Thursday 24 November 2016

ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ለትግራዩ መንግስት ጦር እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን ሰዋ | ከአውሮፓ ነበር ሊዋጋ የሄደው

በሰሜን ጎንደር ከአማራ ታጋዮች በተጨማሪ ውጊያ እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 በአርማጭሆ አብደራፊ ባደረገው ውጊያ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርዬ) በሕወሓት ወታደሮች በተከበበት ወቅት እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን በያዘው ጠመንጃ ማጥፋቱ ተሰማ::

በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ግንባሮች የአማራ ገበሬዎች እና የአርበኞች ግንቦት 7 የሕወሓትን መንግስት እየተዋጉት ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ኮማንደር የነበረው ሻለቃ መሳፍንት በአብራፊ የሄደውን አርበኞች የግንቦት 7 ጦር ሲመራ እንደነበር  ምንጮች ያስታወቁ ሲሆን የህወሓት ጦር በሜካናይዝ ደረጃ ቢከበውም ራሱን አጥፍቷል::

ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ወደ ኤርትራ ሄዶ አርበኞች ግንቦት 7ን የተቀላቀለው የተደላደለ ኑሮውን ከአውሮፓ ሉክዘምበርግ ትቶ ነው::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በሰሜን ጎንደር እያደረኩት ባለሁት ውጊያ የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት ለጊዜው የመሸግኩበትን ቦታ በሄሊኮፕተር ቢደበድብም መክቻቸዋለሁ ሲል መግለጫ አዉጥቶአል::

0 comments:

Post a Comment