ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ ስርአት ባደረጉት ምርጫ 1ኛ.ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው 2ኛ.አቶ ተክሌ በቀለ 3ኛ.አቶ ግርማ ሰይፉ ለመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡
ለመጨረሻው ዙር ሳያልፉ የቀሩት አቶ ትግስቱ አወሉ እና አቶ ሽመልስ ሀብቴ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተናግረው አንድነትን ለመምራት ከሚመረጠው ቀጣይ ሊቀመንበር ጋር ትግሉን ለማፋጠን እንደሚተጉ ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል፡፡
በተያያዘም ዜና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በቅርቡ በሚመረጠው አዲሱ ስራ አስፈፃሚ የሚቀጥሉ ተከታታይ ህዝባዊ ንቅናቄዎች እንደሚኖሩና በቀጣይነት ከሚነሱት የንቅናቄ አጀንዳዎች መካከል ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች እንደሚገኙበት ታውቀዋል፡፡ ከፓርቲው ህዝብ ግንኙነት የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው አንድነት የትግል የተፅእኖውን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ በማድረግ ወደ ለውጥ የሚደረገውን ትግል ከዳር የሚያደርሱ ስትራቴጂዎችን ነድፎ ከዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር እንደሚታገል አስገንዝቧል፡፡
0 comments:
Post a Comment