Thursday, 18 December 2014

ደማቅ ህዝብዊ ስብሰባ በኖርዌ በርገን ከተማ ቅዳሜ Dec 13.2014 ዓ.ም ተካሄደ

ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ አዘጋጂነት የተካሄደው ይህ ህዝባዊ ስብሰባ ከመላው የኖርዌ ከተሞች እና በአቅራቢያዊ ከሚገኙ አጎራባች ሀገሮች የመጡ ኢትዮጵያዊያኖች ተሳታፊ ሆነውበታል:


23
ስብሰባው የተጀመረው ኢትዮጵያ ውሰጥ ባለው አስከፊ ስርዓት በቀጥታ የመንግስት ትእዛዝ በስውርም ይሁን በግለጽ ህይወታቸውን ላጡ ፣ቤተሰባቸው ለተበተነባቸው፣ትዳራቸው ለፈረሰ፣ ጧሪ ቀባሪ አጥተው የስቃይ ህይወት ለሚገፉ፣ በጎረቤት ሀገሮች እስር ቤቶች ውስጥ ለሚሰቃዩ፣ በስደት በበረሃውና በባህር ውሰጥ ህይወታቸው አልፎ ያለቀባሪ ለቀሩት ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር።

በመቀጠል ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አንተነህ አማረ ሲሆኑ፡ እሳቸውም እንግዶቹንና ተሰብሳቢዎቹን እንኳዋን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ በሀገራችንና በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል በመዘርዘር ህብረተሰባችን ከዚህ ውስብስብ ችግር እንዲወጣ ሁላችንም የየድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል በማለት እዚህ በአዳራሽ ውስጥ የተሰባሰብነው ተመካክረን መፍተሄ ለማምጣት እስከሆነ ድረስ ሁላችሁም በንቃት እንድትሳተፉ እየጋበዝኩ መልካም የውይይት መድረክ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

231
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ  ዋና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ይኋንስ አለሙ ሲሆኑ ፡እሳቸውም ይህ የዛሬው ስብሰባ ለኔ በሁለት አብየት ምክነያቶች በጣም  የተለየ ነው ካሉ በኋላ ይህውም  አሉ 1ኛ/ ይህ ስብሰባ ቅርንጫፍ ጽ∕ቤቱ እንደ አዲስ ከተዋቀረ በኋላ በመሆኑ እና 2ኛ. በራስ አነሳሽነት ያለምንም  ድጋፍ በቅርንጫፍ  ጽ∕ቤቱ ብቻ መከናወኑ በማለት አድናቆታቸውን ገልፀዋል። በመቀጠልም የሰማያዊ እና የዘጠኙ ፓርቲዎቸ ህብረት በቅርቡ በመስቀል አደባባይ ያደረጉትን ጀግንነት የተሞላበት እና ብዙ ዋጋ የተከፈለበት የሰላማዊ ሰልፍ ህዘባችን የፍርሃትን ደመና ገፎ አንባገነኖችን ለመጋፈጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጦ መነሳቱን የሚያመለክት መልካም ጅምር ነው በማለት እኛም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለዲሞክራሲ ፣ለፍትህ እና ለነፃነት የሚሰሩ ኋይሎችን በሞራል ፣ በቁሳቁስና እና በፋይናንስ መደጋፋችንን እንቀጥላልን በለዋል በመጨረሻም መደራጀት ህብረትን ፣ህብረት ኋይልን፣ኋይል ደግሞ ለውጥን ያመጣል ሰለዚህ እንደራጅ እና ከማንም ትእዛዝ ሳንጠብቅ በራሳችንና በምንችለው ሁሉ ለትግሉ አስተዋፆ በማድረግ ከባርነት እራሳችንን ነፃ እንውጣ ብለዋል።

2311
ግንቦት 7ን በመወከል በስብሰባው ላይ የተገኙት  የግንቦት 7 ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ዶ∕ር ሙሉዓለም አዳም በበኩላቸው “ለምን ትግሉ እረጅም ጊዜ ወሰደ” በሚል ርዕስ ሥር ስድስት ነጥቦችን በማንሳት ጥልቅ እና ሰፊ የሆነ ትንተና ያቀረቡ ሲሆን ተሰብሳቢዊው በከፍተኛ ተመስጦ ውስጥ ሆኖ ሲከታተላቸው ነበር፡ እነሱም..

1ኛ. ሰለ ነፃነት ያለን ግንዛቤ አነስተኛ መሆን ወይም ነፃነትን ከሀገር ጋር ብቻ ማያያዝ፡
2.የወያኔ ቅጥ ያጣ አፈናና መረን የለቀቀ ረገጣ፡
3.የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል አውቆም ይሁን ሳያውቅ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ መሆን፡
4.ከቤተሰብም ይሁን ከአካባቢ የወሰድነው ጎጂ በህሪ ማለትም ይሉኝታ እና አደርባይነት፡
5.በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ተሰባስበው ያሉ ግለሰቦች ከሀገርና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ለድርጅት ፍላጎት ተገዢ መሆን እና
6.በጥናት ላይ የተመሰረተ በብስለት የታገዘ የፖለቲካ ትግል አለመኖር ናቸው ብለዋል፡
ተሰብሳቢውም ብዙ ጥያቄዎችንና አስተያየቶች ለሁለቱ እንግዶች ያቀረበሲሆን ከመድረክም ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡ በመጨረሻም ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ በርገን ቅርንጫፍ ዋና ሰብሳቢ አቶ አንተነህ አማረ በስብሰባው በጣም መርካታቸውን በመግለፅ እንጋዶቹንና ተሰብሳቢውን በማመስገን የስብሰባው ፍፃሜ ሆኗል።


0 comments:

Post a Comment