በተለያዩ ጊዜያት ሰለ ሰብአዊ መብት መከበር ፣ሰለ ፍትህ ፣እኩልነት እና ሃሳብን በነጻነት ስለመግለጽ ሲጽፉ እና ሲሰብኩ የአወዛጋቢው የጸረ ሸብር ህግ ሽፋን ለከባድ ቅጣት እና እሰራት የተዳረጉት የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አባላት የሆኑት እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ተመሰገ ደሳለኝ፣ ውብሸት ታዮ፣ሰለሞን ከበደ፣የሱፍ ጌታቸው ፣ሳሌህ አድሪስ ተስፋ ልደት ኬዳኔ አና የመሰሳሰሉት ጋዜጠኞች ለአፍታ እንኳን ሊዘነጉ አይገባም ሲል አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል (Amensty International) የተማጸኖ ጥሪውን አቅርቧል።
የመብት ተሟጋቹ ድርጅት በተላንትናው እለት የተከበረው አለማቀፍ የሰብ አዊ መብት ቀንን በማሰመልከት ባወጣው መግለጫው ከላይ የተጠቀሱት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አርበኞቹ እነ አሰክንደር ነጋ እና ሰማቸው ያለተጠቀሱት ነገር ግን በተለያዩ የአገዛዙ ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ ተወርውረው እየማቀቁ የሚገኙትን ወገኖች ሰለ ተጋድሏቸው እና ሰለ ከፈሉት መሰዋትነት ልንዘነጋቸው አይገባም ብሏል።ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአረቡ አለም ተቀሰቅሶ የነበረው የለውጥ ማእበልን በተመለከተ እና ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሰለሚኖረው ተዛማጅነት ሰፊ ትንታኔ ማቅረቡን ተከተሎ በአገዛዙ የጸረሽብር ህግ ክስ ቀርቦበት የ18 አመታት እስራት የተዳረገ ሲሆን ጋዜጠኛ ውብሸት እንዲሁ የኢሃአዲግ የሁለት አሰርት አመታት ጉዞን በመንቀፉ ለ14 አመታታ በዘዋይ ማረሚያ ቤት ተወርውሯል።በአሁኑ ወቅት ከእስራቱ ባሻገር በጤና መታወክ ምክንያት በእስር ቤት አየማቀቀ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገንም የተለያዩ ክሶች ቀርበውበት ለእስራት ተዳርጓል። በቅርቡ የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማ የአ/አ ጉብኝታቸውን ምክንያት በማድረግ የ ዞን 9 ማህበራዊ ድህረ ገጽ ጦማሪያኖች እና ጻፊት ሪዮት አለሙ ከእስራት መለቀቃቸውን ያወሳው ዘገባው ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ 2014 አመት ከ17 በላይ ጋዜጠኞችን በማሰር እና ብዛት ያላቸውን ደግሞ አገራቸውን ፣ ቤተሰባቸውን እና ሙያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግ በአለም በ4ኛ ደረጃ ትገኛለች ሲል ያወሳል።
በጎረቤት ግብጽ በቅርቡ የተደረገውን ህዝባዊ ቁጣን እና የመንግስት ለውጥን ለአልጀዚራ ቲሊቭዥን ሲዘግቡ በካይሮ ባለሰልጣንት ለተወሰኑ ወራቶች ለእስራት ተደርገው የነበሩት ፒተር ግረስቲ ፣መሃመድ ፋሂም እና ባሂር ሞሃመድ በመላው አለም ማህበረሰብ ዘንድ እለታዊ የመወያያ ርእሶች ሲሆኑ ከ10 አመታት በላይ በእስር ቤት አንዲማቀቁ የተበየነባቸው እነ እስክንድር ነጋ የከፈሉት መሰዋትነት እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ለችግራቸው ትኩርት ሰጪነት እና በአገዛዙ ላይ ጫና የመስፈጠር ሚዛኑ የተዛባ (አናሳ )ነው ተብሏል። ጋዜጠኛ አሰክንደር እና የተወሰስኑት በእስር ላይ የሚገኙት የሙያ አጋሮቹ ለፈጸሙት ሙያዊ ኣና ሰነምግባራዊ ተጋድሎ የተለያዩ አለማቀፋዊ ሽልማቶችን እና አክብሮት ማግኘታቸው አይዘነጋም።
በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ በነጻው እና በሰለጠነው አለም የሚኖረው የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ በአገር ቤት ውስጥ ሰላም ፣ ዲሞክራሲ እና የሃሳብ ነጻነት እንዲከበር ከፍተኛ መሰዋትነት በመክፈላቸው እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለ ከፍተኛ አደጋ ያጋለጡት እነ እስክንደር ነጋ ሆነ ለሰደት እና ለተለያዩ ችግሮች የተዳረጉት ቤተሰቦቻቸውን በሞራል እና በገንዘብ በመታደግ በአሰር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች የከፈሉት መሰዋትነት ከንቱ አልመሆኑን ለአገዛዙ ጭምር በተግባር ማሳየት እንደሚገባቸው በርካቶች ይመክራሉ።
0 comments:
Post a Comment