Thursday 12 September 2013

በአዲስ ዓመት አስገራሚ ዜና ከቃሊቲ – ‹‹ከአንድነት›› የሚል ጽሁፍ የሰፈረበት ኬክ ቃሊቲ እንዳይገባ ተደረገ – ፍኖተ ነጻነት

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮች እድሜ ልክ ተፈርዶበት በቅጣት ቤት የሚገኘውን ሰላማዊ ታጋይ አንዷለም አራጌን
‹‹እንኳን አደረሰህ አዲሱ ዓመት ፍጹም ነጻነትህን የምትቀዳጅበት እንዲሆን እንመኛለን እንታገላለንም››
በሚል ስሜት ተነሳስተው ኬክ በማስጋገር
‹‹ከአንድነት››
የሚል ጽሁፍ አጽፈውበታል፡፡
የአንዷለም ጠያቄዎች በሩን አልፈው የያዙትን ኬክ ለማስፈተሸ አስቀማሽ ጋር እንደደረሱ አስቀማሹ ኬኩንና የተጻፈበትን እየተመለከተ አንዴ ቆዮኝ ብሎ ጥሏቸው ሄደ፡፡ አስቀማሹ ሃፊዎቹን አስከትሎ መጣ ፡፡የሆነ ነገር ትከሻቸው ላይ የደረደሩ ሃላፊ ኮስተር ብለው
ኬኩ አይገባም እናንተ ግን መግባት ትችላላችሁ›
ይላሉ፡፡ የኬኩ በደል ምን እንደሆነ ሲጠይቁም
‹‹ከአንድነት››
ይላል አሏቸው፡፡
አንድነት በምርጫ ቦርድ እውቅና የተቸረው ቢሮ ያለው ሰላማዊ ፓርቲ ነው፡፡ አንዷለምንም እናንተ ሽብርተኛ በማለት አሰራችሁት እንጂ እስከሚታሰርበት ቀን ድረስ
የፓርቲው የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ነበር፡፡››
ይሏቸዋል፡፡
ኬኩን አንድነት ከሚለው ውጪ ይዛችሁ መግባት ትችላላች ከዚህ ውጪ አናስተናግድም ሃላፊው ይላሉ፡፡ የአንድነት አመራሮች በበኩላቸው ኬኩ ህገ ወጥ ነገር እስካልሰፈረበት ድረስ አንድነት የሚለውን የፓርቲያችንን ስም አንፍቅም፡፡ ፍላጎታችሁ ሰላማዊውን ታጋይ እንዳንጠይቀው ለማድረግ በመሆኑ እኛም አንገባም በማለት ግቢውን ለቅቀው ወጥተውላቸዋል፡፡1185993_10151839340271870_915504360_n

0 comments:

Post a Comment