Sunday 8 September 2013

የአዳማ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል!!!

የአዳማ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል!!! ኢቴቪ በአዳማ የሁከት ድራማ በመስራት ለመቅረጽ ያደረገችው ሙከራ ከሸፈ ብራቮ አዳማዊያን! ጉዞ ወደ አዲስ አበባ!


September 8th, 2013


የአዳማ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል!!! ኢቴቪ በአዳማ የሁከት ድራማ በመስራት ለመቅረጽ ያደረገችው ሙከራ ከሸፈ ብራቮ አዳማዊያን! ጉዞ ወደ አዲስ አበባ! በጎንደር፣ ደሴ ፣ባህር ዳር፣ጂንካ፣ ወላይታ፣ባሌ ሮቢ፣ ፍቼ፣ አርባ ምንጭ ዛሬ አዳማ ቆይታ በማድረግ የሚልዮኖችን ድምጽ ያሰማው የአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ህዝባዊ ንቅናቄ ለመስከረም 5/2006 የመስቀል አደባባይ ሰለማዊ ሰልፍ ጓዙን ጠቅልሎ ሸገር ገብቷል፡፡
በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በአንድነት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ መሆኑ ታውቋል። የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ የማይቀር መሆኑን የተገነዘቡት የክልል መስተዳድሮች ሰልፉ የሚጀመርበትን አካባቢ በፌደራል አድማ በታኝና በፖሊሶች እንዲከበብ አድርገዋል፡፡ አስገራሚው ነገር ግን ወደ ሰልፉ መጀመሪያ ቦታ እየተመመ የሚገኘው ህዝብ በዙሪያው እየተከናወነ ለሚገኘው ነገር ቁብ ሳይሰጥ የተዘጋጁ መፈክሮችን እይሰማ መንገዱን ቀጥሏል፡፡ የፖሊሶችና የአድማ በታኞቹ ከበባ የህዝቡን ስነ ልቦና በፍርሃት ለመሙላት እንደሆነ የተረዱ የአንድነት አመራሮች በቁርጠኝነት ያለ ምንም ስጋት ህዝቡ እንዲቀላቀላቸው በማበረታት ሕዝቡም የፍርሀትን ጠርሙስ ሰበሮ ሰልፉን በቆራጥነት ተቀላቅሏል። ሆኖም በአዳማ በተደረገው ሰልፍ ላይ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ እንቅስቃሴ እንደጀመሩ ፖሊስ ከፊት በማስቆም ‹‹እኔ የደረሰኝ በዋናው መንገድ እንደማትጠቀሙ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መንገድ ማለፍ አትችሉም›› ይላል፡፡ በዚህ ና በዚያ መንገድ በማለት በዚህ ሰዓት መከልከል እንደማይችሉ በመጥቀስ ሰልፈኞቹ በመንገዱ ተቃውሟቸውን በማሰማት ቀጥለዋል፡፡
ሌላው አስገራሚ ትዕይንት በአዳማ አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ተገን አድርጎ የኦሮሚያ ቴሌቭዥን በአዳማ ሊሰራው የነበረው ድራማ ከወያኔው ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጎን ለጎን የተደናቀፈበት መሆኑ ታውቋል:: በዚሁ ሰልፍ ላይ የአንድነት የምዕራብ ቀጠና ሃላፊ አቶ አስናቀ ሸንገማ በኦሮምኛ ቋንቋና ፣የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስዮም መንገሻ ንግግራቸውን ያሰሙ ሲሆን በመጨረሻም ዶክተር ሃይሉ አርአያ ንግግር አድርገዋል፡፡
በአዳማ በteደረገው ሰልፍ ከተደመጡ መፈክሮች መካከል ፤
ውሸት ሰልችቶናል!
የኢቴቪ የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም ከአሸባሪነት አይለይም!
ድህነት በፕሮፓጋንዳ ብዛት አይጠፋም!
ሰብዓዊ ልማት ለሁሉም!
ስራ ማግኘት የዜግነት መብት ነው!
አምባገነኖች ባሉበት የአንዷለም ቤት እስር ቤት ነው!
ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለችም!
አንዷለም አራጌ፤ እስክንድር ነጋ፤ ናትናኤል መኮንን፤ ውብሸት ታዬ፤ ርዕዮት አለሙና ሌሎችም በአስቸኳይ ይፈቱ!!!!BToiHt6CYAEyOQo1069404_10151870041599743_631710615_n

0 comments:

Post a Comment