Monday 21 November 2016

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አናንያ ሶሪ ታሰሩ – ከ15 ሺህ ሰው በላይ በኮማንድ ፖስቱ ታስሯል

በሶሻል ሚድያ ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትና በተደጋጋሚ በትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ሲጎሳቆሉ የቆዩት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ መታሰራቸው ተሰማ::  ከሳምንት በፊት የዞን 9ና የውይይት መጽሔት ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ በኮማንድ ፖስቱ ትፈለጋለህ ተብሎ መያዙ የሚታወስ ሲሆን አናንያ እና ኤልያስም እንዲሁ በተመሳሳይ ተይዘዋል::

ሁለቱ ጋዜጠኞች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ማዕከላዊ ታስረው ይገኛሉ:: ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በቅርቡ በትግራይ ነጻ አውጪው የፕሮፓጋንዳ ራድዮ ፋና ቀርቦ ስርዓቱን ሲሞግት የነበረ ጋዜጠኛ እንደነበር ይታወሳል::

በተመሳሳይም የቀድሞው የአንድነት አመራር የነበረው ዳንኤል ሺበሺም በኮማንድ ፖስቱ እየተፈለገ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

መንግስት በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩት ወገኖች ቁጥር 11 ሺህ ነው ብሎ ይናገር እንጂ የታሰሩት ቁጥር ከ15 ሺህ እንደሚበልጥ ምንጮች አረጋግጠዋል::

0 comments:

Post a Comment