጅም እና የአጭር ጊዜ ስትራቴጂካል እቅዶችን ከማውጣት ባሻገር ተስማሚ ቴክኖሎጂ በመምረጥ፣ የውሃ እና አፈር አጠባበቅ ተግባርን በማሻሻል፣ የግብርና ምርት ውጤቶችን ወደውጭ እንዳይወጡ በማገድ፣ የገጠር እና የከተማው ልማት በማቀናጀት… ወዘተ ዘላቂ መፍትሄ አስቀምጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሰፋፊ ዘመናዊ እርሻዎች በማስፋፋት፣ የግብርና ምርታቸውን በከፍተኛ እጥፍ በማሳደግና፣ የህዝቡን የመግዛት አቃም በማጎልበት በድርቅ ምክንያት የሚከሰተውን አደጋ ከቁጥጥራቸው ውጪ እንዳይሆን አድርገዋል። ድርቅ ተፈጥሯዊ ነውና በማንኛውም ሰዓት ይመጣል፥ ግን ደግሞ እዚህ ግባ የማይባል ጉዳት አያደርስም። በፖለቲካው መስክም ቢሆን የገነቡት ዲሞክራሲያው ስርዓት ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገት የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል። ያለነጻነት ሁሉን አቀፍ ልማት ማምጣት እንደማይቻል ተገንዝበው ለዜጎቻቸው ነጻነት አጎናጽፈዋል።

እንግዲህ በአለም ያለው እውነታ ይህ ነው። ይሁን እንጂ፣ “ የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ ገዢዎቻችን በስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ በየሁለት አመቱ የሚከሰተውን ከድርቅ የተሻገረ ረሃብ በአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት እንደሆነ ሊያስረዱን ይሞክራሉ። አገዛዙ ስልጣን በያዘ ሁለት አመታት ጀምሮ መጀመሪያ 6 ሚሊዮን፣ ቀጥሎ 10 ሚሊዮን፣ በማስከተል 14 ሚሊዮን ህዝብ በረሃብ ተጋልጦ ነበር። አሁን ደግሞ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ የረሃብ አደጋ አንዣቦበታል። እነዚህ ጥሬ ሃቆች የሚካዱ አይደሉም።

በኢትዮጵያ ቀይ፣ ጥቁር፣ መረሏ አፈር ላይ የተነጠፉ እውነታዎች ናቸው። ዛሬም አገዛዙ በሚከተለው ፖሊሲ ምክንያት ራሳችንን መመገብ አቅቶን አቅማዳችንን ለመጽዋት ክፍት አድርገናል። አገዛዙ ዲሞክራሲያዊ፣ ሰብዓዊና ሌሎች የህዝብ መብቶችን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን እስካልቀየረ አሊያም ስርዓቱ እስካልተቀየረ ድረስ የወደፊት እድላችን የከፋ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሆኗል። የፊተኛው መፍትሄ ኣያለፈበት ይመስላል። የስርዓት ለውጥ የሚለው ደግሞ ይበልጥ ተቀባይነት ማግኘቱ የሚታይበት ሁኔታ ፈጥሯል። ፍጥነቱ በደረሰው መከራ እና አበሳ፣ በደረብን ቁጭት ልክ ባይሆንም። ዞሮ ዞሮ ሃገራችን የገባችበትን የረሃብ አዙሪት ትግሉን ከሚያዘውሩት ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ መሆኑ አልቀረም!

የሕወሓት አስተዳደር አዲስ አበባን “እናሰፋለን” በሚል ሰበብ የሚሰራው ሸፍጥ ተጋለጠ (ምስጢራዊውን ደብዳቤው ይዘናል)

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ሕዝቡ ሕወሓት የሚመራው መንግስት ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም አደባባይ በመውጣቱ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት እና ለበርካቶች መቁሰል ምክንያት እንደነበር ይታወሳል:: እነዚህ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ የሃገራችን ፍሬዎች ምክንያታቸው በአዲስ አበባን የማስፋፋት ምክንያት ምስኪን ገበሬዎችን በማፈናቀል መሬታቸውን ለባለሃብቶች ለመሸጥ ነው የሚል ነው:: ሕወሓት የሚመራው መንግስት “በልማት” ስም የተለያዩ የሃገራችንን መሬቶች ገበሬዎቹን በማሰናበት ለውጭ ባለሃብቶች በመሸጥ ይታወቃልና ወትሮም እነዚሁ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ሕዝቦች አደባባይ ወጥተው ይህን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ገበሬዎችን ያፈናቅላል ያሉትን አዲሱን ማስተር ፕላን ቢቃወሙ አይገርምም::

ዛሬ የተለቀቀው ምስጢራዊ ደብዳቤ በአዲስ አበባን የማስፋፋት ስም በሕወሓት መንግስት የሚደረገውን ጥልቅ ሴል ያጋለጠ ነው:: ምስጢራዊው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ‘ሆዜ ሂማንተሪያን ፋውንዴሽን” የተሰኘ ድርጅት የመለስ ዜናዊን መንደር በሰበታ አዋስ ወረዳ ያቀረበውን ጥያቄ ወረዳው መቀበሉን ያረጋገጠበት ነው:: ደብዳቤው እንደሚለው ለመለሾ ዜናዊ መንደር ግንባታ ለሆዜ ፋውንዴሽን አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሄክታር ወረዳው እንዲያዘጋጅ መጠየቁን እና ይህንንም ማዘጋጀቱን ነው::

እንግዲህ አዲስ አበባን እናስፋፋለን የሚሉት ምስኪን ገበሬዎቹን አፈናቅሎ ምን ለመፍጠር እንደሆነ ከዚህ በታች ከቀረበው ደብዳቤ ይረዱና አስተያይትዎን ያስቀምጡ::

Tuesday, 24 November 2015

“በአዛዙ የአፈና መዋቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነትና የእኩልነት ትግል አይቀለበስም” – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱና በሌሎች ልሹ ባወጣቸው ህጎች በርካታ መብቶችን ለይስሙላ ቢደነግግብ ቅሉ፤ በተግባር ግን እነዚህን መብቶች ሆነ ብሎ ባደራጀው የአፈና መዋቅሩ እየደፈቃቸው ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን አገዛዙ የመደራጀት መብትን በወረቀት ቢያሰፍርም ‹‹áŠĽáŒáˆ­ እስኪያወጡ እንጠብቃለን፤ እግር ሲያወጡ ግን እንቆርጣለን›› በሚል መርህ ፓርቲዎችን በዚሁ የአፈና መዋቅሩ በገሃድ እያፈረሰ ቀጥሏል፡፡ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ፈቅጃለሁ ቢልም ጋዜጠኞችን በማሰር፣ በማሳደድና ሚዲያዎችን በመዝጋት አማራጭ ሀሳብ እንዳይራመድ አድርጓል፡፡ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ወረቀት ላይ ቢደነግግም በአስተዳደራዊ መዋቅሩ መሰረት ክርችም አድርጎ ዘግቶታል፡፡ የዜጎችን የመዘዋወር መብት ቢደነግግም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፓስፖርት በመንጠቅ ጉዟቸውን በማተጓጎል ላይ ይገኛል፡፡ የመንግስት አሰራር ግልፅና ተጠያቂነት አለበት ተብሎ ተደንግጓል፤ ነገር ግን በየ መስርያ ቤቱ ያለ እጅ-መንሻ ዜጎች አገልግሎት ማግኘት አይቻልም፡፡ ይህ ሁሉ አፈና ሆነ ተብሎ ታስቦበት፣ የአገዛዙን ስልጣን ለማራዘም የሚደረግ መዋቅራዊ ጫና መሆኑን ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡

ዛሬ በሀገራችን ከፍተኛ ርሃብ፣ ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሾል አጥነት፤ ስደት እና ሌሎችም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶች በሰፊው ተንሰራፍተው ይገኛሉ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ወቅታዊ ጉዳዮች ከህዝብ ጋር ተወያይቶ አቋም ለመውሰድና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለመሰንዘር ህዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የእውቅና ደብዳቤ ለማስገባት በተደጋጋሚ ጥረት ያደረግን ቢሆንም የአፈና መዋቅሩ የእውቅና ደብዳቤውን መቀበል ባለ መፈለጉ ለ5 ጊዜ ተጉላልተን በ6ኛው በሪኮመንዴ(በፖስታ) ለመላክ ተገደናል፡፡

የእውቅና ደብዳቤው በሪኮመንዴ የደረሰው አስተዳደሩ ህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም ላይ ሆኖ ‹‹áˆ…á‹łáˆ­ 18/2008 ዓ.ም አልፏል›› በሚል ለተጨማሪ ጊዜ ደብዳቤውን ሳያስተናግድ ቀርቷል፡፡ ህዳር 18 ያላለፈ መሆኑን ካስረዳን በኋላ ለሶስት ቀናት በተደጋጋሚ ብንመላለስም ‹‹áŠ¨á‹°áˆ…ንነቾና ፖሊስ ጋር ካልተመካከርኩ እውቅና አልሰጥም›› ሲል እምቢታውን ገልጾአል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአባላትና ደጋፊዎቻችን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ልናደርገው የነበረው ውይይት ሊደናቀፍ ችሏል፡፡

ከዓለም የነጻነት የትግል ታሪክ እንደምንገነዘበው በአገዛዝ አፈና የተገታ የህዝብ ጥያቄ ኖሮ አያውቅም፡፡ አፈናው የነጻነትን ጊዜ ቢያዘገይ እንጅ ፈጽሞ ሊያስቀርም አይችልም፡፡ ስለሆነም ጭቆናው ወደ ነፃነት የሚያስኬደውን ጉዞ እልህ አስጨራሽ ከማድረግ በቀር ዘላቂነት ኖሯቸው የነጻነት ጥያቄውን ፈጽሞ ማዳፈን እንደማይችሉ አገዛዙ ሊረዳ ይገባል፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ለማይቀረው የነፃነት ትግል ቆርጦ እንዲነሳና ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ህዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ፖሊስ የቤተሰብ አባላትን እየጠረነፈ ነው

ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ ‹‹á‹¨á‰¤á‰°áˆ°á‰Ľ ተጠሪ ፎረም›› የሚሉ ቅፆችን በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን ለመጠርነፍ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቅፁ ላይ የቤተሰብ አባላት ‹‹á‰ áˆ˜áŠ–áˆŞá‹Ť ቤታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ያለ መግባባቶችን በራሳችን ለመፍታትና ብሎም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ሆነን በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የድርሻችን ለመወጣት›› በሚል ከቤተሰብ መካከል ለፖሊስ ተጠሪ እንዲወክሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ይህ የቤተሰቡ የፖሊስ ተወካይም ግቢው ውስጥ ተፈጠሩ የሚላቸውን ጉዳዮችና ሌሎችም መረጃዎች ለፖሊስ ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ጥርነፋው ከቤተሰብ ተነስቶ፣ ብሎክ፣ ቀጠና እና ወረዳ እያለ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Sunday, 22 November 2015

CPJ Awards Zone9 Bloggers of Ethiopia: International Press Freedom Award

Zone 9 Bloggers, Ethiopia

In April 2014, Ethiopian authorities arrested six bloggers affiliated with the Zone 9 collective. The bloggers–Abel Wabella, Atnaf Berhane, Mahlet Fantahun, Natnail Feleke, Zelalem Kibret, and Befekadu Hailu–were charged with terrorism.

The Zone 9 blogging collective was formed in May 2012 in response to the evisceration of the independent press and the narrowing of space for free expression. The name, “Zone 9,” is derived from the zones in Kality Prison, the main jail where Ethiopia’s political prisoners, including several journalists, are held. While Kality Prison is organized into eight different zones, the bloggers refer to the entire country as “Zone 9” because of Ethiopia’s lack of democratic freedoms, one of the bloggers told CPJ.

The collective is made up of nine bloggers–the six named above, and Soleyana S Gebremichael, Endalk Chala, and Jomanex Kasaye, all of whom are in exile. Soleyana has been charged in absentia.
In July 2015, weeks before U.S. President Barack Obama visited the country, Ethiopian authorities released Mahlet and Zelalem.

The Zone 9 bloggers were arrested along with three other journalists–editor Asmamaw Hailegeorgis and freelancers Tesfalem Waldyes and Edom Kassaye, who were later released. The initial charges against the group included working with international human rights organizations and taking part in email encryption and digital security training. The group was subsequently charged with terrorism.
Since 2009, when Ethiopia’s anti-terror law was implemented, the government has used the sweeping legislation to imprison more than a dozen critical journalists, according to CPJ research. In 2012, blogger Eskinder Nega was sentenced to 18 years in prison and Woubshet Taye to 14 years, both on terrorism charges. CPJ’s 2014 prison census found that Ethiopia was the fourth worst jailer of journalists in the world, with at least 17 journalists behind bars. Ethiopia also ranked fourth on CPJ’s 2015 list of the 10 Most Censored Countries.

With the motto “We Blog Because We Care,” the Zone 9 collective has voiced concerns over domestic issues, including political repression, corruption, and social injustice. The collective’s posts were frequently blocked inside Ethiopia, but gained a following with Ethiopians in the diaspora, according to local reports. Their posts on Facebook solicited some 12,000 responses a week, reaching 200,000 during a four-part “campaign” they ran on Facebook.

By awarding the Zone 9 bloggers with its International Press Freedom Award, CPJ recognizes the important role that bloggers play in environments where traditional media are weak or have been all but shuttered by financial hardship and direct or indirect state attacks.

Country facts:
  • Ethiopia released at least six journalists from prison in 2015, but is still holding around a dozen journalists in jail in relation to their work.
  • In May 2015, the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) won 100 percent of the vote.
  • In 2014, at least eight independent publications were shut down, according to CPJ research.
  • Between 2013 and 2014, in response to the continued government crackdown on the media, more than 40 journalists fled into exile from Ethiopia.
Source: CPJ

Saturday, 21 November 2015

የሀብታሙ አያሌው መልዕክት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት

በሞት ጥላ መካከል ብሄድ እንኳን ክፉን አልፈራም !!!

የልቤን ምጥ ልፃፈው ብዬ ደጋግሜ ብዕሬን ይዤ ወረቀቱ ላይ ብፅፍም እንደተራበው ወገኔ ሆድ ብዕሬ ባዶ ሆኖ ቀለም አልነጥበው አለ፡፡ በቅሊንጦ ማጎሪያ ቤት ሰማይ ሾር ነፍሴ ሀዘን አቆርዝዛ በማይገፉ ቀንና ሌሊቶች ውስጥ ባዘነች፡፡ ለወትሮው ወገኔ እንደከፋው ስሰማ እንደወፍ በርሬ ችግሩን ልጋራው ከመሃሉ እደርስ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የህዝቤ ስቃይ ወደ ሰማይ ጉኖ በጠኔ ሲንበረከክ እንደ ጅብራ ተገትረው በማያንቀሳቅሱኝ ወታደሮች ተከብቤ በጭንቀት እየባዘንኩ ከመጠውለግ በቀር አደርገው ነገር አጣሁ ፡፡ ወይ ሀገሬ!!! ወይ ወገኔ!!! ….. እመነኝ እንዳልኩህ አሁንም እመነኝ … አሁንም እመነኝ !!! እመነኝ ደርግ ወድቋል ኢህአዴግ ይወድቃል፡፡ ዛሬ በአሳሪዎቼ ጡጫ ተደቁሼ፤ ድምፄ በኢትዮዮጵያ ሰማይ ሾር ባይሰማም የታገልኩለት እውነት ወደ አደባባይ ወጥቶ ህዝቤ የነፃነት ሻማ እሚጎናፀፍበት ቀን እንደሚመጣ ግን ጥርጥር የለኝም፡፡ የልጄ ናፍቆት የሚስቴ ስቃይና እንግልት የእህቶቼ መባከን እና መሳቀቅ አቅሜን ሲፈታተኑት በማዕከላዊ የስቃይ ማማ ሾር ጉዳት ያተረፉት ሁለቱ ኩላሊቶቼ የቀን ከሌት ስቃዬን ሲያረዝሙት የነከስኩት ጥርሴ ጉልበቴ አበርትቶ የነፍሴን መዛል ብሸሽግም… ዛሬ ግን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖ የታገልኩለት ህዝብ በረሃብ ጠኔ እየተመታ በሞት ጥላ መንበርከኩን ስሰማ ነፍሴ በውስጤ አለቀች እናም የልቤን ሀዘን እፅፍ ዘንድ ሞከርኩ… ሞከርኩ ግን አቃተኝ…. ጃርት እንደ በላው ዱባ በየቦታው የተፈረካከሰው ፓለቲካችን ዛሬም እርስ በእርስ እየተሸነቋቆጠ ይቀጥላል ወይስ ወገኑን ለመታደግ እንኳ አንድ ይሆናል? ነፍሴ በየእለቱ የምትሟግተኝ ጥያቄ ነው ፡፡ ሳንተባበር ጉልበት አንድ ሳንሆን ኃይል ከወዴት እናገኝ ይሆን ? የአምባገነኖች ጡጫ እየደቆሰን ረሃብ በየዘመኑ የሚቆላንስ እስከመቼ ነው? በእውነቱ በሀሳብ ብዙ ባከንኩ አገኝለት ዘንድ ግን መልስ አጣሁ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር እና የኢትዮጵያ ህዝብ መልስ አጥተው አያውቁም እና ተስፋዬ ፈፅሞ አይመክንም፡፡ 

እናም ያገባናል ለሚሉ ሁሉ እላለሁ የኢትዮጵያ ገፅታ የሚገነባው በየሰርጡ በጠኔ የሚሞቱ የወገኖችን እሬሳ በመደበቅ እንዳልሆነ ካሳለፍናቸው ክፉ ጊዜያት ተምረን ባለን አቅም ተረባርበን ወገኖቻችንን ለመታደግ እንበርታ እላለሁ…!!! በአዲስ አበባ፤ በባህር ዳር፤በአርባ ምንጭ፤ በጎንደር፤ በደሴ፤ በአዳማ፤ በአዋሳ፤ በወላይታ ህዝብ በሚንቀለቀል የለውጥ ፍላጎት ድምፁን ባሰማባቸው ሰላማዊ ሰልፎች… ‹‹áŠ˘áˆ…አዴግ ከታሪክ ይማር፤›› ‹‹áŠ áˆá‰ŁáŒˆáŠáŠ–ች ባሉበት ሀገር የጀግና ሞቱ እስር ቤት ነው ፤›› ‹‹á‰łáŒ‹á‹­ ይታሰራል ትግሉ ይቀጥላል፤ ›› ‹‹ እጃችን ባዶ ነው እነዚህ አምባገነኖች ነገ አሸባሪ ይሉናል›› ፤ ‹‹áŠĽáˆ˜áŠáŠ ደርግ ይወድቃል ኢህአዴግም ይወድቃል›› ማለታችንን ….. በእርግጥም ልክ ነበርን፡፡ ዛሬ አሸባሪ ተብለን ከትግል አጋሮቼ ከዳንኤል ሺበሺ ፤አብርሃ ደስታ ፤ የሺዋስ አሰፋ ፤አንዷለም አራጌ፤ ተመስገን ደሳለኝ ፤እስክንድር ነጋ ፤ ወዘተ…. ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ጋር የነፃነት ቀንን እየናፈቅን በእስር ቤት አለን ፡፡ የፍርድ ቤት ድራማውም ተጠናክሮ ቀጥሏል ፍርድ ቤቶችን ከጀርባ ቆመው የሚዘውሩ በቀጭን ትዕዛዝ ማረሚያ ቤቶችን የሚያሽቆጠቁጡ፤ በፍትህ ስም የሚቀልዱ ፓርቲዬን ያፈረሱ፤ የህዝቤን ተስፋ ለማምከን ቀን ከሌት የሚደክሙ የካዛንቺሱ መንግስቶች እጃቸው የሚያጥርበትን ቀን አብዝተን እንናፍቃለን ፡፡ በእውነት እላለሁ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ክፉን አልፈራም !!!

Esat Stavanger's photo.

Friday, 20 November 2015

Ethiopia’s Zone9 bloggers say “We are still prisoners”


Evidently six members of the Zone9 & three journalists are released from prison after they spent 14 to 18 months in prison. The three journalists and the two bloggers were released as the charges were ‘withdrawn’ in July. While the other four bloggers were acquitted in October. And one member the blogging collective, Befeqadu, was released on bail and he is yet to defend himself later this year in December on charges related with inciting violence.

However, since we walked free from prison we often are running into difficulties that suggest that we are not completely free and we can also testify that our difficulties are not easing off yet. As a result have decided to issue a brief statement on our situation:

1. The three journalists and the two bloggers who were released in July are still under travel restrictions although they got their seized passports back. For instance, Zelalem Kibret was denied exit and he got his passport confiscated at Bole International on November 15, 2015. He was traveling from Addis Ababa to Strasbourg, France to attend an award ceremony of Reporters Without Borders as Zone9 Bloggers are the recipient of the 2015 Citizen Journalism Award. Due to this complications Zelalem’s chance to travel to New York to attend CPJ Press Freedom Award ceremony is seriously hampered. We do not know why this happened to Zelalem but we want to remind that article 32 of the Ethiopian Constitution protects Ethiopians’ freedom of movement both within Ethiopia as well as to travel abroad.

2. The three bloggers, Abel Wabela, Atnaf Birahane,and Natnael Felek who were acquitted at the beginning of October have not got their seized passports and electronic equipment back. Although they have requested to have their confiscated passports and properties back stating the prosecutor’s ‘appeal’ as a reason, the concerned government agency denied them to get their properties back. But the issue of appeal is still unresolved and four weeks after their release the bloggers are yet to learn their fate

3. Abel Wabela, Edom Kassaye ,Mahlet Fantahun and Zelalem Kibret were employees before their imprisonment. But so far their employers are not willing to rehire them or allow them back to their work. The time they spent in a prison is considered is as the fault of the bloggers and they are being laid off.

4. Recently, BBC reported that Prime Minister Hailemariam Desalegn insisted that we not real journalists and we had terror links. Likewise, other government officials also routinely give similar unconstitutional opinions which infringes the court’s pronouncement of our innocence.

Leaving these issues unattended is making us to feel as if we are living under a house arrest. The uncertainty coupled with and other issues putting us in an incredible amount of pressure to censor ourselves. Hence, we request the Ethiopian government or the concerned government agency

1. To respect our freedom of movement
2. To return our seized properties and confiscated passports back
3. To respect the court’s pronouncement of our innocence.

Respect the Constitution
Zone9 Bloggers & Journalists

Thursday, 19 November 2015

እነ የሺዋስ አሰፋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መልዕክት አስተላለፉ

‹‹áˆ­áˆƒá‰ĄáŠ• ለዓለም ለማሳወቅ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ሾል መሰራት አለበት››
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለህዝብ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ መልዕክቱን ያስተላለፉት በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙት የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ ሲሆኑ በተለይ ርሃቡ ለዓለም ማህበረሰብ እንዲታወቅ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበረሰቦች፣ ሚዲያውና ሌሎችም የቻሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አደራ ብለዋል፡፡

በተለይ ከመንግስት ርሃቡን የመደበቅ ባህሪ አንፃር በሌሎች ኢትዮጵያውያን በኩል ርሃቡን ለዓለም ለማሳወቅ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ሾል መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ ‹‹á‰ áˆ­áˆƒá‰Ą ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት መጥፋት አልነበረበትም›› ያሉት የፖለቲካ አመራሮቹ መንግስት ተራበ በተባለው ህዝብ ቁጥር ጨዋታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ለተራቡት መድረስ እንደነበረበትም ገልፀዋል፡፡ መንግስት የተራቡትን ቁጥርና መረጃ ስለሚደብቅም ኢትዮጵያውያን ርሃቡን ለዓለም በማሳወቅ እርዳታ እንዲገኝ ከማድረግ ባሻገር እርዳታ በማሰባሰብ ሊያግዟቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ከርሃቡ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ መልስ አለማግኘቱን፣ ህገ ወጥ የእስረኛ አያያዝ፣ የፍርድ ቤቶች ገለልተኛ አለመሆንና በአጠቃላይ የፍርድ መጓደልን በስፋት ያነሱት ሲሆን እነዚህ ጉዳዮች አጀንዳ ሆነው በጠነከረ መልኩ ወደ አደባባይ መውጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ችግሮችና ጭቆና ቢኖርም አጀንዳ ሆኖ መታገያ እየሆነ አይደለም ሲሉ ትዝብታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎችም መንገዶች አጀንዳዎቹ ለህዝብ መድረስ እንዳለባቸው መክረዋል፡፡

Wednesday, 18 November 2015

በውጭ ሃገር ያሉ ኢትዮጵያውያን የተራቡ ኢትዮጵያውያንን እንዳይረዱ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በየሃገራቱ መግለጫ እያወጡ ነው (ይዘናቸዋል)

(ዘ-ሐበሻ) 15 ሚልዮን ሕዝብን ለረሃብ የዳረገው የድርቅ አደጋ በየቀኑ የሰው ሕይወትን እየቀጠፈ መሆኑን የተረዱ ኢትዮጵያውያን በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርጉትን እንስቅቃሴ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ሕገወጥ ነው በሚል መግለጫ በማውጣት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን እንዳይረዱ በማከላከል ላይ እንደሚገኙ ታወቀ::

ዘ-ሐበሻ ከትናንት በስቲያ ባቀረበችው ሰበር መረጃ መሠረት መንግስት በድርቁና ረሃቡ የተነሳ መልካም ስሜ እየጠፋ ነው በሚል “ረሃብ አልተከሰተም… የሞተ ሰውም የለም” በሚል እያስተባበለ ይገኛል:: የመንግስት ሚዲያዎችና ኢምባሲዎች እንዲሁም ከፍተኛ ባለስልጣናት ከጠ/ሚ/ር ጽሕፈት ቤት; የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የመንግስት ኮምዩኒኬሽን መስሪያ ቤት በተላለፈላቸው ት ዕዛዝ መሰረት ይህንኑ ረሃብ የለም የሞተም የለም ዘገባ በሰፊው እያሰራጩት ይገኛሉ::

ኢምባሲዎች በሚገኙበት ሃገራት ኢትዮጵያውያን ማንኛውንም የገንዘብ ማሰባሰብ እንዳያደረጉ በማከላከል ሼል ላይ እንዲሰማሩ በወረደላቸው ት ዕዛዝ መሰረት “ሕዝቡ ገንዘብ እንዳያዋጣና ረሃብም አልተከሰተም; መንግስት ጉዳዩን ተቆጣጥሮታል” በሚል ደብዳቤ እየበተኑ ይገኛሉ::

በሳዑዲ አረቢያ; በዱባይ; በአቡዳቢ የሚገኙ ቆንስላዎች እና ኢምባሲዎች በረሃቡ ስም ሕዝቡ ገንዘብ እንዳያዋጣ ቢያከላክሉም ሕዝቡ ግን ገንዘቡን ለመንግስት ባንሰጥም በውጭ ድርጅቶች በኩል ለሕዝቡ እንዲደርስ እናደርጋለን በሚል በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ እየሰበሰበ ይገኛል:: መንግስት በውጭ ሃገር የሚደረጉ የገንዘብ ማሰባሰቦች “ገጽታዬን” ያበላሸዋል በሚል ረሃቡን ለመደበቅ የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር የነገሩን የዘ-ሐበሻ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ይህ ረሃብ ስርዓቱን በወዳጆቹ ሃገራት ፊት እንዲዋረድ አድርጎታል ብለውናል::

ዘ-ሐበሻ ቀድማ በዘገበችው መሠረት በቢቢሲ ላይ ቀርባ ልጇ በርሃብ እንደሞተባት የገለጸችው ብርቱካን በደህነቶች አስገዳጅነት ልጄ የሞተው በበሽታ ነው ብላ እንድትናገርና በቲቭ እንድትቀርብ የተደረገውም ይኸው ገጽታን በማስተካከል ሰበብ ነው ተብሏል::
የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ከበተኗቸው ደብዳቤዎች መካከል የተወሰኑትን እነሆ::



Sunday, 15 November 2015

ጋዜጠኞች ረሀቡን እንዳይዘግቡ ገደብ ተቀመጠ

(ዋዜማ ሬዲዮ) በሀገሪቱ የተከሰተውን ረሀብ በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ለዓለም ህዝብ ይፋ መሆኑን ተከትሎ መንግስት መረጃዎችን ለማፈንና ለመደበቅ እየሞከረ ነው።

መንግስት ለክልል መንግስታትና በውጪ ሀገራት ላሉ ኤምባሲዎቹ ባስተላለፈው መመሪያ ረሀብ ወደ ተከሰተበት አካባቢ ጋዜጠኞች እንዳይሄዱ፣ የረድዔት ድርጅት ሰራተኞችም መረጃ እንዳያቀብሉ ብርቱ ጥረት እንዲደረግ አሳስቧል።

“ሁኔታውን ተጠቅመው የልማት ስኬታችንን ለማንኳሰስ ያሰፈሰፉ ፅንፈኛ ተቃዋሚዎችንና ለኢትዮዽያ በጎ አመለካከት የሌላቸውን ግለሰቦችና ተቋማትን መመከት ይገባል” ሲል መክሯል መመሪያው። ሁሉም መንግስታዊ አካላት ኢትዮዽያ የድርቁን አደጋ ለመቋቋም የሚያስችል በቂ አቅም እንዳላትና ጅምር የልማት ስራዎችን ላለማደናቀፍ አለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ማስፈለጉን አፅንኦት ስጥተው እንዲያብራሩ አሳስቧል መመሪያው።

ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮዽያ ለመግባት በሚጠይቁ ጋዜጠኞች ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ገደብ እንዲደረግና ለኢትዮዽያ በጎ አመለካከት ያላቸው ብቻ እንዲፈቀድላቸው፣ አስፈላጊው ማብራሪያም እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ አስተላልፏል።

wazema radio

Saturday, 14 November 2015

‹‹áˆ­áˆƒá‰ĄáŠ• ያመጣው የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው!›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

 áŠáŒˆáˆ¨ ኢትዮጵያ
• ‹‹áˆˆáˆ˜áá‰ľáˆ„ው መረባረብ አለብን››
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት

‹‹á‹¨áˆ­áˆƒá‰Ą የቅርብ ጊዜ ምክንያቱ የዝናብ እጥረት ነው፡፡ የዝናብ እጥረት ድርቅን እስከተለ፡፡ ርሃቡን ያመጣው ግን የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው፡፡ የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ለረዥም ጊዜ፣ ለሀገር በሚጠቅም መልኩ ታቅዶ እንዳይሰራ አድርጎታል፡፡ ኢህአዴግ የሚሰራው ለአጭር ጊዜ የፖለቲካ ጥቅም እንጅ ለህዝብ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ የሚሰራው አቅዶ ቢሆን፣ 10 አመት አደግን ተብሎ የ2 ወር ዝናብ መጥፋት ይህን ያህል ርሃብ ባላስከተለ ነበር፡፡ አሁን በየቀኑ የሚያወሩልን የውሸት ክምር ነው፡፡

የጭካኔያቸው ጭካኔ ደግሞ፣ ያኔ ርሃብን የስልጣን መወጣጫ እንዳላደረጉት አሁን ይህን ያህል ህዝብ ተርቦ ‹‹á‹¨áŠ á‹áˆ­ ድርጅት በዓሉን አከበረ፣ ብአዴን የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው›› የሚል ዜና ነው በመንግስት ሚዲያ የምንሰማው፡፡ ይህን የሚያደርጉት ሾለ ርሃቡ እንዳይሰማ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ጨካኞች እንደሆኑ፣ ከህዝብ ጋርም እንደተጣሉ ነው፡፡ ተግባራቸው ሁሉ የእብሪት እንጅ ህዝብን የሚጠቅም አይደለም፡፡

አገዛዙ ለርሃቡ ትኩረት አልሰጠም፡፡ በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያውያን ዋናው ትኩረታችን መሆን ያለበት መፍትሄው ላይ ነው፡፡ በችግሩ የተጎዳው ህዝቡ፣ እንዲሁም መፍትሄም የሚያመጣው ህዝቡ መሆኑን አውቀን መረባረብ ይገባናል፡፡ ለችግሩም ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ የአደባባይ ሰዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ለዓለም መንግስታት ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያንና ደርጅቶች በሙሉ ልንረባረብ ይገባል፡፡ ለመፍትሄው መረባረብ አለብን!››

Thursday, 12 November 2015

Center for the Rights of Ethiopian Women welcomes Reeyot Alemu

Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) is delighted to announce the arrival of the award winning journalist, Reeyot Alemu to the United States on Saturday, November 7, 2015. CREW sent invitation to the respected journalist and freedom of speech advocate, Reeyot Alemu and her sister Eskedar Alemu to speak at the upcoming Women and Leadership Conference which will be held sometime in the coming month.

.CREW welcomes Reeyot Alemu

Reeyot has been imprisoned for over 4 years and was released in July of 2015. Reeyot was first sentenced to 14 years over “terrorism charges” that was later reduced to 5 years. Reeyot refused to admit guilt in exchange for her release and as a result she was in solitary confinement for 13 days.

Reeyot is a hero who is bold, defiant and had told her persecutors she would remain in prison rather than admit guilt for a crime that she never committed. Reeyot has inspired Ethiopians and generally all human right activists around the world with her courage and strength to fight for respect of human rights and freedom of expressions in Ethiopia. The International Women’s Media Foundation awarded Reeyot with the 2012 Courage in Journalism. UNESCO also recognized her for her “commitment to freedom of expression” with its Guillermo Cano World Press Freedom Prize in May, 2013.

CREW has great admiration for Reeyot’s courage and determination and considers her an inspiration to Ethiopian women of all ages. She is a role model to many Ethiopian men and women at home and abroad. CREW is honored to have Reeyot as a keynote speaker at its Women and Leadership conference. Please stay tuned for more information about the upcoming conference.

Wednesday, 11 November 2015

በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የተነሳ በቆቦ ወረዳ አንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ብቻ በየቀኑ 2 ህፃናት ይሞታሉ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ በተከሰተው ከባድ ድርቅ የተነሳ 15 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ:: ድርጅቱ ባወጣው መግለጫውም በሃገሪቱ ሰሜናማው ክፍል ለዘገባ በተመረጠ ቦታ ብቻ በረሃብ የተነሳ (በቆቦ ወረዳ አንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ብቻ) በቀን 2 ህፃናት ሕይወታቸው እንደሚያልፍ አስታውቋል::

ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳ ሰብል ማምረት እንዳልተቻለ ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት የሚጠበቀውን ያህል ማምረት እንዳልተቻለ ጠቅሷል:: በዚህም መሠረት የተባበሩት መንግስታት በድርቁ የተነሳ የተጎዱትን ለመርዳት ከ330 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል::

ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያምም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቅርቡ በሰጧቸው ቃለምልልሶች በዚህ ረሃብ የሞተ ሰው የለም ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ የቢቢሲ ዘገባ ሁለቱንም ሚኒስተሮች እርቃናቸውን ያስቀረ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ::

በ2016 መግቢያ ላይ ይህን ያህል ገንዘብ ኢትዮጵያውያኑን ለመመገብ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ሲያስቀምጥ ቢቢሲ በሰሜን ኢትዮጵያ በቆቦ አካባቢ ተዘዋውሮ ድርቁን እንደሚከተለው ዘግቦታል::



የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ በተከሰተው ከባድ ድርቅ የተነሳ 15 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ:: ድርጅቱ ባወጣው መግለጫውም በሃገሪቱ ሰሜናማው ክፍል ለዘገባ በተመረጠ ቦታ ብቻ በረሃብ የተነሳ (በቆቦ ወረዳ አንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ብቻ) በቀን 2 ህፃናት ሕይወታቸው እንደሚያልፍ አስታውቋል::
ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳ ሰብል ማምረት እንዳልተቻለ ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት የሚጠበቀውን ያህል ማምረት እንዳልተቻለ ጠቅሷል:: በዚህም መሠረት የተባበሩት መንግስታት በድርቁ የተነሳ የተጎዱትን ለመርዳት ከ330 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል::
ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያምም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቅርቡ በሰጧቸው ቃለምልልሶች በዚህ ረሃብ የሞተ ሰው የለም ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ የቢቢሲ ዘገባ ሁለቱንም ሚኒስተሮች እርቃናቸውን ያስቀረ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ::
በ2016 መግቢያ ላይ ይህን ያህል ገንዘብ ኢትዮጵያውያኑን ለመመገብ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ሲያስቀምጥ ቢቢሲ በሰሜን ኢትዮጵያ በቆቦ አካባቢ ተዘዋውሮ ድርቁን እንደሚከተለው ዘግቦታል::
- See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10946#sthash.wuoHPf1Q.dpuf

Tuesday, 10 November 2015

They can jail the journalist but not journalism



On November 7, 2015, journalist Serkalem Fasil posted a Facebook reminder. It was her husband’s birthday. “Four years and two months have passed since we physically separated,” she wrote.

No matter how long it takes, I will persevere and will never give up hope with the help of Almighty God,’” she promised to her husband. Sentenced to 18 years in jail on trumped-up terrorism charges in Ethiopia, Eskinder Nega cannot read the note from his beloved wife.

The couple have been through hell together that she certainly feels his presence and unbreakable spirit is with her at all times.

Ethiopian jailed journalist Eskinder Nega
Journalist Serkalem Fasil and Eskinder Nega proudly show off their son Nafkot and Menelik, one of banned newspapers they used to publish in Ethiopia.

When Serkalem met Eskinder nearly two decades ago, she could not have predicted the trials and tribulations awaiting them along their ways.

Eskinder is now serving 18 years behind bars for using pen and paper and sharing powerful stories and his thoughts with his people.

Theirs is a touching story of true love that has endured constant threats, attacks, prison, torture and exile spanning almost two decades. Serkalem leads a challenging life as an exiled “single mom” in Alexandria, Virginia, with their nine-year old son Nafkot, who was condemned to be born in jail.
Her husband is languishing in Kaliti jail, which he referred to as “Gulag” in a New York Times op-ed that he penned two years ago. After that article was published and exposed the harsh realities behind bars, he has been banned from having access to his lethal weapons, pen and paper. He is not allowed to read anything–even his Bible, which was confiscated by prison guards.

Charged with treason and “genocide”, Serkalem and Eskinder were among a group of journalists falsely accused of causing turmoil during the 2005 national election. Unprepared to accept any electoral defeats , the late Meles Zenawi declared a state of emergency and took personal control of the armed forces. Security forces massacred hundreds of unarmed peaceful protesters and injured almost 800 others. Scores of opposition leaders, journalists, human rights activists and civic leaders, along with some 30 thousand suspected supporters of opposition parties, were also jailed.

They languished in vermin-ridden jails, where their son Nafkot was born. Serkalem was denied prenatal care in prison under the orders of Meles Zenawi. The couple were released after 18 months behind bars with the condition that they “never write, never publish and never speak out against injustice”.

Terrorist journalists

In many parts of the world, journalism is a very dangerous profession. Whoever chooses to be a journalist ready to take on the challenges of telling truth to power and exposing wrongdoings, corruption, abuse of power or human rights violations knows the exorbitant costs and sacrifices that must be paid at one point or another.

In Ethiopia, journalism is not only dangerous but officially treated as an act of “terrorism”. Most of the “terrorists” convicted and jailed under Proclamation No. 652/2009, or the Anti-Terrorism Proclamation, are journalists and bloggers.

According to the latest CPJ’s data on exiled journalists, Ethiopia is the second top source of exiled journalists in the world after Syria, which took the top spot earlier this year. Fleeing from persecution and torture chambers, hundreds of journalists and writers have left the country and become hapless refugees and asylum seekers.

When Eskinder was denied permission to run his newspaper again, he resorted to publishing a series of hard-hitting blogs and opinion pieces online. In September 2011, he was arrested for the ninth times and charged with terrorism offenses.

The evidence presented in the federal Kangaroo court by the regime’s hack prosecutors was nothing but a collection of online stories and articles he had previously published. The most “damning evidence” the regime presented to prove Eskinder’s guilt was an opinion piece that contended that something like the Arab Spring was inevitable in Ethiopia unless the regime took serious political and economic reform measures. “Those who make peaceful revolution impossible will make violent revolution inevitable,” he warned quoting President John F. Kennedy.

In another op-ed–General Tsadekan, the EPRDF and the North African Revolution, he had revealed prior to his final arrest that he was detained by a group of armed men and taken to the then federal police commissioner Workneh Gebeyehu. The police boss fumed with anger and threatened him that they would no longer waste time to arrest him. “We will come to your house and will take the final action,” he told him.

Nonetheless, Eskinder was arrested again while he was picking up his son from school. His captors were cruelly videotaping his arrest mocking and laughing at the crying boy who begged them in vain to leave his dad alone.

The last decade has been the harshest for Ethiopian journalists. CPJ’s 2015 list of 10 Most Censored Countries ranked the country in fourth place, in league with North Korea, Eritrea, Saudi Arabia and Azerbaijan.

Empty rhetoric

BBC World Service Africa editor Mary Harper recently posed a few questions to “Prime Minister” Hailemariam Desalegn on the disturbing state of journalism in Ethiopia.
“Free media is very essential for the democratic process and development,” Hailemariam said. He seems to have a difficulty of distinguishing between democracy and tyranny.

Eskedar Alemu welcoming her sister Reeyot Alemu
Eskedar Alemu welcoming her sister Reeyot Alemu at Dulles International Airport.

Hailemariam insisted that the bloggers and reporters arrested and jailed were not real journalists. To him, they are all terrorists. “This has to be very clearly underlined because that shouldn’t be confused with the noble profession journalism and the work that journalists do in this country,” he said.
While Serkalem was trying to figure out a way to celebrate her jailed husband’s birthday, another journalist arrived from Ethiopia on the same day.

Reeyot Alemu spent over four years in jail. She was denied access to medical care despite the pain of a malignancy on her breast. She is another convicted “terrorist” who suffered a lot in solitary confinement until she was suddenly released last July in advance of President Obama’s visit to Ethiopia.

In her Facebook post, Serkalem also expressed her worries about another fiery journalist and her husband’s good friend, Temesgen Desalegn. Temesgen, the former publisher and editor of Feteh newspaper has also been denied access to medical care. He is not even allowed to get painkillers. They want him to bear unbearable pains physical and mental pains like so many others before him. This is how a desperate tyranny defends itself when it feels totally besieged by the brave warriors of truth.
As Eskinder wrote in his Letter from Ethiopia’s Gulag (NY Times, July 24, 2013):
"Tyranny is increasingly unsustainable in this post-Cold-War era. It is doomed to failure. But it must be prodded to exit the stage with a whimper — not the bang that extremists long for. I am confident that America will eventually do the right thing. After all, the new century is the age of democracy primarily because of the United States. Here in the Ethiopian gulag, this alone is reason enough to pay homage to the land of the brave."
The land of the free and home of brave that has guaranteed us freedom and granted us refuge in these dark hours should also hear the voices from faraway jails. America can exert its leverage, at least to prod and nudge its East African ally, to release the “terrorist” journalists for its own sake.
There is no journalism without those who take risks for the sake enlightening and informing the world.

All the brave journalists that go to war zones, confront powerful tyrannies and expose crimes and atrocities deserve attention. After all, they are the light of the world.

In a lengthy piece, “Letter to My Son”, Eskinder noted that his suffering for the sake of freedom and justice is exalting. But he never denied that the most unbearable pain to him is the physical separation from his beloved wife and son. He wrote movingly:

I miss you and your mother terribly. The pain is almost physical. But in this plight of our family is embedded hope of a long suffering people. There is no greater honor. We must bear any pain, travel any distance, climb any mountain, cross any ocean to complete this journey to freedom. Anything less is impoverishment of our soul. God bless you, my son. You will always be in my prayers.

Locking up, torturing and killing journalists has never been a show of strength and power. It only magnifies the very crimes and wickedness that perpetrators of such acts of terror want to hide from the rest of the world.

Tyrants that terrorize nations don’t seem to pay attention to one important fact. When true journalists suffer, journalism also suffers and feels the pain.

Eskinder is the living defiant embodiment of press freedom. He has been given major international awards and honors including PEN America’s Barbara Goldsmith Freedom to Write Award (2012), Golden Pen of Freedom Award of World Association of Newspapers and News Publishers (2014), PEN Canada’s One Humanity Award (2015). None of these coveted prizes are reserved for criminals, tyrants and terrorists.

Eskinder today is a free man because he has inspired the young bloggers of Zone 9. He has inspired thousands of Ethiopian “citizen journalists” who freely express themselves on social media.
Eskinder is the very face of journalism today. A face bloodied and bludgeoned by the wrath of tyrants but unbowed. A face menaced by 18 years of prison but unafraid.

His life in prison means only one thing. Tyrants can jail the journalists, but never journalism.
Journalism will never die. Journalism has outlived so many tyrannies in recorded history.

We shall never forget Eskinder Nega!

Monday, 9 November 2015

እነ የሺዋስ ለሶስተኛ ጊዜ ባልተገኙበት ቀጠሮ ተሰጠባቸው

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ዛሬ ጥቅምት 29/2008 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ ባልቀረቡበት ለህዳር 6/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም፣ ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም እንዲሁም ዛሬ ጥቅምት 29/2008 ዓ.ም እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው ለሶስተኛ ጊዜ በሌሉበት የተቀጠረባቸው አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ሀምታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሽበሺና አብሯቸው ይገብኝ የተጠየቀበት አቶ አብርሃም ሰለሞን ናቸው፡፡ 

ጥቅምት 22/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ማስረጃ ዝርዝር ከብይን ጋር ተያይዞ ባለመቅረቡ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ መርምሮ ለመወሰን ስላልቻለ፤ ይግባኝ ያስቀርባል አያስቀርባል የሚለውን ለመወሰን በእስር ፍርድ ቤቱ ያሉ ዝርዝር የአቃቤ ህግ ማስረጃዎች ተያይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበር ሲሆን በዛሬው ችሎት አቃቤ ህግ ማስረጃዎቼ ያላቸውን አያይዞ ቀርቧል፡፡ ይሁንና ፍርድ ቤቱ ‹‹áˆ˜áˆ¨áŒƒá‹Žá‰š ስላልተመረመሩ መርምሮ ይግባኝ ያስቀርባል አያስቀርብም የሚለውን ለመወሰን›› በሚል ለህዳር 6/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡

Saturday, 7 November 2015

ከዞን ዘጠኝ በኋላስ-ዝምታ?

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን መፈታትን ተከትሎ በኢትዮዽያ ውህኒ የሚማቅቁ ሌሎች ጋዜጠኞች ጉዳይ ተገቢውን ትኩረትና ድጋፍ እንዳላገኘ የሚያመላክቱ ፍንጮች እየታዩ ነው። አለም አቀፍ ተቋማትም ሆኑ የመብት ተቆርቋሪ ወዳጆች ሾለ ቀሪዎቹ ታሳሪዎች አስታዋሽ የሚፈልጉ ይመስላሉ።

በኢትዮጵያ መንግስት የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች አያያዝ ኹኔታ እየከፋ መምጣቱን ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች በሚሰሙ ቅሬታዎች እየተተገለጹ ነው። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የጋዜጠኛው ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ተመስገን ከጤናው መታወክ በተጨማሪ በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝና ምግብ እንዳይገባለት በመደረጉ ያለበትን እስር የከፋ ደረጃ ላይ እንዳደረሰው ተናግረዋል። ቤተሰቦቹ ከሚኖሩበት 165 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኘውየዝዋይ እስር ቤት የታሰረው ተመስገን ይህን ያህል ርቀት እየተመላለሱ እንዲጠይቁትና ስንቅ እንዲያቀብሉት በተገደዱት የቤተሰቡ አባላት ላይ የተጣለው እገዳ ተጨማሪ መንገላታት እንዳመጣባቸው ይናገራሉ።
ተመስገን ደሳለኝ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
ከጥቅምት 3/2007 ዓ.ም ጀምሮ የመንግስትን ስም ማጥፋት፣ ህዝብን ማነሳሳትና የህዝብን አመለካከት ማናወጥ በሚሉ ሶስት ክሶች፣ የቅጣት ርዝመት 3 አመት ጽኑ እስራት
ይህን የመሰለው ድርብ ቅጣት በተመስገን ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ይህን የመሰለ ችግር እየደረሰባቸው እንደኾነ ሲነገር ቆይቷል። ሌላው ታሳሪ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም ይህን የመሰለድርብርብ ቅጣት እንደተጣለበትም ይነገራል። በሽብርተኝነት ሴል ተካፍለሃል በሚል ሰበብ የ18 ዓመት እስር የተፈረደበት እስክንድር በተመሳሳይ ኹኔታ በቤተሰቡና በጓደኞቹ እንዳይጎበኝ ከመደረጉም በተጨማሪየሚያነበው መጽሐፍ እንዳይገባለትና ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዳይገናኝ ማዕቀብ ሲጣልበት መቆየቱም ሲዘገብ ነበር። ከዚህም በላይ በተደጋጋሚ በጭለማ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆይ ሲደረግ ቆይቷል።

መታሰሩ በራሱ የከፋ የመብት ጥሰትና በደል ሆኖ ሳለ ስለምን ነውረኝነት የተቀላቀለበትና የበቀል አያያዝ በጋዜጠኞች ላይ ይበረታል? የሚለው ጥያቄ – መልሱ ……የኢህአዴግ መንግስት ለዜጉቹ ባለው ዝቅ ያለ አመለካካትና ጥቂቶች ለስልጣናቸው ባላቸው ስስት ሳቢያ ነው።
እስክንድር ነጋ

                             ሳተናው፣ ወንጭፍ እና ምኒልክ የተባሉ ጋዜጦች አዘጋጅ
                             ጥፋተኛ የተባለበት ወነጀል ከአሸባሪነት ጨምሮ 23 ወንጀሎች
                             የቅጣት ውሳኔ የተሰጠበት ጊዜ ሐምሌ 6/2004 የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት
                            የቅጣት ርዝመት ለ18 ዓመታት

የውብሽት ደሳለኝ አያያዝም ከዚህ የተለየ አይደለም። ዘላለም ወርቃአገኘሁ፣ ዮናታን ተስፋዬና ባህሩ ደጉ በኢንተርኔት ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ይሰጣል የሚል መረጃ ደርሷቸው፣ በስልጠናው ለመወዳደር ማመልከቻ በመፃፋቸው የአሸባሪነት ክስ ቀርቦባቸው ከአንድ አመት በላይ ወህኒ እየተንገላቱ ነው።
“የፖለቲካ እስረኞች የሉም፣ ማንም ሰው በሚጽፈው ነገር ምክንያት ወይም ባለው የፖለቲካ አመለካከት ሰበብ አልታሰረም” እያለ የሚክደው የኢትዮጵያ መንግስት ይህን የመሰለውን ተደራራቢ ቅጣት በእነኚህና በሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ላይ መፈፀሙ ሰለሀገሪቱና ስለዜጎቹ ያለውን ዝቅ ያለ አመለካከት ያንፀባርቃል።

በእስረኞቹ ላይ ይህን በቀለ መሰል ተደራራቢ ቅጣት መፈጸሙ ለብዙዎች በእነዚህ ሰዎች ላይ የሚቀርበው ክስ ፖቲካዊ ለመኾኑማረጋገጫ ነው። እነዚህን ታሳሪዎችም ከሌሎች እስረኞች በተለየ አደገኛ ናቸው ብሎም እንደሚሰጋ የሚያሳይ ድርጊት እንደሚፈጸምባቸው ማሳያ እንደኾንም ለብዙዎች የማያከራክር ጉዳይ ነው።
ውብሸት ታዬ
የአውራምባ ታይምስ ምክትል-ዋና አዘጋጅWubshet
የታሰረው ሰኔ 2003 አ.ም
ጥፋተኛ የተባለበት ወንጀል በሽብርተኝነት ክስ
የጥፋተኝት ፍርድ የተሰጠበት ጊዜ ጥር 2004
የቅጣት ርዝመት 14 አመት ፡፡

የዞን 9 ጦማርያንና አብረዋቸው ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ጉዳይ ባልተጠበቀ ኹኔታ መንግስት የቀረበባቸውን ክስ በመተው ከክሱ ነጻ ናቸው የሚል ብያኔ ተሰጥቶ ከእስር ከመፈታታቸው በፊት ይህንኑ መሰል የተለየበደል ሲፈጸምባቸው እንደነበረ ሲነገር ቆይቷል። በቅርቡ የዞን 9 ጦማርያንና የጋዜጠኞቹን መፈታት እንደ ተስፋ ሰጪ በጎ ጅምር አድርገው የተመለከቱት ቢኖሩም እስካሁን ድረስ ሌሎቹ የፖለቲካ እስረኞችእንደሚፈቱ የሚያሳይ ፍንጭ የለም። በእስር ላይ ያሉበትም ኹኔታ ከቀድሞው በምንም ያልተለየ እንዲያውም እየባሰ መምጣቱን የችግሩ የቅርብ ገፈት ቀማሽ የኾኑት ቤተሰቦቻቸው እየተናገሩ ነው።
ዘላለም ወርቃገኘሁ ፣ ዮናታን ወልዴ ፣አብረሃም ሰለሞን እና ባህሩ ደጉZelalem Workagegnehu
ጥፋት የኢንተርኔት ደህንነት ስልጣና ለመካፈል ማመልከት
ክስ ሽብር ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኘነት
የታሰሩት ሀምሌ 2006

የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና አብረዋቸው ታስረው የነበሩት 3 ጋዜጠኞች ባልተጠበቀ ኹኔታ የመፈታት ጉዳይ አንዳንድ ተንታኞች ዘንድ በገዥው ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረ ድንገተኛ ለውጥ ምክንያት የተወሰደ ርምጃ ሊኾን እንደሚችል ግምት አሳድሮ ነበር። ይኹንና ይህን የመሰለ የአቋም ለውጥ መምጣቱን የሚያሳይ ቀጣይ ርምጃ ሲወሰድ አልታየም። ብዙዎችን የሚያስማማው ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት በዞን 9 ጦማርያንና በተፈቱት ሌሎች ጋዜጠኞች ባቀረበው ክስ ምክንያት የደረሰበትን ዓለማቀፋዊ ተጽዕኖ ለማርግብ ሲል ብቻ ይህን ያልተጠበቀ ውሳኔ ማሳለፉ ነው። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጉብኝትም ይህንኑ ዓለማቀፋዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ደረጃ ላይ አድርሶት እንደነበረ ይጠቀሳል።
ለዚህ ዓለማቀፋዊ ተጽዕኖ ምክንያት የነበረው ከሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በተለየ ለዞን 9 ጦማርያን ይደረግ የነበረው ዘመቻ #Freezone9bloggers በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን በዓለማቀፍ ደረጃም ሲወዳደር ብዙ ተሳታፊዎች የነበሩት እና ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት የሳብም ነበር።
በአገር ውስጥ ካለው ስም ይልቅ በውጪው ዓለም ላለው ገጽታው የሚፈራ የሚመስለው የኢትዮጵያ መንግስት እያንዳንዱ የፍርድ ሂደት እየተመዘነ የፈጠራ ክሶቹ ለስላቅ በመዳረጋቸው ባልጠበቀው ተጽዕኖ ሾር መውደቁ ይህን ከባህርይው ውጪ የኾነ ውሳኔ እንዲወስን ያስገደደው ይመስላል።
በተመሳሳይ ክስ ወንጀለኞች የተደረጉት ዘላለም ወርቅአግኘሁና ሌሎች 3 ጓደኞቹ አለመፈታታቸውም በመንግስት በኩል የተደረገ የአቋም ለውጥ አለመኖሩን ማሳያም ተደርጎ ይቀርባል።
ዘላለም ወርቅአግኘሁና ጓደኞቹ የቀረበባቸው ክስ የኢንተርኔት ደኅንነት (Internet Security) ስልጠና ለመውሰድ ማመልከታቸው ነው። ይህንንም መሰል ክስ በዞን 9 ጦማርያን ላይ ቀርቦ የነበረና መንግስትንም ለከፍተኛ ትችት ያጋለጠው መከራክርያው ነበር።

ይህን ስልጠና መውሰድም ይኹን ተግባራዊ ማድረግ ከማንኛውም ኢንተርኔት ተጠቃሚ ግለሰብ የሚጠበቅና የኢሜይል መልዕክቶችንም ይኹን በኢንተርኔት የሚደረጉ ማንኛውንም የመረጃ ልውውጦች በጠላፊ ወይም ሀከር እንዳይጠቃ የመጠበቅ የኢንተርኔት ሀ ሁ ነው። ብዙ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይህን ስልጠና ለጋዜጠኞችና ሰበአዊ መብት ተሟጋቾች ቢሰጡትም እንደ ወንጀል ሲቀርብ የታየው ግን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን አይቀርም። ዘላለም ወርቅአገኘሁና ጓደኞቹም ይህን ስልጠና ለማግኘት ያላቸው ምኞት ብቻ ከወንጀል ተቆጥሮ ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ላይ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሐሳብን በነፃነት መግለጽንና የፈለጉትን የፖለቲካ አቋም መደገፍን ወንጀል አድርጎ እንደሚቆጥር በተደጋጋሚ ቢከሰስም የዞን 9 ጦማርያንን በተመለከተ የተደረገውን ዓይነት ውጤታማ ዘመቻ ተደርጎበት አያውቅም።
አሁን በተመስገን፣ በእስክንድርና በነዘላለም ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ሲገልጹ የሚታዩት በዋነኝነት የቤተሰቦቻቸው አባላትና የቅርብ ጓደኞቻቸው ናቸው። ዓለማቀፍ የመብት ተሟጋች ቡድኖችም ችግሩ በዞን 9 ተጀምሮ በእነርሱ መፈታት ያቆመ ይመስል ድምጻቸውን ብዙም አያሰሙም። አንዳንድዕቹ የድረገጽ መረጃዎቻቸውን እንኳን ወቅቱን በጠበቀ መረጃ አላስተካከሉትም።
የእነዚህ እስረኞች ጉዳይ የቤተሰቦብቻቸው ችግር ብቻ ተደርጎ መተዉም ጉዳዩን በአገር ደረጃ ካለው የለውጥ ጥያቄ የነጠለው ይመስላል። በዚህ ወቅት ለዞን 9 ጦማርያን የተደረገውን ውጤታማ ዘመቻ ለመቃኘትና ለመብት መከበር ብለው ዋጋ እየከፈሉ ላሉ ጋዜጠኞች፣ ጦማርያን፣ የመብት ተሟጋቾችና የፖለቲካና የሐይማኖት መሪዎች አዲስ ዘመቻ የሚጀመርበት እንጂ ጉዳዩ የተደመደመ አይመስልም።

Source:: wazemaradio

Thursday, 5 November 2015

ረሃብ የመንግሰት ፖሊሲ ብልሹነት እንጂ የዝናብ እጥረት ዉጤት አይደለም!

ከኤፍሬም ማዴቦ...............ከአርበኞች መንደር !!

ደርግ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤን ስርዐት ከደመሰሰ በኋላ ወሎ፤ ትግራይና ሰሜን ሸዋ ዉስጥ ህዝብ እንደ ቅጠል ሲረግፍ እሳቸዉ የልደት በዐላቸዉን ለማክበር ከዉጭ አገር ኬክ ያስመጣሉ ብሎ ነበር ንጉሰ ነገስቱንና ስርዐታቸዉን የከሰሰዉ። በአስራ ሰባቱ የደርግ ዘመን ሁለት ግዜ ከባድ ረሃብ ተነስቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን አልቀዋል። በተለይ በ1977 ዓም ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተከሰተዉና የአለምን ህዝብ ያስደነገጠዉ ረሃብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያንን እንደ ቅጠል ሲያረግፍ ደርግ የስብሰባ አዳራሽ ለመስራትና የኢሠፓን ምስረታ ለማክበር ብዙ ሚሊዮን ዶላር እንዳባከነ ይታወሳል። ህወሃት የደርግን ስርዐት ሲዋጋ የኢትዮጵያን ህዘብ ከጎኑ ለማሰለፍ ከተጠቀመባቸዉ ዋና ዋና የፕሮፓጋንዳ ስራዎች ዉስጥ አንዱ ይህንኑ ረሃብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻቸንን ሲገድል ደርግና ባለሟሎቹ የፓርቲ ምስረታ ለማክበርና አዳራሽ ለማሰራት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያባክናሉ የሚል ፕሮፓጋንዳ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በአገሪቱ ዉስጥ ለደረሰዉ ረሃብ ዋናዉ ምክንያት የዝናብ እጥረት ሳይሆን የደርግ የተበላሸ የኤኮኖሚና የፖለቲካ ፖሊሲ ነዉ ብሎ ደጋግሞ ደርግን መክሰሱ አይረሳም። ህወሃት ኢትዮጵያን በመራባቸዉ ባለፉት ሃያ አራት አመታት ዉስጥ የዘንድሮዉን ጨምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ሦስት ግዜ ለረሃብ አደጋ ተጋልጧል። የዘንድሮዉ ረሃብ ደግሞ ስፋቱና ጥልቀቱ እጅግ በጣም አደገኛ መሆኑ በአለም አቀፍ የመገናኛ አዉታሮች እየተነገረ ነዉ።

ዛሬ ኢትዮጵያ በየአመቱ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዉጭ ዕርዳታ ታገኛለች፤ በየአመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ትበደራለች፤ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዉጭ ምንዛሪ በዉጭ አገር ከሚገኙ ዜጎቿ ታገኛለች። ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ የልማት ሰራዎች እንደሚሰሩ ይነገራል። ግድቦች፤ መንገዶች፤ ህንጻዎችና የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ይገነባሉ እየተባለ ይነገራል። የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአመት ከ10% በላይ እንደሚያድግ ይነገራል። ይህ ሁሉ ሆኖ ረሃብ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያንን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል። ለምን? ከህወሃት በፊት የነበሩት ሁለት መንግስታት በስልጣን ላይ በነበሩበት ግዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለደረሰዉ ረሃብና በረሃብ ላለቁ ወገኖቻችን ተጠያቂዎች ነበሩ። ደርግና የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ስርዐት የተከተሏቸዉ ብልሹ የሆኑ የኤኮኖሚ ፖሊሲዎችና ጎታች የመሬት ይዞታ አስተዳደር በሁለቱ ስርዐቶች ዉስጥ ለደረሰዉ ረሃብ አይነተኛ ምክንያቶች ነበሩ። ዛሬስ የሃያ ሚሊዮን ወገኖቻችንን ህይወት አደጋ ላይ ለጣለዉ ረሃብ ምክንያቱ ምንድነዉ? ተጠያቂዉስ ማነዉ? በነገራችን ላይ ህወሃት ሠላም አነገስኩባት በሚለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ረሃብተኛ ቁጥር ላለፉት አምስት አመታት በእርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰዉ ሦሪያ ዉስጥ ካለዉ ረሃብተኛ ቁጥር ይበልጣል።

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር አቶ መለሾ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዝብ በአጭር ግዜ ዉስጥ በቀን ሦስት ግዜ የመብላት ዋስትና ይኖረዋል ብለዉ ባዶ ተስፋ ከቀለቡን በኋላ የዘንድሮዉን አመት ጨምሮ እኛ ትዮጵያዉያን ሦስት ግዜ የረሃብ አደጋ ላይ ወድቀናል። ለመሆኑ ምን ይሆን ባለ ራዕዩ መሪ ያዩልን ራዕይ? በቀን ሦስት ግዜ መብላታችንን ወይስ ረሃብ ሦስት ግዜ እንደሚጎበኘን? ከአንድ አመት በፊት ክረምቱ መገባደጃ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያ ዉስጥ 6.5 ሚሊዮን ህዝብ የረሃብ አደጋ ይጠብቀዋል ብሎ ባስጠነቀቀ ማግስት ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ በምግብ ምርት እራሷን የቻለች አገር ሆናለች ብለዉ ለአለም አወጁ። እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በሰኔ 2015 ዓም እኚሁ ሰዉ ኢትዮጵያ ረሃብን በግማሽ እንደምትቀንስና በአመቱ ማለቂያ ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለረሃብ የሚጋለጠዉ ህዝብ ከ5% በታች እንደሚሆን አረጋገጡ። በተመድና በብዙ ለጋሽ አገሮች ጥናት መሠረት በ2015 ማለቂያ ላይ ከኢትዮጵያ ህዝብ 21% የሚሆነዉ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ካላገኘ ከፍተኛ አደጋ ይጠብቀዋል። ለምንድነዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሪ ነን ተብዬዎች የኢትዮጵያን ህዝብ የማይጨበጥ ባዶ ተስፋ የሚቀልቡት? ለምንድነዉ ፈጣኑና ታዳጊዉ የአፍሪካ ኤኮኖሚ ለዜጎቹ የስራ ዕድል መፍጠር ተስኖት ወጣት ኢትዮጵያዉያን አገራቸዉን እየጣሉ የሚሰደዱት? ለምንድነዉ በቀን ሦስቴ ትበላላችሁ ተብለን አንዱም ያረረብን? ለምንድነዉ በምግብ እህል እራሳችንን ችለናል ተብሎ ተነግሮን መንፈቅ ሳይሞላ ረሃብ የሚጨፈጭፈን? ለምንድነዉ? . . . ለምንድነዉ? . . . ለምንድነዉ?

በቅርቡ CNN እና ኒዮርክ ታይምስን ጨምሮ አያሌ ታዋቂ የአለማችን መገናኛ አዉታሮች ኢትዮጵያ ዉስጥ እየመጣ ያለዉን አስፈሪ የድርቅ አደጋ መዘገብ ሲጀምሩ ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ድርቅ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አዉስትራሊያንና አሜሪካንን ጭምር እንዳስቸገረ ገልጸዉ ነበር። ይባስ ብለዉም “ኤልኒኖ” የተባለዉን የተፈጥሮ ክስተት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለተከሰተዉ ድርቅ ተጠያቂ አድርገዋል። የሚገርመዉ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝና መንግስታቸዉ ዛሬ ምግብ ካልሰጣችሁን በረሃብ ልናልቅ ነዉ እያሉ የሚወተዉቱት እንደ ኢትዮጵያ እነሱንም ድርቅ መቷቸዋል ያሉትን አሜሪካንና አዉስትራሊያን ነዉ። በነገራችን ላይ ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ትክክል ናቸዉ – ድርቅ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደገባ ሁሉ አሜሪካና አዉስትራሊያ ዉስጥም ገብቷል፤ ኤልኒኖም ኢትዮጵያ ዉስጥ በተከሰተዉ የአየር ጸባይ መዛባት ላይ ተፅዕኖ ነበረዉ። ሆኖም እሳቸዉ ሾል ስለሚበዛባቸዉ ረስተዉ ሳይጠቅሱት ቀረ እንጂ ድርቅ ጎረቤት አገር ኬንያ፤ ሱዳንና ኤርትራ ዉስጥም ገብቷል። ጠ/ሚኒስትሩ የኮነኑት ኤልኒኖም ቢሆን ኤርትራንና ኬንያን ዘልሎ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ አልመጣም። ድርቅ ማለት ደግሞ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠዉ በቀር የዝናብ እጥረት ማለት ነዉ። ዝናብ በተከታታይ ካልዘነበ ዬትም አገር ዉስጥ ድርቅ ይከሰታል። ነገር ግን ድርቅ ሁሉም አገር ዉስጥ ወደ ረሃብ አይለወጥም። ድርቅን አስመልክቶ በአገሮች መካከል ያለዉ ትልቁ ልዩነትም እዚህ ላይ ነዉ። አንዳንድ አገሮች ድርቅን በሩቁ ያዩና ዝግጅት አድርገዉ ረሃብን ይከላከላሉ፤ እንደ ኢትዮጵያ አይነቶቹ በልመና የተካኑ አገሮች ደግሞ ድርቁ ወደ ረሃብ እስኪለወጥ እጃቸዉን አጣጥፈዉ ይጠብቁና ህዝቡ ሲራብ አለም አቀፉን ህብረተሰብ “ሾለ ማሪያም” ማለት ይጀምራሉ።

በቅርቡ ፕሮፌሰር መስፍን በግልጽ እንደተናገሩት አገራችን ኢትዮጵያ ክብሯንና ኩራቷን ለምዕራባዉያን አሳልፋ የሸጠች አገር ሆናለች። ምዕራባዉያንም በተለይ አሜሪካና ታላቋ ቢሪታኒያ ለዚህ በርካሽ ዋጋ ለገዙት ክብርና ልዕልና ሲሉ ኢትዮጵያን እንደ በኩር ልጃቸዉ በአንቀልባ ታቅፈዉ እሹሩሩ ሲሉ ከርመዋል፤ አሁንም እያሏት ነዉ። የአሜሪካዉ ባራክ ኦባማና የእንግሊዙ ዴቭድ ካምርን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ኢትዮጵያን ሲጠቅሱ ተአምረኛዉ ኤኮኖሚ፤ በድርብ አኃዝ የሚያድገዉ ኤኮኖሚ ወይም የአፍሪካ ፈጣኑ ኤኮኖሚ እያሉ ነዉ። የህወሃት አገዛዝም ጧትና ማታ ስራዬ ብሎ የሚደክመዉ “ተዳጊዉ ኤኮኖሚ” ለመባል ነዉ እንጂ የ96 ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያንን ህይወት ለመለወጥ አይደለም። ለዚህም ነዉ 15 አመት ሙሉ ፈጣን ዕድገት፤ ህዳሴ፤ ትራንስፎርሜሺን እየተባለ በተዘፈነባት አገር ዉስጥ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎች (ከጠቅላላዉ ህዝብ 1/3ኛዉ) በቀን የተመድ የድህነት መመዘኛ ከሆነዉ ከ$1.25 በታች እያገኘ በድህነት የሚማቅቀዉ።ግሎባል ፖስት የተባለ የዜና ማዕከል በቅርቡ ኢትዮጵያ በ30 አመት ዉስጥ ታይቶ የማይታወቅ የረሃብ አደጋ ዉስጥ ወድቃለች ካለ በኋላ ለመሆኑ ይንንን አደጋ የኢትዮጵያ መንግስት መቋቋም ይችላል ወይ ሲል ጠይቋል። ይህንን ጥያቄ ለመመለሾ የኢትዮጵያ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠዉ ለምንድነዉ የሚለዉን ጥያቄ መመለሹ የሚበቃ ይመስለኛል። የህወሃት አገዛዝ አይን ላወጣ ዘረፋና ለሜዲያ ፍጆታ በሚያመቹ ፕሮጅክቶች ላይ ካማተኮሩ በፊት ቅድሚያ የሚሰጠዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር ለመጠበቅ፤ የኢትዮጵያን ህዘብ ልመና ይዞት ከሚመጣዉ ዉርደትና የሂሊና ዝቅጠት ለማዉጣትና ረሃብን ከአገራችን ምድር ለማጥፋት ቢሆን ኖሮ ረሃብ ከኢትዮጵያ የሚጠፋዉ ዛሬ ሳይሆን ህወሃት የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን በተቆጣጠረባቸዉ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ይሆን ነበር።

The Famine Early Warning Systems Network (FEWS Net) የተባለ ድርጅት ኢትዮጵያ ዉስጥ የምግብ እህል ምርት ከሚጠበቀዉ በታች መሆኑን ወይም ይመረታል ተብሎ የሚጠበቀዉ ምርት አገሪቱ ከሚያስፈልጋት የምርት መጠን እጅግ በጣም ያነሰ መሆኑን በግዜ አስጠንቅቆ ነበር። ለመሆኑ ለዚህ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠዉ ምላሽ ምን ነበር? እርግጠኛ ነኝ FEWS Net ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአካባቢዉ ድርቅ ለሚያዘወትርባቸዉ አገሮች መንግስታትም የድርቅ አደጋን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። ሌሎች መንግስታት ለዚህ ማስጠንቀቂያ የሰጡት ምላሽ ምን ይሆን? የኢትዮጵያ መንግስትስ በራሱም ቢሆን እንዲህ አይነቱን በዝናብ እጥረትና በአየር ሁኔታ መለዋወጥ የተነሳ ሊከሰት የሚችለዉን የምግብ እጥረት ከግምት ዉስጥ ያስገባ ጥናት በየአመቱ ማካሄድ አይገባዉም ነበር?

በ1977 ዓም በአገራችን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ረሃብ ትግራይ፤ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዉስጥ የሰዉን ልጅ እንደ ቅጠል ሲያረግፍ የዚህ ጸሁፍ ፀሀፊ የሰሜን ኢትዮጵያ ፕላን ቀጣና ጽ/ቤትን ወክሎ ትግራይ ዉስጥ ይሰራ ነበር። በወቅቱ የትግራይ ጎረቤት ክፍለሀገር በነበረችዉ ኤርትራ ዉስጥ ድርቅ ቢኖርም ረሃብ የሚባል ነገር አልነበረም። ዛሬ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለት የተለያዩ አገሮች ከሆኑ ሩብ ምዕተ አመት ሊሆን በወራት የሚቆጠር ግዜ ነዉ የሚቀረዉ። አንድ ነገር ግን ዛሬም አልተለወጠም። ኢትዮጵያና ኤርትራ ዉስጥ ዛሬም ድርቅ አለ፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ድርቁ ዛሬም ወደ ረሃብ ተለዉጦ የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል። ኤርትራ ዉስጥ ግን ድርቅ ቢኖርም ድርቁ ወደ ረሃብ አልተለወጠም፤ ወይም የኤርትራ መንግስት እንደ ኢትዮጵያ መንግሰት ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ የምግብ ያለህ የሚል የልመና ጥሪ አላቀረበም። ለምን?

ኤርትራ የምዕራቡ አለም በተለይ የአሜሪካ መንግስት የማይገባ ማዕቀብ ጥሎባት ከዉጭ አገር ቤሳ ቤስቲን የማታገኝ አገር ናት። ኢትዮጳያ ግን በጥቁር አለም ዉስጥ ከፍተኛዉን የዉጭ ዕርዳታ የምታገኛ አገር ናት። የኤርትራ ኤኮኖሚ የራሱ በሆነ መንገድ እያደገ ቢሆንም በአሜሪካ የሚመራዉ የምዕራቡ አለም ይህንን ዕድገት መመስከር አይፈልግም። የኤርትራ መንግስትም ቢሆን እንደ ወያኔ በነጋ በጠባ አደግን እያለ ጥሩምባ አይነፋም። ኤርትራ አንድም አመቱን ሙሉ የሚፈስ ወንዝ የሌለባት አገር ናት፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የወንዞች ማማ ተብላ የምትጠራ አገር ናት። ኤርትራ ዉስጥ አንድም ሐይቅ የለም፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን የሀይቁን ብዛት መቁጠር ያዳግታል። ኢትዮጵያ ያላት የእርሻ መሬት ስፋቱ ከጠቅላላዉ ኤርትራ የቆዳ ስፋት እጅግ በጣም ይበልጣል። የቀድሞዉ የወያኔዉ ጠ/ሚኒስቴር በቀን ሦስቴ እንበላለን ብሎ ትንቢት ነግሮን ነበር፤ ይህ ትንቢት ሳይፈጸም ነበር እሱን የተካዉ ሰዉ ከዛሬ ወዲህ በምግብ እህል እራሳችንን ችለናል ብሎ ለአለም ህዝብ ያወጀዉ። የኤርትራ መንግስት በእንደነዚህ አይነት ተራ የሜዲያ ፍጆታዎች ግዜዉን ሲያጠፋ አናይም። ለአገሩ ህዝብ የሚያስፈልገዉን የምግብ ፍጆታ አሟልቶ አገሩን ከረሃብ አደጋ ሲከላከል የምናየዉ ግን የኤርትራ መንግስት ነዉ። እነዚህን በሁለቱ አገሮች መካካል የሚታዩትን ልዩነቶች ያነበበ ሰዉ ሁሉ አንድ ሊገነዘበዉ የሚገባ ትልቅ ሀቅ አለ። እሱም ኢትዮጵያ ዉስጥ በመንግስት ብልሹ የኤኮኖሚና የፖለቲካ ፖሊሲ የተነሳ ድርቁ ወደ ረሃብ ተለዉጦ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል። የኤርትራ መንግስት ግን የድርቁን መምጣት አስቀድሞ ስለተገነዘበ እርምጃ በመዉሰዱ ኤርትራ ዉስጥ የገባዉ ድርቅ ወደ ረሃብ አልተለወጠም። በመሆኑም ዛሬ ኤርትራ ዉስጥ ረሃብ የለም። ኤርትራ ዉስጥ ድርቁ ወደ ረሃብ አለመለወጡ የሚያሳየን ኤርትራዉያን ልዩ ፍጡሮቸ መሆናቸዉን ሳይሆን የሁለቱ አገር መንግስታት ቅድሚያ የሚሰጡት ለምን እንደሆነና በሁለቱ መንግስታት መካክል ያለዉን ከፍተኛ የፖሊሲ ልዩነት ነዉ። ወያኔ የሚያጮኸዉ የድርብ አኃዝ ዕድገትና የህዳሴ ጩኸት ከቅርብም ከሩቅም ይሰማል። በኤርትራና በኢትዮጵያ መንግስታት መካከል በምግብ ራስን መቻልን አስመልክቶ የሚታየዉ ከፍተኛ የፖሊሲ ልዩነት ግን በቀላሉ አይታይም። ኤርትራ ላይ የተጣለዉ ማዕቀብ እንዳይነሳ የሚፈልጉት አሜሪካኖችማ በተለይ እነ ሱዛን ራይስን የመሳሰሉ የአዕምሮ አይነስዉራን ይህንን ልዩነት ቢታይም ማየት አይፈልጉም።

ድርቅ ድንበር አይልም፤የፖለቲካ ስርዐት አይልም፤ ደሃና ሀብታም አይለይም- አገር ከአገር ህዝብ ከህዝብ አይለይም። ድርቅ በዬትም አገር ዉስጥ በማንኛዉም ግዜ ሊከሰት የሚችል የተፈጥሮ ክስተት ነዉ። የሰዉ ልጅ ድርቅ ይዟቸዉ ሊመጣ የሚችለዉን አደጋዎች ነዉ መቆጣጠር የሚችለዉ እንጂ ድርቅን እራሱን መቆጣጠር አይችልም። ዝናብ በተከታታይ ከጠፋ ድርቅ መምጣቱ አይቀሬ ነዉ። በ2007 ዓም ኢትዮጵያ ዉስጥ የገባዉ ድርቅ ኤርትራ ዉስጥም ገብቷል። ሁለቱ አገሮች የዝናቡ እጥረት ወደ ድርቅ ከመለወጡ በፊትና በኋላ የወሰዷቸዉ እርምጃዎች ግን የሰማይና የምድርን ያክል የተራራቁ ናቸዉ። እነዚህ ሁለቱ አገሮች የወሰዷቸዉ የተለያዩ እርምጃዎች ናቸዉ ዛሬ ኢትዮጵያን የምግብ ለማኝ ኤርትራን ደግሞ በራሷ የምትተማመን አገር ያደረገዉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ድርቅ እየመጣብህ ነዉ ተብሎ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠዉ ትኩረት የሰጠዉ እየመጣ ላለዉ ረሃብ ሳይሆን ለ“እዩኝ እዩኝ” ፕሮጅክቶች ነዉ። ፕሮጀክቶች አያስፈልጉንም ማለቴ አይደለም። ያስፈልጉናል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በረሃብ እያለቀ ደርግ አዳራሽ ይሰራል ብሎ የወነጀለ አካል የሱም ትኩረት በመጀመሪያ የህዝብን የምግብ ፍላጎት መሟላት እንጂ ህዘብ በረሃብ እያለቀ ሌላ ሌላ ፕሮጀክት ላይ ማተኮር አልነበረበትም። የኤርትራ መንግስት የ2007 ዓም ዝናብ መጠን የእህል አምራች በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎች አስተማማኝ አለመሆኑን ሲረዳ ገና ከጧቱ ነበር ከተለያዩ ምንጮች የምግብ እህል በግዢ በማሰባሰብ የአገሪቱን የምግብ ፍላጎት ማሟላት የጀመረዉ። ዛሬ የኤርትራ ህዝብ ስሙ በረሃብ የማይነሳዉ ኤርትራ ዉስጥ ድርቅ ስላልገባ አይደለም። የኤርትራ መሪዎች ድርቁ ወደ ረሃብ ከመለወጡ በፊት ቀድመዉ የወሰዱት እርምጃ አገራቸዉን ከረሃብ አደጋ ስላዳነዉ ነዉ። የኛ መንግስታት ግን ንጉሱም ሆኑ፤ ደርግ ወይም ወያኔ ድርቅ ወደ ረሃብ ተለዉጦ ህዝብን ሲጨርስ ምግብ መለመን ነዉ እንጂ ዛሬ ትንሿ አገር ኤርትራ እንዳደረገችዉ የድርቅን መምጣት አይተዉ ረሃብን ተከላክለዉ አያዉቁም። ለዚህ ነዉ መሰለኝ ኢትዮጵያ ዉስጥ በድርቅና በረሃብ መካከል ልዩነት ያለም አይመስልም።

እዉነትን ማሞጋገስና በዉሸት አለቆች ሰትደፈጠጥ ደጋግፎ ማቆም እስትንፋሴ እስካለች ድረስ በፍጹም የማልተወዉ ቋሚ ስራዬ ቢሆንም የዚህ ጽሁፍ አላማ ግን የኤርትራን መንግስት ማሞጋገስ አይደለም። እሱ የኤርትራዉያን ሾል ነዉ። የዚህ ጽሁፍ ብቸኛ አላማ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዛሬ የ20 ሚሊዮን ዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የጣለዉ ረሃብ መንስኤዉ የዝናብ እጥረት ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት ቅደም ተከተሎች ያላስተዋለ ብልሹ የመንግስት ፖሊሲ ዉጤት መሆኑን ለማሳየት ነዉ። ይህና ይህ ብቻ ነዉ የዚህ ጽሁፍ አላማ። ቸር ይግጠመን።

ኤፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር
ebini23@yahoo.com

መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ

• በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው
• ‹‹áˆ°á‹ በርሃብ እያለቀ ነው››
• ‹‹á‹¨áˆšáˆ‹áˆľ የሚቀመስ የለም፡፡ ቤተሰባችን ፈርሷል››
• ‹‹áŠĽáˆ­á‹łá‰ł ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አንመጣም ነበር፡፡››

 áŠáŒˆáˆ¨ ኢትዮጵያ

መንግስት በርሃብ ለተጎዱት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ቀያቸውን ለቀው አዲስ አበባ የገቡት የርሃቡ ሰለባዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች በርሃብ የተጠቁ ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወሎ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች አልፈው ወደ ጎጃም፣ ጎንደርን እንዲሁም አዲስ አበባ እየተሰደዱ ሲሆን አዲስ አበባ በርካታ ተጎጅዎች ህፃናትን አዝለው እየለመኑ ይገኛሉ፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ካነጋገራቸው መካከል ሁሉም መንግስት ለርሃቡ ተጎጅዎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውና ጎረቤቶቻቸውም እንደነሱ ቀያቸውን ጥለው ወደ መተማ፣ ሁመል፣ ባህርዳር፣ ደሴ፣ እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ መሰደዳቸውን በሀዘን ገልፀዋል፡፡

ወሎ ውስጥ ጮሬ ሶዶማ ከተባለ ቦታ ተነስታ እንደመጣች፣ አዲስ አበባ ከገባች ሶስት ሳምንት እንደሆናት የገለፀችውና ሁለት ህፃናትን ይዛ ስትለምን ያገኘናት፤ በግምት በ30ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ የምትገኝ እናት ‹‹á‹¨áˆ˜áŒŁáŠá‹ የሚላስ የሚቀመስ ስለሌለ ነው፡፡ ከብቶቻችን አልቀዋል፡፡ አዝመራ የሚባል የለም፡፡ ሰው በርሃብ እያለቀ ነው፡፡ እኛ ሴቶቹ ወደ ከተማው ስንመጣ ወንዶቹ ደግሞ ወደ ሁመራና መተማ ሄደዋል፡፡ እኛም ከዚህ የመጣነው ጉልበት ስላለን ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ደካሞች በዛው አካባቢ ቀርተዋል፡፡›› ስትል በሀዘን ገልፃልናለች፡፡ መንግስት እርዳታ አይሰጥም ወይ ብለን ላነሳንላት ጥያቄም ‹‹áˆáŠ•áˆ እርዳታ አልተሰጠንም፡፡ እርዳታ ቢሰጥ ኖሮ ቤታችን ጥለን አንመጣም ነበር፡፡ ባያበቅልም መሬት አለን፡፡ የከተማው ሰው ይሻላል ብለን ነው ወደዚህ የመጣነው›› ስትል ሾለ ርሃቡ አስከፊነትና መንግስትም እርዳታ እየተሰጠ እንዳልሆነ ገልፃልናለች፡፡

ባለቤቷ ወደ መታማ ሲሄድ እሷም ቤቷን ጥላ ወደማታውቀው አዲስ አበባ እየጠየቀች እንደመጣች የገለፀችልን ወጣት በበኩሏ ‹‹á‰¤á‰´ ተፈትቷል፡፡ ባለፈው አመት ከብቶችም እህልም ነበረን፡፡ ዘንድሮ ግን ምንም ነገር የለም፡፡ ጊዜው ከፍቷል፡፡ ባሌ ወደ መተማ ሄዷል፡፡ እኔም ልጄን አዝዬ እስከ ደሴ በእግሬ መጣሁ፡፡ ከዛ በኋላ እየለምንኩ ከዚህ ደርሻለሁ፡፡ ማንም እርዳታ አልሰጠንም፡፡›› ስትል ስለሁኔታው ገለፃልናለች፡፡

ከመርሳ ወረዳ እንደመጡ የገለፁልንና ከልጃቸው ልጅ ጋር እየለመኑ ያገኘናቸው የ65 አመት አዛውንት በበኩላቸው ‹‹á‹áŠ“ብ ሲቀር ከብቶቻችንም ሞቱ፡፡ አዝመራ የሚባልም ነገር የለም፡፡ ከመርሳ ደሴ እየለመንኩ መጣሁ፡፡ ደሴም እንደኛ ብዙ ሰው አለ፡፡ አገኝ ብሎ በየከተማው ተሰራጭቷል፡፡ ወደዚህ ይሻላል ብዬ በለመንኳት ተሳፍሬ መጣሁ፡፡ ርሃቡ ሲብስብን ወደማናውቀው አገር መጣን፡፡›› ሲሉ የርሃቡን አስከፉነት ገልፀውልናል፡፡

‹‹áŠĽáˆ­á‹ąáŠ!›› እያሉ እየለመኑ ያገኘናቸው ከኬሚሴ አካባቢ እንደመጡና ከ8 ቀን በፊት አዲስ አበባ እንደደረሱ የገለፁልን ሌላኛዋ እናትም ቤታቸውን ጥለው እንደመጡና፣ ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ወደ የት እንደሄዱ እንኳን እንደማያውቁ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ መንግስት እርዳታ እየሰጠሁ ነው እንደሚል ስንገልፅላቸው ‹‹áˆˆáŠĽáŠ” አልደረሰኝም፡፡ እርዳታ ተሰጠኝ ያለም አልሰማሁም፡፡ እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አልመጣም ነበር፡፡ አሁን ነው ከከተማው ሰው ትንሽ ትንሽ እያገኘን ያለነው፡፡ በየ ከተማው ስንደርስ ሰው አይነፍገንም›› ሲሉ ከህዝብ እንጅ ከመንግስት እርዳታ እንዳላገኙ ገልፀዋል፡፡

ካሳንቺስ አካባቢ ልጅ አዝለው ታክሲ ተሳፋሪዎችን ምንም አይነት ቃል ሳያሰሙ ልጃቸውን በመዘርጋት ብቻ እንዲረዷቸው እየጠየቁ ያገኘናቸው እናትም የራሳቸውንና የታዘለውን ልጅ ነፍስ ለማዳን ቀያቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

የርሃቡ ተጎጅዎች አዲስ አበባ ውስጥም ነፍሳቸውን ለማቆየት በጠራራ ፀሀይ ሲለምኑ እንደሚውሉና ምቹ ያልሆነ ቦታ አንድ ላይ የሚያድሩ በመሆኑ ልጆቻቸው ለበሽታ እየተጋለጡ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ተማሪ የነበሩና በርሃቡ ምክንያት ለማቋረጥ የተገደዱት ልጆቻቸው ከእነሱ ጋር ወይንም ወደ ሌላ አካባቢ ነፍሳቸውን ለመዳን መሰደዳቸውን፣ በያለፉበት ከተማም በርካታ ስደተኛ እንዳለም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

Wednesday, 4 November 2015

የታማኝ እዳ (እንግዳ ታደሰ)

እንግዳ ታደሰ – ኦስሎ
በቃል የምነት እዳ ሸክፎ ሸክሙን
እንደ ሴባስቶፖል ሽቅብ ቁልቁለቱን
ሲወጣና ሲወርድ ቋጥኝ አቀበቱን
እስቲ እንካፈለው የሃገር እዳውን ፡፡

Ethiopian activist Tamagne Beyene

እዳው በግል የናት አባት እዳ አይደለም ፡፡ የርሱ እዳ የዕምነቱ እዳ ነው ፡፡ ለሸክም የከበደ ፥ የሰው ፊት የሚያስገርፍ፥ ዕረፍት የሚነሳ ፥ ከወለዳቸውና ከሚወዳቸው ቤተሰቡ ለወራት የሚያቆራርጥ፣ እንደ አጼ ቴዎድሮስ መድፍ ሴባስቶፖል ሽቅብና ቁልቁል የሚያስሮጥ፣ ኢሳትን በግሩ ለማቆሞ የሚደረግ ትግል ፡፡

ይህ ሰው በህወሃት ቀንበር ሼር ተሸብቦ ድምጹ የታፈነውን የዘጠና ሚልዮን ህዝብ መከራና እዳ ብቻውን የተሸከመ እስኪመስል ከምድር ጫፍ ሰሜን ዋልታ ኖርዌይ ፣ እስከምድር ግርጌ ደቡብ አፍሪቃ ፥ ከዚያም አውስትራልያ ረጅም የጢያራ ጉዞ በማድረግ ኢሳት በባለቢሊዬኖሮቹ የህወሃት ቱጃሮችና ረዳት ከበርቴዎቻቸው እንዳይዘጋ የሰው ፊት እያሳቀቀው ምጽዋት ሲለምን ይታያል፡፡ በርግጥ ከጎኑ የቆሙ ቆራጥ ወገኖቹ ቢኖሩም ፣ ዳገቱን ሲያዘግም የብርታት ከዘራ የሚያቀብሉት ወገኖች ባይጠፉም፣ በዚያው አንጻር ደግሞ ምክንያት በሌለው ጥላቻ የሚጎንጡትም አልጠፉም ፡፡

ምናልባት ከአህጉር ፥ አህጉር ለርዳታ ሲዘዋወር ፣ የደላው የሚመስላቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ፡፡ አድካሚውንና እጅግም ሲበዛ ለበሽታ አሳልፎ የሚሰጠውን ረጅም ሰዓታት የአውሮፕላን ጉዞ ከግምት ውስጥ ያላስገቡ ተቺዎች የሚሰነዝሩት ባዶ አስተያየት እና የህወሃት ጭፍሮች ጥላቻም ጭምር እንደሆነ የታወቀ ነው ፡፡ የአባት ቅርብ ክትትልን የሚጠይቀውን ፥ በትምህርት ቤት ልጆች የሚሰጣቸውን የቤት ሥራና ከወላጆች ማግኘት የሚገባቸውን እርዳታን ፍቅር በአባት እምነት እዳ ምክንያት በቅርብ የሚያጡትን ልጆቹንም ማሰብ በተገባ ነበር ፡፡ ትልቁን የጋራ የቤተሰብ ኃላፊነት ታማኝ ለወራት የኢሳትን ዓላማ ለማሳካት ሲደክም ፣ እናትም ፥ አባትም ሆና በአሜሪካን አገር ኑሮና ፥ አስቸጋሪ የደህንነት ዋስትና በተመናመነባት አሜሪካ የምትንገላታውንም ውድ ባለቤቱንም ማሰብ ባስፈለገም ነበር ፡፡ በርግጥ ታማኝ ከህወሃት ሰዎችና ደጋፊዎቻቸው ይህን ነቀፋ ስለሚጠብቅ ብዙ የሚያሳስበው ጉዳይ አይደለም ፡፡ ይህ እዳ የታማኝ በየነ ፥ ይህ እዳ የሻምበል በላይነህ ፥ ይህ እዳ የአበበ ገላው ፥ ይህ እዳ የኤርምያስ ለገሰ ወዘተ እዳ ብቻ አይደለም ፡፡ ድምጹ የተሸበበት የዘጠና ሚልዮን ህዝብ እዳ ነው ፡፡

ኢትዮጵያ ከዘረኞችና ከባንዳዎች ነጻ ስትወጣ ፣ ሁሉም በነጻነት ወደ እናት ምድሩ ሲተም ፣ በእናት አገሩም ህይወቴና ሞቴ ከርሷ ይሁን ብሎ መኖር ሲጀምር ፣ ታማኝም እንደማንኛውም ዜጋ ነው አየሯን በነጻነት የሚስበው ፡፡ ለርሹ ለብቻው አየር አይጠለፍለትም ፡፡ ለርሹ አገሪቱ ለመጠጥ ከምታቀርበው የለገዳዲም ሆነ የገፈርሳ ውሃ ውጭ ልዩ የመጠጥ ውሃ ጅረት ለብቻው አትጠልፍለትም ፡፡ ይህ እንኳ እየተሰማ ያለው ፣ ከገዥዎቻችን መንደር ብቻ ነው ፡፡ ዛሬ ሰፈሬን በባለስልጣን ሰፈር ያድርገው እየተባለ እንደሚለመነው ፣ የህወሃት ባለስልጣኖች ካሉበት መንደር መብራትም ሆነ ዉሃ በፍጹም እንደማይጠፋ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው ? ለሃጣን በመጣ መብራትና ዉሃ በአክባቢው ያሉ ሰዎች እየበራላቸውም እየጠጡም ነው ፡፡

በኪነ ጥበቡ ዓለም የሚገኘው ሃብት የተሻለ ነው ፡፡ ዓለምን በመዞር ከሆነ ኪነጥበቡም ያዞራል ፡፡ ብብት ሳይኮረኩሩ አስቆ ሃብት በመሃረብ ሊቋጠር ይችላል ፡፡ ለአገር ነጻነትና ትንሳኤ ኢሳትን በግሩ እናቁም ተብሎ ለልመና ሲወጣ ግን የሰው ፊት ይገርፋል ፡፡ ታማኝ ባለፈው ሳምንት ኦስሎ ውስጥ በተደረገው አኩሪ የኢሳት አምስተኛ ዓመት ክብረ በዓል ዕለት እርሱም ልክ እንደፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ ከንግዲህ ህዝብ ሰብስቤ አዋጡ አልልም ፡፡ በጋራ ሽክሙን ብንካፈል ወደ ነጻነት ያደርሰናል ፡፡ አናዋጣም ግን የሚሉ ካሉ አይስጉ ! የቆረጡ ሃብታቸውን አሟጠው እስከመጨረሻው የሚረዱ ቆራጥ ዜጎች አሉ ሲል እድምተኛው ረጅም ደቂቃ በቆየ ጭብጨባ ነበር ድጋፉን ያሳየው ፡፡

ታማኝ በተገኘበት ሥፍራ የሚነቅፉትን የሃሳብ ድኩማኖች አንስቶ ሲተች አልተሰማም ፡፡ ይልቅስ ወደላኳቸው አለቆቻቸው ነው በተጨባጭና በማስረጃ ያሰማሯቸው ከለቀቁት ፊልም ተነስቶ ባገናዛቢ መልኩ ራሳቸውን ሲሞግታቸው የሚስተዋለው ፡፡ እንደመሰለኝ ታማኝ መለመን ደክሞታል ፡፡ ኢሳት የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆኖ እንዲቀጥል እዳው መሆን ያለበት ወደ ነጻነት ናፋቂው ህዝብ ትከሻ ባስተማማኝ መልኩ እንዲሸጋገር ነው ፡፡ከዚህ በተረፈ ወዳጃችን ታማኝ የሚፈራው ታላቁ እስክንድር እንዳለው ፣ በአንበሳ ፊት አውራሪነት የመጣን የበግ መንጋን ሠራዊት እንጂ፣ በጠቦት በግ ፊት አውራሪነት የመጣን የአንበሳን ሠራዊት አይደለም የሚፈራው፡፡

I am not afraid of an army of lions led by a sheep; I am afraid of an army of sheep led by a lion.

Tuesday, 3 November 2015

ለጥቅምት 22 ሰማዕታት የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ምርጫ 1997 ዓ.ምን ተከትሎ ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለሾ ዜናዊ ቀጥታ ትዕዛዝ በ‹‹á€áŒĽá‰ł ሀይሎች›› በጭቃኔ ለተገደሉት ሰማዕታት እና ለቆሰሉት ኢትዮጵያውያን በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት መታሰቢያ ተደረገ፡፡ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የገጠማቸውን በተለይም ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ ያዩትንና የራሳቸውን ገጠመኝም አካፍለዋል፡፡

የፕሮግራሙ ተሳታፊዎቹ የተገደሉትን በክብር መቅበር እንዳልቻሉ እና ታፍሰው በተለያዩ እስር ቤቶች መታሰራቸውን አስታውሰዋል፡፡ አዛውንቶችንና ህፃናትን በጭካኔ ተገድለው ባንክ ሊዘርፉ ነው የተባለበትና የሥርዓቱን የህግና ሞራል የማይገድበው መሆኑን ያሳየበት ነውም ብለዋል፡፡ ሥርዓቱ ካለፈው ስህተቱ ሳይማር ዛሬም ለመግደል ዝግጁ እንደሆነ መቀጠሉንም ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሥርዓቱ ወደ ባሰ አምባገነንነት በመግባቱም ትግሉን መቀላቀላቸውን ገልፀው፣ ዘላቂው አማራጭ የሰማዕታቱን የትግል መንፈስ ፅናት ይዞ መታገል ነው ብለዋል፡፡ እነሱ አላማ ያደረጉትን ተጉዘው በአንድነት የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚገባቸውም ገልፀዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በ1997 ዓ.ም በኋላ የሥርዓቱ ሁኔታ እየተባባሰ እንደመጣና ለዚህም ዋናው ምክንያት ኢትዮጵያውያን ሥርዓቱ የሚያደርስብንን በደል ችለን ወደ ውስጥ የምናለቅስ መሆናችን ነው ብለዋል፡፡ ሥርዓቱ ይቅር የማይደረግለት ሆኖ፣ ፖለቲካው በመነታረክ መቀጠሉን ትክክል እንዳልሆነም ገልፀዋል፡፡

‹‹áˆĽáˆ­á‹“ቹ ታሪክና የጋራ ነገር የላችሁም ብሎናል፡፡ መናናቅንና ሀይማኖትን ማቃለልን በተግባር አሳይቶናል፡፡ የወደፊት ኢትዮጵያ በእኛ እጅ እንድትሆን ከፈለግን የነበረውን የሀገራችን እሴት ማናናቅ የለብንም፡፡›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል ኢትዮጵያውያን የገነቧቸው እሴቶች ሁሉ በወጣቱ ልብ ውስጥ ማደር እንዳለባቸው፣ ሰማዕታቱ የሞቱለት አላማና ኢትዮጵያውያን የገነቡት እሴት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

Sunday, 1 November 2015

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ነጻነትን ክፉኛ ከሚገድቡ አገራት አንዷ ናት ተባለ

    
በኢንተርኔት ነጻነት ከ12 የአፍሪካ አገራት የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች ቻይና የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ 1ኛ ናት 

የኢንተርኔት ነጻነት በአለማቀፍ ደረጃ ለአምስት ተከታታይ አመታት እያሽቆለቆለ እንደሚገኝና ኢትዮጵያም የኢንተርኔት ነጻነት ከሌለባቸው የአለማችን አገራት አንዷ መሆኗን “ፍሪደም ሃውስ” የተባለው አለማቀፍ ተቋም ሰሞኑን ባወጣው አመታዊ ሪፖርት አስታወቀ፡፡ተቋሙ በ65 የአለማችን አገራት ላይ ያካሄደው የ2015 የኢንተርኔት ነጻነት ጥናት ሪፖርት፣ ከአለማችን አገራት የከፋ የኢንተርኔት ነጻነት የተንሰራፋባት ቻይና መሆኗን ጠቁሞ፣ ጥናቱ ካካተታቸው 12 የአፍሪካ አገራት መካከልም ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ነጻነት የመጨረሻውን ደረጃ ትይዛለች ብሏል፡፡

2.9 በመቶ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽፋን ባለባት ኢትዮጵያ፣ የማህበራዊ ድረ ገጾችና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አፕሊኬሽኖች እንዲሁም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች ይታገዳሉ፣ ጦማርያንና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ተጠቃሚዎችም ይታሰራሉ፣ ፕሬሱም ነጻ አይደለም ብሏል፡፡

በአገሪቱ የኢንተርኔት አቅርቦትና ተደራሽነት ችግሮች እንዳሉ የጠቆመው ሪፖርቱ፣ የአገልግሎት መቆራረጥና አዝጋሚነት በስፋት እንደሚያጋጥምና በአይሲቲው ዘርፍ ለሚሰማሩ ገለልተኛ ተቋማትና ሾል ፈጣሪዎች የሚሰጠው ዕድልም እጅግ ውስን ነው ብሏል፡፡የ2007 አገራዊ ምርጫ መቃረቡን ተከትሎ በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ዜናዎች እንዳይሰራጩ ታግደዋል፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድረገጾችም አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርገዋል ያለው ሪፖርቱ፤ ከ100 በላይ ድረገጾችም አሁንም ድረስ ታግደዋል፤ መንግስት በኢንተርኔትና በሞባይል በሚደረጉ ግንኙነቶች ላይ የሚያደርገውን ክትትልና ስለላ አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል፡፡

መንግሥት በበኩሉ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚሰነዘሩ ተመሳሳይ ትችቶችን ማስተባበሉ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በቅርቡ እንደገለፀው፤ የኢንተርኔት ስርጭትና አጠቃቀምን ለመቆጣጠር የሚያስችል ህግ ይፀድቃል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚ ከሆኑት የአለማችን አምስት አገራት አንዷ ናት ያለው ሪፖርቱ፣ ከ2014 እስከ 2015 ባለው ጊዜም፣ መንግስት ሃሳባቸውን በገለጹ ጦማርያንና በድረገጽ ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰውን እንግልትና እስራት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ገልጿል፡፡የ2015 የኢንተርኔት ነጻነት ሪፖርት እንደሚለው፤ ጥናት ከተደረገባቸው 65 የአለማችን አገራት መካከል ነጻ የተባሉት 18 ሲሆኑ፣ 28 አገራት የተወሰነ የኢንተርኔት ነጻነት እንዳለባቸው፣ 19 አገራት ደግሞ  የኢንተርኔት ነጻነት እንደሌለባቸው ተረጋግጧል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የለሊቱ የቪኦኤ ሚስጥራዊ ጉባኤ

በአበበ ገላው (ትርጉም በታኬ)

በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እና አምባሳደር ግርማ ብሩ በዩናይትድ ሰቴትስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ በሌሊት በድብቅ በመግባት ሕጋዊ ስልጣኑ ሳይኖራቸው ስለስርጭቱ ለጥቂት የድርጅቱ ሠራተኞች የኢዲቶሪያል መመሪያ ከሰጡ በኋላ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት (ቪኦኤ) እና በህወሀት የበላይነት በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት ያልተጠበቀ አቅጣጫ ይዟል፡፡ ስብሰባው በሚስጥር በተካሄደበት ጊዜ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች ለሬዲዮ ስርጭቱ ሰራተኞች ስለዜና አዘጋገብ፣ እንደዚሁም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚተላለፈው የስርጭት ጥራት ሁኔታ መመሪያ የመስጠት ሙከራ ያደረጉ ለመሆናቸው ከታመኑ ምንጮች በተገኙ መረጃዎች ተረጋግጧል፡፡

Tedros Adhanom and Ambassador Girma Birru

ከቪኦኤ ባለስልጣኖች ዕውቅና ውጭ በሚስጥር እንዲከናወን የተደረገው ይህ ስብሰባ የተካሄደው በዋሽንግተን ዲ.ሲ 330 ኢንዲፔንደንስ አቬኑ በሚገኘው በቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል የኢዲቶሪያል የስብሰባ ቢሮ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ድብቅ ስብሰባ እንዲካሄድ የተደረገው ባልተለመደ እና እንግዳ በሆነ መልኩ በሰንበት፣ እ.ኤ.አ መስከረም 26 ቅዳሜ ዕለት ከስራ ሰዓት ውጭ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ ነበር፡፡

የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ፕሮግራም ስርጭት ባልደረባ በሆነው በሰለሞን አባተ ግንባር ቀደም አደራጅ እና አስተባባሪነት እንዲሁም በአሜሪካ ድምጽ የትግርኛው ፕሮግራም ስርጭት ባልደረባ በሆነው በበትረ ስልጣን ተባባሪነት በዲፕሎማቶቹን እና ሁለት ቴክኒሸኖችን ጨምሮ ሰባት የቪኦኤ የስራ ባልደረቦችን ባካተተው ቡድን መካከል የተካሄደው ስብሰባ ተገቢነት የሌለው እና አግባብ ያልሆነ ተብሎ ተፈርጇል፡፡

አገዛዙ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡትን ብዙሀን መገናኛዎች ጸጥ ለማድረግ እና የስርጭት አድማሳቸውን ለመገደብ እያራመደ ካለው አውን ያወጣ ስልት አንጻር ከፍተኛ በሆኑ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች እንደዚህ ያለ ስብሰባ መካሄዱ እና ስለቪኦኤ እያራገቡት ያለው የጥላቻ አጀንዳ በሕጋዊ መልኩ ስልጣን የተሰጠውን የመተዳደሪያ ደንብ እና የጋዜጠኝነት ስነምግባርን የሚጥስ ዕኩይ ድርጊት እንደሆነ ተደርጎ ይታሰባል፡፡

ይህ በቅሌት የታጀበ ስብሰባ እንዲካሄድ የተፈለገበት ዋናው ምክንያት አገዛዙን በየዓመቱ የፕሬስ ነጻነትን በመደፍጠጥ የቀዳሚነቱን ቦታ ከሚይዙት የፕሬስ ደፍጣጮች መካከል እያስመደበው የመጣ ስለሆነ ይህንን ሁነት ለማደብዘዝ ሲባል በጋዜጠኞች እና በጨቋኙ መንግስት መካከል መተማመን እና ትብብር እንዲኖር ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ ክስተት ነው፡፡ በስብሰባው ወቅት በተደረገው ንግግር የህወሀት ተወካይ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የሬዲዮ ስርጭት ጥያቄ በማቅረብ እና በድብቅ የማስፈራሪያ ድርጊቶችን በመፈጸም በስርጭቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ መፍጠር እና የስርጭቱንም ይዘት ማስቀየር እንደሚቻል የቀረበውን ሀሳብ ለደህንነታቸው ሲባል አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው ይፋ አድርገዋል፡፡

እየተካሄደ የነበረው ስብሰባ ውይይት በመቅረጸ ድምጽ እንዳይቀዳ እግድ የጣለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማያያዝም ቪኦኤ ጠንካራ የሆኑ ትችቶችን ለሚያቀርቡት የአየር ጊዜ በመስጠት እና ዓላማቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱትን አመጸኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ መንግስትን ለመገልበጥ ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋሉ በማለት ቅሬታውን አሰምቷል፡፡ ሚኒስትሩ በመቀጠልም ቪኦኤ “አሉታዊ ትረካ” ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰራ ሜዲያ ነው በማለት ቅሬታውን ገልጿል፡፡

የአምባገነን ምልከታ፣
ጥቂት ጥያቄዎችን ከወሰደ በኋላ ሚኒስትሩ ባለፈው ሐምሌ ወር ለቪኦኤ የሰጠው ቃለመጠይቅ የመንግስትን ፖሊሲ በሚተቹ ትችት አቅራቢዎች በቪኦኤ በኩል ትችት የቀረበ በመሆኑ ቅሬታ የተሰማው መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፡ እንደዚህ ያሉ ተሞክሮዎች ስህተት ናቸው፣ እናም መደረግ አልነበረባቸውም በማለት ለተሰብሳቢዎቹ ተናግሯል፡፡

አወዛጋቢ በነበረው የቪኦኤ ቃለመጠይቅ የህወሀት ሚኒስትር ካለው እውነታ በተጻረረ መልኩ ፕሬዚዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ የመጨረሻው ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ስለሆነ አጽድቆታል በማለት የተዛባ መረጃ አሰራጭቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት የመን ላይ የታፈነው እና በኢትዮጵያ ውስጥ ስቃይ እየተፈጸመበት ያለው ታዋቂው አመጸኛ አንዳርጋቸው ጽጌ መልካም የሆነ አያያዝ እየተደረገለት እንደሆነ እና እንዲያውም የልማት ፕሮጀክቶችን በማድነቅ ላይ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ አንዳርጋቸው መጽሐፍ እንዲጽፍ ላፕቶፕ የተሰጠው መሆኑን ተናግሯል፡፡

ሚኒስትሩ እና አምባሳደሩ ሁለቱም መንግስት ከቪኦኤ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት እና ጋዜጠኞች አዎንታዊ ትረካ እና ስዕሎችን አጉልተው ማውጣት እንዳለባቸው እና አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያደርግላቸው ግልጽ ያደረጉ መሆናቸውን ምንጮቹ ይፋ አድርገዋል፡፡

ባለስልጣኖቹ ሰባት የቪኦኤ የስራ ባልደረቦች ያሉበትን ስብሰባ እየመሩ ባሉበት ጊዜ ሲሰጡት በነበረው መመሪያ ቪኦኤ ወደ ኢትዮጵያ በሚያስተላልፈው የሬዲዮ ስርጭት ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ መዘገብ ያለበት ከአሉታዊ ትረካዎች እና አስተያየቶች፣ እንዲሁም አንገብጋቢ ከሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀም እና ከሙስና ይልቅ አዎንታዊ እና የልማት ስራዎችን መዘገብ እንደሚያስፈልግ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚህ ብቻ ሳያቆም ንግግሩን ቀጥሎ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተገኙ ያላቸውን ጥቂት ዕድገት እና መሻሻሎች ከዘረዘረ በኋላ ጋዜጠኞቹ እራሳቸው እውነታውን በግንባር ወደ ሀገር ቤት በመሄድ ማየት እንዳለባቸው የግብዣ ጥሪ አስተላልፎላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ስለቪኦኤ ውስጣዊ የስራ እንቅስቃሴ ቀጣይነት ባለው መልኩ መረጃ እንደሚቀበል ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ይፋ አድርገዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞቹ በየስራ ክፍሎቻቸው ማን ምን እንደሚሰራ እያንዳንዱን ነገር እንደሚያውቁ እና እነዚህ ጋዜጠኞችም ከዚህ አንጻር እራሳቸውን እንደገና በጥንቃቄ መመርመር እንዳለባቸው በይፋ የተናገረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

አንድ ስሙ እንዳይታወቅ የፈለገ የስብሰባው ተሳታፊ የሆነ የቪኦኤ የስራ ባልደረባ እንዲህ በማለት ሀሳቡን ገልጿል፣ “በእንደዚህ ዓይነት ስራዎች ላይ ልንከተላቸው የሚገቡ ሕጎች፣ የአሰራር ሂደቶች እና የሙያ ስነምግባሮች አሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምሽት ከመሆኑ አንጻር ሰራተኛው ሁሉ ለመኝታ ወደየቤቱ በሄደበት ሁኔታ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድርጅቱ ኢዲቶሪያል ክፍል ውስጥ በመገኘት ጥቂት የድርጅቱ ሰራተኞችን በመያዝ እንደዚህ ያለ ስብሰባ ማካሄድ በድርጅቱ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ የማያውቅ አዲስ እና ያልተለመደ ነገር ነው“ በማለት ሀሳቡን ግልጽ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ምንጩ ከዚህ ጋር በማያያዝ እንደገለጸው የአሰራር የዕዝ ሰንሰለቶችን በመጣስ የቪኦኤን ነጻነት በገደበ መልኩ እየተካሄደ ባለው በዚህ ስብሰባ ላይ እኔ እና መሰል ባልደረቦቼ በእጅጉ አዝነናል የሚል መልዕክት እንዳስተላለፈ ምንጮች ዘግበዋል፡፡

የስብሰባ ምንጮች እንዲህ የሚል ግልጽ የሆነ መልዕክት የተላለፈ መሆኑን ጠቁመዋል፣ “ስለቪኦኤ የአዘጋገብ ፕሮግራም እና ስለሌሎች ማናቸውም ጉዳዮች ለመወያየት እና ቅሬታን ለማቅረብ ሲፈለግ ባለስልጣኖች የኢዲቶሪያል ስብሰባ ለማድረግ የዩኤስ ፌዴራል መንግስት ሰራተኛ የሆኑትን የተመረጡ ጥቂት የቪኦኤ ጋዜጠኞች ቡድንን በምሽት ስብሰባ ከመጥራት ይልቅ የተለመደውን የአሰራር ስርዓት እና የዕዝ ሰንሰለት መከተል ነበረባቸው“ ብሏል፡፡

ሌላው ምንጭ በመቀጠል ከተሰብሳቢዎች የቀረበውን እንዲህ የሚለውን አስተያየት ይፋ አድርጓል፣ “እኛ ለቪኦኤ የምንሰራ ነጻ ጋዜጠኞች ነን፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወይም አምባሳደሩ ወደ ቪኦኤ ዘልቀው በመምጣት ስራዎቻችንን እንዴት መስራት እንዳለብን የሚያስገድዱን ወይም ደግሞ መመሪያዎችን የሚሰጡን ለምንድን ነው? ይህ ዓይነት አካሄድ አግባብነት የሌለው የሙያ ጣልቃገብነት ጉዳይ ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን ይህ ጉዳይ በእኛ የማሰብ ችሎታ እና ሙያዊ ብቃት ላይ የተሰነዘረ ግልጽ ዘለፋ ነው“ ብሏል፡፡ ይኸው ምንጭ፣ “ቪኦኤ ያለምንም ፍርሀት እና ከምንም ዓይነት አድልኦ በጸዳ መልኩ የመስራት ተግባሩን መቀጠል እንዳለበት ጠንካራ እምነት አለኝ“ ብሏል፡፡

ቪኦኤ እንደ ነጻ የሜዲያ ተቋም በትክክለኛ እና በእውነት ላይ የተመሰረተ ዘገባን የማቅረብ ተልዕኮን የሚያራምድ ጠንካራ የሆነ ኃላፊነትን የተሸከመ ድርጅት እንደሆነ አጽንኦ በመስጠት ግልጽ አድርገዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ “ሕግን መሰረት አድርጎ የተቋቋመውን እና ሕጋዊ ስልጣን ያለውን የቪኦኤን የመተዳደሪያ ደንብ እና የሙያ ስነምግባር ማንም ድርድር ሊያደርግበት እና ሊለውጠው አይችልም“ ብለዋል፡፡ ይኸ ቅንነት የጎደለው ስብሰባ “አምባገነኑ እየተመለከታችሁ ነው“ የሚል ቀጥተኛ ያልሆነ እንደምታ ይኖረዋል በማለት ሌላው ምንጭ ጠቁሟል፡፡ ለሾል በጣም ምቹ የሆነ እና ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ በዚህ የፌዴራል መንግስት ህንጻ ውስጥ እንደዚህ ያለ ክስተት እንዴት እና ለምን እንደተፈጠረ ጥቂት ሰዎች በጣም ያሳሰባቸው ስለሆነ ድርጊቱ ለምን እንደተፈጸመ ሊያጣራ የሚችል አጣሪ አካል መቋቋም እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ባለስልጣኖቹ ለቪኦኤ የስራ ባልደረቦች የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሮች በሰፊው ተከፍተው የቆዩ መሆናቸውን ነግረዋቸዋል፡፡ ሆኖም ግን የተወሰኑ የስብሰባው ተሳታፊዎች ባለስልጣኖቹ የመጡት በስቱዲዮ በመገኘት ቃለመጠይቅ እንዲሰጡ ነው ተብሎ የተሳሳተ መረጃ በመሰራጨቱ እና እዚህ ከገባን በኋላ እየተደረገ ያለው የኢዲቶሪያል ሕገወጥ ስብሰባ መሆኑን በመመልከቴ ወደ ስሰብሰባው ከፍል በመግባቴ ጸጸት ተሰምቶኛል በማለት ተናግሯል፡፡

የኢትዮ-አሜሪካ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት አበበ ኃይሉ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ የተሰማቸውን ሀዘን እና እምነት ማጣት እንዲህ በማለት ግልጽ አድርገዋል፣ “በአሁኑ ጊዜ በቪኦኤ ላይ እየተደረገ ያለው ድርጊት የቪኦኤን ታማዕኒነት የሚያጠፋ ስለሆነ ድርጊቱ በድርጅቱ ህልውና ላይ ያነጣጠረ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው፡፡ እንደ ኢትዮ-አሜሪካውያን ዜጎች ለዚህች ታሪካዊ ለሆነች ሀገር ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪከ ግብር ከፋይ ሕዝቦችም ነን“ ብለው ነበር፡፡

አቶ አበበ አስተያየታቸውን በመቀጠል ቪኦኤ እና የቪኦኤ የስራ ባልደረቦች በሌላ በውጭ ኃይል ጣልቃገብነት የመጦዝ እና የመታዘዝ ዕድል እንዳይገጥማቸው የሜዴያን ነጻነት ለማስከበር ወጥተን መጠየቅ እንዳለበን ምክንያት የሚፈጥር ጉዳይ ሆኗል፡፡ በመጨረሻም ይኸ ድርጊት በጠቅላይ የምርመራ ጽ/ቤት/Inspector General መመርመር እንዳለበት ጠንካራ እምነነት አለኝ በማለት ጥቆማ አቅርበዋል፡፡

የውጥረት ታሪክ፣
በኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው አገዛዝ ከሕግ አግባብ ውጭ ግድያ በመፈጸም፣ በዜጎች ላይ ስቃይ በማድረስ፣ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ በመጠቀም፣ በሙስና በመዘፈቅ፣ ሕዝብን በጅምላ በማፈናቀል፣ በመሬት ቅርምት ወረራ በመረባረብ፣ በዜጎች ላይ አድልኦ በመፈጸም እና በሌሎች ዓይነት ጅምላ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና በሰዎች ልጆች ላይ በሚፈጽማቸው ሰብአዊ ወንጀሎች በሰፊው ይተቻል፡፡

እ.ኤ.አ በ2005 የተከሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተፈጥሮ የነበረውን ውዝግብ ተከትሎ አገዛዙ በጉዳዩ ላይ የዩኤስ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ክሱ ውድቅ እስከሚደረግ ድረስ በአራት የቪኦኤ ነባር ጋዜጠኞች ከሌሎች በርካታ ተወንጃዮች ጋር በመጨመር የሀገር ክህደት እና የዘር ማጥፋት መፈጸም የሚል የውንጀላ ክስ ተመስረቶባቸው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 የቪኦኤን እና የሌሎች ዓለም አቀፍ የዩኤስ ዜና ማሰራጫዎችን የሚገመግም ሶስት አባላትን ያካተተ የሬዲዮ ስርጭቱ የቦርድ አመራሮች/Broadcasting Board Governors (BBG) ቡድን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ሄዶ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በስልጣን ላይ የነበረው አገዛዝ በቬኦኤ የስርጭት አድማስ እንዳያገኙ እና ቃለመጠይቅም እንዳይደረግላቸው የሚፈለጓቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር እና ሌሎች አመጽ ያካሂዳሉ ብለው የፈረጇውን ድርጅቶች ዝርዝር ያካተተ ረዥም ቅሬታ አቅርበው ነበር፡፡
የቀድሞው የአፍሪካ ቀንድ የቪኦኤ ዋና ኃላፊ የነበሩት ዴቪድ አርኖልድ አገዛዙ ትችት ለሚያቀርቡት እና አመጽን ለሚያራምዱት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ቪኦኤ መድረክ እንዳይሰጣቸው ይፈልጋል በማለት ግልጽ አድርገው ነበር፡፡ ሆኖም ግን አርኖልድ ሀሳባቸውን ግልጽ ካደረጉ በኋላ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከስራቸው እንዲታገዱ ተደርገዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለሾ ዜናዊ ቪኦኤን ሀገሪቱን ካወደመው እና የዘር ማጥፋት ሰይጣናዊ የቅስቀሳ ድርጊት በማድረግ በመጥፎነቱ ከሚታወቀው ከሩዋንዳው ሬዲዮ ሚሌ ኮሊንስ ጋር አንድ ዓይነት ነው በማለት ድምዳሜ ሰጥቷል፡፡
ይህንንም በማስመልከት በኢትዮጵያ የሚሰራጨውን የቪኦኤን የስርጭት ሞገድ ካፈነ/ጃም ካደረገ በኋላ አምባገነኑ መለሾ እንዲህ የሚል ዲስኩር አሰምቶ ነበር፣ “በብዙ መንገድ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የመጫረሻ ዝቅተኛ የሆነውን የጋዜጠኝነት ስነምግባርን የማያሟላ እና የሁከት ፕሮፓጋንዳ የሚነዛ የሩዋንዳውን የሬዲዮ ኮሊንስን ተሞክሮ እንዳለ የሚተገብር ሜዲያ እንደሆነ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ እምነት አድርቦብናል“ ብሎ ነበር፡፡

ይኸው የውንጀላ ክስ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ “መሰረተ ቢስ እና ቆጥቋጭ” በሚል ውድቅ ተደርጎበታል፡፡ የአሜሪካ የመንግስት መምሪያ ለቀረበው የውንጀላ ክስ ምላሽ እንዲሆን በማሰብ ይልቁንም መንግስት የሰው ልጆች መሰረታዊ መብት የሆነውን ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንዲያከብር ጠይቋል፡፡

የሙያ ስነምግባር መርሆዎች፣
የቪኦኤ የሙያ የስነምግባር መርሆ በግልጽ እንደሚያስቀምጠው የቪኦኤ ቋሚ ወይም ደግሞ የኮንትራት ሰራተኞች በተለዬ ምክንያት በልዩ ትዕዛዝ በተላለፈ የስልጣን ተዋረድ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ መንግስት ወይም ደግሞ የሜዲያ ተቋም ሊያገለግሉ አይችሉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጨቋኝ አገዛዝ መዳፍ ሾር ወድቀው ለሚሰቃዩ ህዝብች ትክክለኛ መረጃ እና ዜና በማቅረብ ረገድ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ የቪኦኤ የጋዜጠኝነት የስነምግባር መርሆ እንዲህ በሚለው ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፣ “ቪኦኤ በነጻነት እና በዴሞክራሲ ላይ ሙሉ እምነት እና ተስፋ ላላቸው ህዝቦች ብሄራዊ ጥቅምን ለመጠበቅ እና ለዓለም ህዝብ በተለይም ደግሞ ትክክለኛ መረጃ ለማያገኙት ህዝቦች ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና የተሟላ መረጃ እንዲያገኙ ያደርጋል“ ይላል፡፡

ባለፈው ዓመት በህወሀት የበላይነት የሚመራው አገዛዝ የተሟሉ የሳቴላይት መሳሪያዎችን በመጠቀም እና ዓለም ሕጎችን በማክበር ትክክለኛ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን በመከተል እና በስራ ላይ በማዋ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መረጃዎችን እና ዜናዎችን የሚያሰራጩትን ዓለም አቀፍ ሜዲያዎች ስርጭትን ቪኦኤን ጨምሮ በማፈኑ/ጃም በማድረጉ ቢቢጂ/BBG ከቢቢሲ/BBC፣ ዶቼ ዎሌ/Deutsche Welle እና ከፍራንስ 24/France 24 ጋር በጋራ በመሆን አገዛዙ ሰብአዊ መብቶችን በሰፊው እየደፈጠጠ ነው በማለት አውግዘውታል፡፡

እነዚህ ዓለም አቀፍ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዲህ የሚል ተካትቶ ይገኛል፣ “ይህ ጣልቃገብነት ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ሞገድ የስርጭትን አጠቃቀም እና የሳቴላይት ስርዓቱ የሚመሩባቸውን ደንቦች በተጻረረ መልኩ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 19ን በመተላለፍ ግለሰቦች ነጻ የሜዲያ ሽፋን መረጃዎችን እንዳያገኙ እገዳ ጥሏል ወይም ጃም አድርጓል“ የሚል የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

የቢቢሲ አገልግሎት ቡድን ተጠባባቂ ዳይሬክተር የሆኑት ሊሊያን ላንዶር የአገዛዙን አፋኝነት በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የዓለም አቀፉን የዜና ማሰራጭ አውታሮች አውከዋል፡፡“

የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ፣
ለጠንካራ ትችቶች እና ለሜዲያ ሽፋን ጠላት በመሆን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ፕሮግራምን ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በእራሱ ስልጣን ስርጭቱን ለማቋረጥ እና ለመዝጋት ያለ የሌለ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህንን ያህል ጥረት በኢትዮጵያ የቪኦኤን አጭር ሞገድ እና የሳቴላይት ስርጭት ለማፈን/ጃም ለማድረግ እንዲሁም የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖዎችን ሲያደርግ የቆዬ ቢሆንም ቅሉ ዓላማ አድርጎ የተነሳበትን ግብ ሳይመታ እና የታለመውን ውጤት ሳይስገኝ የውኃ ላይ ኩበት ሆኖበት ቀርቷል፡፡

እ.ኤ.አ በ2015 ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ተከላካይ ድርጅት/CPJ የጽሁፍ እና የሕትመት ምርመራ የሚደረግባቸውን 10 ዋና ዋና ጨቋኝ መንግስታት የደረጅ ዝርዝር ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ከሳውዲ አረቢያ በመቀጠል በ4ኛነት ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ የCPJ የምርመራ ውጤት ዘገባ እንደሚያመለክተው “ከፍተኛ የሆነ የህትመት እና የሜዲያ ምርመራ ከሚያደርጉ ሀገሮች መካከል ኢትዮጵያ በ4ኛነት ደረጃ ላይ የምትገኝ በመሆኗ ምክንያት የጋዜጠኞች እስራት በገፍ የሚከናወን በመሆኑ በርካታ ጋዜጠኞች ሀገራቸውን እየተው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ እ.ኤአ. በ2014 በጦማሪያን እና በነጻው ፕሬስ ህትመት አዘጋጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ የኃይል እርምጃ በመወሰዱ ምክንያት ከ30 በላይ የሚሆኑ ጋዜጦች ለስደት ተዳርገዋል፡፡“ CPJ ማንኛውንም ትችት ማቅረብ እና ሀሳብን በነጻ መግለጽ ወንጀለኛ የሚያደርገውን እ.ኤ.አ በ2009 የወጣውን የጸረ-ሽብር አዋጅ አውግዞታል፡፡

አገዛዙ ይህንኝ ያህል ጥረት እያደረገ የህወሀት የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎችን የማፈን እና በጋዜጠኞች እና በሰላማዊ አመጸኞች ላይ የሀሰት የውንጀላ ክሶችን ቢመሰርትም ያሰበው እና የሚያደርገው ሁሉ የእምቧይ ካብ እየሆነ ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁን በቅርቡ ደግሞ የእስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ በቀጥታ ከቪኦኤ ጋዜጠኞች እና ከሌሎች ነጻ የሜዲያ ተቋማት ጋር በግንባር በመገናኘት እያደረገ ያለው ንግግር አገዛዙ ከውስጥ የግንኙነት መረብ አድማሱን እያሰፋ እና እያጠናከረ እንዲሁም ካሮት እና ዱላ እያሳየ እያስፈራራ ያለው ዕኩይ ድርጊት ያለምንም ጥርጥር በአፍሪካ ቀንድ የቪኦኤ ክፍል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ ከዚህም በላይ ከጋዜጠኝነት ስነምግባራቸው በተዛነፈ መልኩ ካሮት እየተሰጣቸው ለርካሽ ጥቅም በማጎብደድ መሳሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ግምት አለ፡፡

ቪኦኤ በሚስጥር ስለተካሄደው ስብሰባ ምንነት እና በኢትዮጵያ የቪኦኤ የሬዲዮ ስርጭት ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተጽዕኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት በስብሰባው ክፍልም የተደረገውን ውይይት በማስመልከት በዚህ ዘገባ አጠናቃሪ ለቀረቡለት ጥያቄዎች እስከ አሁን ድረስ ምላሽ አልሰጠም፡፡