Wednesday 9 December 2015

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምግብ ቦይኮት አደረጉ - የሚሊዮኖች ድምጽ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በስፋት ተቃዉሟቸውን እያሰሙ ነው። በወያኔ ግፈኛ ታጣቂዎች በጎንደር እና በኦሮሚያ በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ሃዘናቸውን በመግለጽ፣ እህቶቻችንም ጥቅር በመልበስ፣ በካፌቴሪያ ምሳ አንበላም ብለው ብይኮት አደርገዋል።

እንቅስቃሴ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ወደ አዲስ አበባ እየገባ ነው።  እንቅስቃሴው በኦሮሞ ተማሪዎች በማስተር ፕላኑ ዙሪያ ቢጀመርም፣ መልኩን በስፋት ቀይሮ፣ አሁን የሁሉም ዜጎች እንቅቃሴና ሆኗል። ለመሰረታዊ የመብት፣ የነጻነት የእኩልነትና የዲሞክራስ ጥያቄ ሆኗል።

በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች እየተደረጉ ያሉ እጅግ በጣም ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በሃረር ከተማ (ሃረሬ ክልል)፣ በዲላ ( ደቡብ ክልል፣ ጌዶ ዞን ዋና ከተማ) እንዲሁም በአዋሳ (የደቡብ ክልል ዋና ከተማ) ተቃዉሞዎች ተደረገዋል።
በተለይም በአዲስ አበባ ህይ ስኩሎችን በቅርብ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።



0 comments:

Post a Comment