በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት በዛሬው እለት በኖርዌይ ኦስሎ 18, December, 2015 (ታህሳስ 8, 2008 ዓ.ም ) በአዲስ አበባ ማስተር
ፕላን የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ያደረሰውን ግድያ እና በምዕራብ ኢትዮጵይ በጎንደር ክልል ለሱዳን
ተላልፎ የሚሠጠውን መሬት ምክንያት በመቃወም በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በኖርዌይ፣ ኦስሎ ተደረገ ።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ በኦስሎና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች
የድጋፍ ድርጅቱ ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ሰልፉ በተጀመረበት ቦታ በመገኛት በግፍ ለሞቱት የኦሮሞ ተማሪዎች ዘረኛውና
አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በመቃወም ድምጻቸውን አሰምታዋል ::
ሰላማዊ ሰልፉ በኖርዌይ የሰአት አቆጣጠር
ከቀኑ 14:00 ጀምሮ እስከ 15:30 የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያኖች በሰላማዊ መንገድ
ጥያቄያቸውን ሲጠይቁ በነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ጥይትን በማዝነብ ኢሰብሃዊ ድርጊት የፈጸመውን ግድያ እንዲሁም
ለሱዳን ያለ አግባብ በሚስጥር ተላልፎ ሊሠጥ ስለታሰበው መሬት የተነሳ በጎንደር ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን የዘር
ማጥፋት ወንጀል እና በጎንደር እስር ቤት ውስጥ ለተገደሉ ወገኖቻችን በመቃወም ቡዙዎችን የገደለውን የወያኔን
መንግስት የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን በማያዝ እና በማሰማት ተቃውሞቸውን በሀይል ገልጸዋል::
በሰልፉ ላይ
ሰልፈኞቹ ያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል የወያኔ መንግስት ገዳይ መንግስት ነው፣ የኦሮሞ ተማሪዎችን በጅምላ
መግደል ይቁም፣የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የእኛም ደም ነው፣ በኢትዮጵያ በጅምላ ስለተገደሉት የኦሮሞ ተማሪዎች
አዝነናል፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ መንግስት በሚስጥር የሚሰጠው የመሬት ውል ተቀባይነት የለውም የሚሉ
ይገኙበታል:: ሰልፈኞቹ በቀጥታ ወደ ኖርዌይጃውያን ፓርላማ ጽህፈት ቤት በመሄድ ለኖርዌይ መንግስት ጉዳዩን በግልጽ
ያሳወቁ ሲሆን ኖርዌይ ከወያኔ መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረም ጠይቀዋል::
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ
ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አመራር አቶ ዳንኤል አበበ፣ የአርበኞች ግንቦት7
ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዶ/ር ሙላለም አዳም፣ ከኖርዌይ ሸንጎ አቶ ግደይ ዘራፅዬን፣የኢትዮጵያውያን ማህበር
በኖርዌይ አመራር ወ/ሮ ዙፋን አማረ የተገኙ መሪዎችና ተወካዪች የወያኔን ግፍ በመቃወም ንግግር
አድርገዋል::በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ አቶ ዳንኤል አበበ
ወያኔ በዘር ከፋፍለህ ግዛ ስርአት ከታሪካዊ ጠላታችንን ከወያኔ ለመጋላገል የኦሮሞ ወንድሞቻችን የጀመሩትን ህዝባዊ
እምቢተኝነት አሁኑኑ በመቀላቀል የምናደርገውን ወገናዊ ግዴታችን ብቻ ሳይሆን ለራሳችንና ለኢትዮጵያ ህልውናም ጭምር
የምናደርገው ታሪካዊ የትውልድ ጥሪ ነው በማለት አስተላልፈዋል።
በዚህም ድርጅታቸው በድርጊቱ በጣም እንዳዘኑና
በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑና ለሞቱ ዜጎች ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን በመመኘት የታሰሩ ወጣት የኦሮሞ ተማሪዎች በአስቸኮይ
እንዲፈቱ፣ የዚህም ድርጊት ፈጻሚ አንባገነኖች በአስቸኮይ ለፍርድ እንዲቀርቡ በመጠየቅ የድርጅቱን የአቋም መልክት
ለኖርዌይጃውያን ምክር ቤት ተወካይ ያስረከቡ ሲሆን የምክር ቤቱም ተወካይ ንግግር አድርገው ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት
ሰአት ተጠናቋል::
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!.
0 comments:
Post a Comment