Tuesday 13 October 2015

ሐብታሙ አያሌው በኩላሊት ጠጠር መታመሙ ተገለጸ * እነ አብርሃ ደስታ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ


በእስር ቤት የሚገኘው ታዋቂው ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ በድንገተኛ ህመም ዘውዲቱ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር ተዘገበ:: በአዲስ አበባ የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳሉት ሃብታሙ ከ እስር ቤት ወደ ዘወዲቱ ሆስፒታል የተወሰደበት ምክንያት በሁለቱም ጎኖቹ ላይ የህመም ስሜት ስለተሰማው ነበር::

የዘውዲቱ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ምርመራ ካደረጉለት በኋላ ህመሙ የኩላሊት ጠጠር መሆኑን ለባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም መናገራቸውን እነዚሁ ምንጮች አብራርተዋል:: ሃብታሙ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተመለሰ ሲሆን በነገው ዕለትም ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል::

ከሃብታሙ አያሌው ጋር አብረው የተከሰሱትና በቅርቡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በነፃ የተለቀቁት አብርሃ ደስታ; ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋም በነገው ዕለት አቃቤ ሕግ ይግባኝ በጠየቀባቸው ክስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው የቃል ክርክር ያደርጋሉ ሲሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::


0 comments:

Post a Comment