Sunday 27 November 2016

በጎጃምና በጎንደር ከ19,847 በላይ ወጣቶች ሲታሰሩ በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖችደግሞ ከ734 የጦር መሣሪያ ተገፏል

• በጎጃምና በጎንደር 19,847 ወጣቶች መታሰራቸው ተገለጸ፤
• በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖች 734 የጦር መሣሪያ ተገፏል

የመንግሥትን ፍርሀት መሸሻና መደበቂያ የሆነውን አስቸኳዋይ ጊዜ አዋጅ የቂም መወጣጫ ያደረጉት የብአዴን የወረዳ ባለሥልጣናት አስካሁን በቻግኒ ከፍጠኛ ቁጥር ያለው ወጣት በቀበሌ ጽ/ቤቶች ታጉሮ እንደሚገኝ መረጃዎች አመለከቱ።

ይህ ከፍተኛ ዘግናኝ ድርጊት የፊድራሉ መንግሥት ሪፖርት ካደረገው ውጭ ሆነው ቁጥር ባለሥልጣናቱ በቀበሌ ሊቀ መናብርቶቻቸው አማካኝነት የአማራን የለውጥ ኃይል ሞራላዊ ጉዳት እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማጥፋት በማለም እየተንቀሳቀሱሰ ሲሆን በዞን ደረጃ በአዊ ዞን በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች 4967 ወጣቶች ከማንድ ፖስቱ እውቅና ውጭ በአካበቢ ካድሪዎች ታስረው ወራት አልፏቸዋል። ይህንን ግፍ ላለማየት በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በመሰደድ ላይ ናቸው።

በምዕራብ ጎጃም 2941፣ በምስራቅ ጎጃም 871፤ በደቡብ ጎንደር 3441 እንዲሁም በሰሜን ጎንደር 4167 ወጣቶች በየቀበሌው የመገኝታቸው ዜና መረጃ የታፈነ ሲሆን የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ እንኳን ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ገልጧል።
ይህ በዚህ እንዳለ በአማራ ክልል ከሚገኙ 25489 መደበኛ እስረኞች ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጨመሩትን 19847 ወጣቶችን መመገብ አልቻልኩም ሲል የክልሉ ማረሚያ ቤት ተቃውሞውን ገለጸ። በክልሉ ለአንድ ታሳሪ በቀን 9.30 ብር ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በጀት የተመደበላቸው ሲሆን እስረኞችም በቂ ምግብ ባለማግኘታቸው እንደተራቡ ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙርያ እና በአዊ ዞን በዚገም አካባቢ የመሣሪያ ገፈፋ ተጀምሯል። እስካሁን በምዕራብ ጎጃም በተካሄደው የሌሊት ገፈፋ 534 እንዲሁም በአዊ ዞን ደግሞ 200 ክለሽ እና ቤለጅግ ተገፏል። መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሚኒሻዎችን እያስታጠቀ መሣሪያ እየገፈፈ የሚገኝ ሲሆን ያልተገፈፉ ዐማሮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
ከአማራ ፖሊስ በተገኝው መረጃ መሰረት ገፈፋው በደቡብ እና ሰሜን ጎንደር አጠናክሮ ለመቀጠል የመከላከከያ አደረጃጀት ተፈጥሯል።

(ሙሉቀን ተስፋው)

0 comments:

Post a Comment