Saturday, 14 September 2013

“ሌኒን : ትሮተስኪ : ስታሊን” ከ “መለስ : አርከበ : አባይ”


Abraha Desta 




(ፅሑፉ የማን እንደሆነ አላወቅኩም። አንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ የላከልኝ ነው። የአፃፃፍ ጥበቡና ቁምነገሩ ስለማረከኝ እነሆ ለጠፍኩት፤ የአፃፃፍ ስልቱ ግን የተስፋዬ ገብረአብ ይመስላል። ለማንኛውም መልካም ንባብ)

የቦልሸቪኩ መሪ ሌኒን በጣም የሚታወቅበት በዲሞክራሲ ማእከላዊነትና በተለያዩ ሰዎች የሚታወቁ ንድፍ ሃሳቦችን በራሱ መንገድ በመናገሩና በማሳመኑ ነው:: በፖሊት ቢሮው ውስጥ እጅግ በጣም ልቅ የሆነ ክርክር ሲያደርጉ አብዛኛው ግዜ ወጥሮ የሚይዘውና እስከ መሸነፍም የሚደርሰው የአብዮቱ አጋር የሆነው ትሮተስኪ ነበር:: ትሮተስኪ ከሌኒን በላይ የማሳመን ችሎታ ያለው እንዲሁም ሲበዛ ዲሞክራት ነበር:: የሌኒን ፍስፍና ተንኮል የበዛበት ሲሆን አብዛኛው ግዜም የራሱ አዲስ ሃሳብ የቀድሞ የኢኮኖሚክስ ፈላስፋዎች ነው እያለ ለፖሊትቢሮው ያቀርብ ነበር ፤ ይህ ያደረገበት ምክንያትም የራሴ ሃሳብ ነው ካለ ቶሎ አይቀበሉኝም ያንቋሽሹብኛል በማለት ነበር:: ሌኒን የብሄር ችግርም ስለነበረው የሚያደርገው እንቅስቃሴ ስልጣኑን የሚያደላድልበት አዃኋን ነበር:: ሌኒን ያ ሁሉ የዓምስት ዓመት መርሃ ግብር አለኝ እያለ ሳይወድ ለዘልአለሙ አሸለበ:: ሌኒን በካድሬዎቹ አማካኝነት በሕዝቡ ዘንድ በጣም እንዲወደድና እንዲከበር አድርጓል:: በዚህ ምክንያትም የሶቭየት ሕብረት ህዝብ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር-------‘’Lenin is like a God who couldn’t do any wrong’’----- መለስም የሌኒን አስተሳሰብ እንዳለ በመገልበጥ ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት እንዲሁም የተለያዩ ሙሁራን የሚያማክሩትን ሃሳብ በመሰብሰብ የሯሱ አስመስሎ ገልብጦ መናገር ይችልበት ነበር:: እነዚህ ከተነሱ የማይመለሱት አርሶ አደሮች እንዳይነሱበት በሚመቻቸው ቋንቋ እየተናገረ እስኪአመልኩት “አንተ ህዝብ ካንተ መፈጠሬ እድለኛ ነኝ” እያለ ሆዷቸውን እስኪበላቸው አጫወታቸው:: መለስ ልክ ክርስቶስ ሃዋርያትን አስተምሩ ብሎ እንደበተኛቸው ካድሬዎቹን በህዝብ ዘንድ ሙገሳ እንዲያገኝ “መልስ በኪሱ ÷ የድሃ አባት ÷ ልብስና መፃሕፍት ብቻ ያለው” እያሉ ሰበኩለት:: እንደ ሌኒን ግን He is like a God አላሉትም:: መለስ በጣም የሚፈታተኑትን ፖለቲኮኞች ከድርጅቱ ካባረረ በኋላ ሊፈታትኑት የሚችሉት አባይ ፀሃዬና አርከበ ዑቑባይ ነበሩ:: አባይ ፀሃዬ ካለው የሶሻሊስም አሰተሳሰብ መለስ ከዘረጋው ካፒታሊዝም ጋር መግባባት ስላቃታው ነገሮች ሁሉ ፈርሰውበታል ፤ እንዃን መለስን ሊከራከር ከሯሱ ጋርም መታረቅ አቅቶታል:: ከኢህአደግ ተወዳጅና ከዘመኑ ጋር የሚሄደው አርከበ ነው:: አርከበ በደከመች የመለስ ዲሞክራሲ ማእከላዊነት ውስጥ በከፊሉ የሚከራከረው ብቸኛ ሰው ነበር:: አርከበ ለመለስ የሚከራከረው ለህዝበ ሲል እንጂ መለስን ሊፈታተን አልነበረም ፤ መለስ ግን እንደጠላቱ ያየው ጀመር እንደሌሎቹ እሱ ያለውን ዝም ብሎ ስላልተቀበለው:: እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ምስስሉ ሌኒንና ትሮተስኪ ፤ መለስና አረከበ:: ሌኒንና መለስ ከሞቱ በኋላ የድርጅቱና የህዝብ ድሕንነት ያሰጋቸው የፓርቲው አባላት “አሁን የምንፈተንበት ግዜ ነው” ፤ ህዝቡ ለኛ ያለው አመለካከት የወረደና የተሳሳተ እንዳይሆን ተግተን መስራት አለብን የሚሉ እንደ ትሮተስኪና አርከበ የፓርቲያቸውን ቤት ነቀነቁት:: በዚህ ሰዓት በጣም የማሳመን ችሎታቸው ደካማና በተፈጥሮ አምባገነናዊነት የታደለዱ የፓርቲው አባላቶች የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠሩ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎችን ቦታ እንዲያጡ ለማዳከም ቆርጦው ተነሱ:: እነዚሀ ሰዎች ስታሊንና አባይ ናቸው:: ስታሊንና አባይ ይዘውት የተነሱት ሓሳብ ራሳቸውን ወደላይ የሚሰቅል ሳይሆን “የሌኒንና የመለስ ራእይ” እያሉ ለየዋሆቹ የፓርቲውን አባላት ማታለል ተያያዙት:: እንደነ ትሮትስኪና አርከበ ያሉ ጠንካራ ፖለቲከኞች ደግሞ ሌኒንና መለስ የራሳቸውን ሰርተዋል እኛም ለህዝቡ የበለጠ ነገር እንድንሰራለት ራሳችንን እናዘጋጅ ፤ ወቅቱ በህዝበ የምንፈተንበት ሰዓት ነው የሚል አቋም ይዘው ከሞቱት ጋር አንሞትም ማለታቸውን ቀጠሉበት:: የነ ትሮተስኪና አርከበ ብስለታቸውንና እውቀታቸውን በደንብ ጠንቅቆው ያወቁት ስታሊንና አባይ ህዝብን በማደራጀት መጀመርያ እነዚህ ለህዝብ ብለው የሞቱት መሪዎቻችን ትተዋቸው የሄዱት ያልተፈፀሙ ስራዎች በነሱ ስም እንጨርስ:: ለህዝብ ብለው ለህዝብ የሞቱ ምናምን ምናምን እያሉ ሆድ የሚበላ የልመና ዓይነት ፕሮፖጋንዳ ወደ ህዝብ ዘረጉ:: የዋሁ ህዝብም “ምን ዓይነት ቃላቸውን የማያጥፉ ፉጥሮች ናቸው ፤ እንዲህ ነው እንጂ አመራር ለህዝበ ብለው ለተሰውትም እንዳልሞቱ ማሳየት” ይሏቸው ጀመር:: በዚህ ሰዓት ስታሊንና አባይ ቢሮ ውስጥ ሆነው ቁልቁል ወደ ህዝቡ እያዩ በግራ እጃቸው ሲጋራ እየሳቡ የሌኒንና የመለስ ሞት እያስደሰታቸው ሳቃቸውን ከሲጋራው ጋር እፍፍፍ ያደረጉታል:: ስታሊንና አባይ ይቺ መሸወጅያ “ራእይ” የምትል ቫይረስ ወደ ህዝቡ በደንብ መግባቷን ካረጋገጡ በኋላ ፊታቸውን ወደ ማእከላይ ኮሚቴ አደረጉና ዲሞክራሲ ማእከላዊነትን ማፍረስ ጀመሩ : ልክ መለስ በ1993 አንጃዎቹ ከወጡ በኋላ ማእከሉን እንዳጠፋው:: ስታለንና አባይ ምንም አጀንዳ ሳይዙ ጉባኤ ጠሩ:: አጀንዳቸው ራእይ ስትሆን ለዚህ “ራእይ” የሚተናኮል ወይም የሚፈታተን የድርጅቱ ጠላት ተብሎ እንዲፈረጅ ወሰኑ:: በዚህ መሰረት ስታሊንና አባይ “ራእይ” ፤ ትሮተስኪና አርከበ ከጓዶቻቸው ጋር ተመካክረው የራሳችው “አዲስ ራእይ” የሚል ይዘው ጉባኤው ውስጥ ተሰባሰቡ:: ጉባኤው ከተከፈተ በኋሏ ባለ አዲስ ራእዮቹ ስለ ጉባኤተኞቹ ካድሬዎች ምንም የሚያውቁት ነገር ስላልነበረ የተለመደው ብስለት የተሞላው ትነተና ጀመሩ:: ትሮተስኪና አርከበ የተሳሳቱት የካድሬዎቹ ጭንቅላት ከጉባኤው ከመጀመሩ በፊት ስታሊንና አባይ ፎርማት ያደረጓቸው መሆኑ ያለማወቃቸው ነበር:: ካሁን በፊት ለትሮተስኪና አርከበ ስያንጨበጭብላቸው የነበረው ካድሬ “እምቧእ” /ኣረ ተው/ በማለት ዲስኩርናቸውን ተቀባይነት እንደሌለው ገለፁላቸው :: እንዲህ በጉባኤው ከተበሳበሱ በኋላ በቀጣዮቹ ስብሰባዎች ላይም ትሮተስኪ በጤና አርከበ በዕድሜ ሰበብ ከፓርቲው እንደሚሰናበቱ ተነገረ:: ትሮተስኪና አርከበ ድንጋጤ ሳይታይባቸው ጉባኤውን አጠናቅቀው ወጡ:: ዲሞክራሲ ማእከላዊንት ከፈረሰ በኋላ እንዲሁም ትሮተስኪና አርከበና ከድርጅቱ ከተሰናበቱ በኋላ ስታሊንና አባይ ራእዩን ትተው የራሳቸውን ስልጣንና መንገዳቸውን ማሳመር ተያያዙት:: ስታሊን ተረጋግቼ መስራት አልቻልኩምና አገር ለቀህ ሂድልኝ አለው ትሮተስኪን:: ከድርጅቱ መሰናበቱ ያልተሰማው ትሮተስኪ ሀገር ለቀህ ውጣ ሲባል በጣም ጨንቆት ትንሽ ካንገራገረ በኋላ የቀድሞዋን ሶቭየት ሕብረት ለቆ ወጣ:: ስታሊንም የቀሩትን ትናንሽ ትሮተስኪዎች እየጠራረገ ከትሮተስኪዎች ነፃ በመሆን ተረጋግቶ ስራውን ጀመረ:: ትሮተስኪ ግን ውጭ አገር ሄዶም ስታሊንን ሊያሰራው ስላልቻለ ስታሊን ሰላዮች በመላክ ትሮተስኪን በ1947ዓ/ም/ፈ በሀገረ ሜክሲኮ አስገደለው:: ስታሊን ያለ ትሮተስኪ 25 ዓመት ማንም ሳየተናኮለው ሩስያዎችን ቀጠቀጣቸው:: ልክ እንደ ትሮተስኪ አርከበ ለሕወሃቶች/ለአባይ ሊያሰራቸው ስላልቻለ በራስሕ ፈቃድ ከአገር ለቀሕ ውጣ አሉት ፤ ከዛ ለትምህርት ዶክትሬት ሊሰራ ሄዷል እንልልሃለን አሉት:: አባይ ከስታሊን የተማረው አርከበን በስምምነት ከአገር እንዲወጣ ስላደረገው ነው:: አርከባ ወደ እንግሊዝ አገር ለትምህርት ሄዷል እያሉት ነው ፤ እኛ ግን ወደ እንግሊዝ ይሂድ እዚሁ እንግሊዝ አምባሲ ተሸሽጎ ይሁን አላወቅንም:: ሕወሓቶች ከስታሊን የተማሩትና እንደብልጠት የሚቆጠርባቸው ያልፈለጉትን ሰው አገር ውስጥና በግልፅ አይገድልቱም:: አርከበ ልክ እንደ ትሮተስኪ ከአገር በፍቓዱ እንዲሄድ ጠይቀውታል ፤ አገር ለቆ ሄዷልም እየተባለ ነው:: አሁን የቀረን ዜና አርከበ በመኪና አደጋ ወይም በደም ካሰር ሕመም ወይም በስዃር ሕመም ወይም በደም ብዛት ሕመም ወይም መጠጥ ቤት ተጣልቶ ተገደለ ወይም ማንነቱ ያልታወቀ ሰው በተኮሰለት ሂወቱ አለፈ የምትለዋን ዜና ነው:: ይሄውላቹህ እንግዲህ እነዚህ ሲጀመርም የሩስያ አብዮት እስክራቸው በረሃ የወጡት “የነፃነት ታጋዮች” ስልጣን አጠባበቅ ላይም ከራሽያ እየተማሩ ልክ ሶቭየት ሕብረት ወደ አስር አገራት እንደፈራረሱባት ይቺን አገርም ሊያፈራርሱ የሚጠቅሟትን ሰዎች እያባረረችና በግፍ እያረደች ትገኛለች:: ማን ነበር ጋዜጤኞቿን በልታ ዝም የምትል ሀገር ያላት? ...ትልቅ ''ግን''......... ስታሊን ያንሁሉ ነገር ያደረገው የውትድርና ልብስና አውቶማቲክ ሽጉጥ እንደያዘና አብዛኛዎቹ ጓዶች ደግሞ በደረጃ ከሱ በታች ስለነበሩ ነው:: አባይ ግን ሰሞራና ሰዓረ በሁለት አቅጣጫ ወገቡ ላይ እንደሽጉጥ ካልታጠቃቸው በስተቀር የሚፈራውና የሚቀበለው ሰው የለም:: ሽጉጥ መታጠቅና የወታደር ካኪ መልበስ የተወው በ1985ዓ/ም ነው:: ሳሞራንም እንዳይታጠቀው ሳሞራ ራሱ አሁን አሁን ሽጉጡን ማቀበበል አቅቶታል:: ሰዓረ ደግሞ በግራ ስትታጠቀው ወደ ቀኝ እየዞረ በቀኝ ስትታጠቀው ወደ ግራ እየዞረ ስለሚያስቸግር አባይ አጣቢቅኝ ውስጥ ሊያገባው ይችላል:: ወዲ ወረደና ወዲ አሸብር እንዳይዛቸው እነሱም ዲሞክራሲና ሊበራል ሶሻሊዝም እንፍጠር እያሉ ከአባይ ጋር ሊግባቡ አይችሉም:: ባጫን እንዳይዝ : ባጫም እያወራው ሳለ ዳንስ እየጀመረ ሊያዋርደው ይችላል:: አበባው ደግሞ እንደማሊዎቹ ተገንጣይ ጓዶች አገውን ይÿ እገነጠላለሁ እያለ ሊያስቸግረው ስሚችል ቢቀርበት ነው የሚሻለው:: አባይ ያለችው ብቸኛ አማራጭ ከደርግ ውድቀት ወደዚሀ በውትድርና ቢቆይ እርከኑ ምን ያህል እንደሚሆን ካወራረደ በኋላ/ያው እንደሌሎቹ ሌቴናል ጀነራል ይደርስ ነበር/ ለአንድ ዓመት በውትድርና አገልግሎ በመፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን ስልጣን መረከብ ነው:: ይህ ዓይነት መንገድ ደግሞ ሊሆን አይችልም :: ምን ሊያደርግ እንደሚችል እኔም እንደሱ ጨንቆኛል:: እስቲ የስታሊን አምላክ ይርዳው!

0 comments:

Post a Comment