Saturday 7 September 2013

ዜና ከአዳማ፤ የአዳማው ድራማ – ፍኖተ ነጻነት

በህገ መንግስቱ መሰረት ለአዳማ አስተዳደር አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግና መስተዳድሩ ይህንኑ በማወቅ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ በደብዳቤ ካሳወቀና መስተዳድሩም የሰልፉ ቀን ይቀየርልኝ በማለት ባቀረበው ምክንያት የተነሳ አንድነት ሰልፉን ለፊታችን እሁድ ማዞሩን አስታውቆ ቅስቀሳ ይጀምራል፡፡
ድራማ 1
በራሪ ወረቀቶች መበተን እንደተጀመሩ ፖሊስ አባላቶችን ጣብያ በመውሰድ መበተን አትችሉም አለ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አሳውቀናል፣ ይህ ወረቀት ለሰላማዊ ሰልፍ የተዘጋጀ በመሆኑ ልትከለክሉን አትችሉም ፡፡ የሚል ምላሽ ተሰጠው፡፡ለሰዓታት በጣብያ እንዲቆዮ የተደረጉ አባላት በጭቅጭቅ ከጣብያው እንዲወጡ ተደረጉ፡፡
ድራማ 2
ከአዲስ አበባ ለቅስቀሳ የወጣ መኪና ሞንታርቦ ተጭኖለት ወደ ስራ ሊሰማራ ሲል ፖሊስ መኪናውን በማስቆም መቀስቀስ አትችሉም አለ፡፡ ምክንያቱ የተፈቀደው ለሰልፍ እንጂ ለቅስቀሳ አይደለም የሚል ነው፡፡የአንድነት ልጆች ፖሊስ ቢፈልግ ማሰር እንደሚችል በመጥቀስ ከመቀስቀስ ወደ ኋላ እንደማይሉ አስረግጠው በመናገራቸው ጭንቅ ያለው ፖሊስ ‹‹ሂዱና የቱሪዝም ኮሚሽንን አነጋግሩ››ይላል፡፡
ዛሬ ማለዳ ወደ አዳማ ቱሪዝም ቢሮ የሄዱ አባላት አስገራሚ መልስ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ባለስልጣኑ ‹‹በመኪና መቀስቀስና ፖሰተር መለጠፍ ትችላላችሁ ነገር ግን በራሪ ወረቀት መበተን አትችሉም ምክንያቱም ወረቀቱ ኦህዴድን የሚሳደብ ነው››በማለት ፖሊስ ዙሪያ ጥምጥም ሲዞር የዋለበትን እቅጩን ተናግረዋል፡፡ኦህዴድን ትሳደባለች የተባለችው በኦሮምኛና በአማርኛ የተዘጋጀችው በራሪ ወረቀት በአሁኑ ሰዓት በአዳማ ነዋሪ እጅ እየገባች ነው፡፡1184928_597863573605729_818771416_n

0 comments:

Post a Comment