
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ የደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ
ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ በትናንትናው
ዕለት ኢህአዴግን የሚተቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣
20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ ከመደረጉም ባሻገር ጥያቄ የሚያነሱት ላይ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለነገረ
ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት ጥያቄ ያነሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ስልጠና ወደሚሰጡባቸው ትምህርት ቤቶች ግቢ እንዳይገቡ ከመደረጉም
ባሻገር የድብዛ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስልጠናውን መቃወማቸውን ተከትሎ ፖሊስ እርምጃ
እየወሰደ...