የኢትዮጵያ ‹‹መንግስት›› እስርኞቹን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አምነስቲ ጠየቀ
ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ታፍሰው የታሰሩትና ከፍተኛ ደብደባ የደረሰባቸው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎችን እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ፡፡ ከአሁን ቀደምም በርካታ ኢትዮጵያውያን ሀሳባቸው በነጻነት በመግለጻቸውና ህገ መንግስቱን የሚሰጣቸውን መብት በመጠቀማቸው መታሰራቸውን ያስታወሰው አምነስቲ ኢንተርናሽናል በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ላይ የተወሰደው እርምጃ ባለስልጣናቱ ምርጫው ከመድረሱ በፊት ለተቃውሞ ጎራው ያሳዩት ጥላቻ ነው ብሎታል፡፡
ምርጫ 2007 ዓ.ም በተቃረበበት ሁኔታ እንዲህ አይነት እርምጃ መወሰዱ ያሳስበኛል ያለው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አፍሶ ያሰራቸውን ብቻ ሳይሆን ሀሳባቸውን በመግለጻቸውና ህገ መንግስቱን ተጠቅመው በመቃወማቸው የታሰሩትን ሁሉንም እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈታ ይገባል ሲል ጠይቋል፡፡
http://www.amnesty.org/en/library/info/AFR25/009/2014/en

0 comments:
Post a Comment