Wednesday, 30 November 2016

Prominent Ethiopian opposition leader reportedly arrested by the Ethiopian government security forces

A prominent opposition leader and Chairman of the Oromo Federalist Congress, Professor Merera Gudina, has reportedly been arrested by the Ethiopian government security forces upon his returning from Europe. It has been known that Professor Gudina was one of the invitees along with Professor Berhanu Nega, Chairman of patriotic Ginbot 7, in a recent Brussels European parliament hearing about the grave human right situation in Ethiopia.

Professor Merara Gudina has been arrested by the government security forces upon his arrival at the airport. Many speculate that the cause of his arrest might be related with the Belgium Ethiopian community meeting that was attended by both Professor Merera Gudina and Berhanu Nega.

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

ኢትዮጵያንና ኢትዮጲያዊነትን ለማዳን ብሎም የተጨቆነውን ህዝባችንን በጫንቃው ላይ የተጫነበትን የባርነት ቀንበር አሽቀንጥሮ በመጣል ህዝብ ቀና ብሎ እንዲሄድና የዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን መራራና እልህ አስጨራሽ የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘው ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይልና መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት እርምጃ የወያኔን ሹማምንቶች አንገት ያስደፋ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራ ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ህዳር 16 ቀን 2009 .. የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔው አወቃቀር ክልል 3 ብሎ በሚጠራው አካባቢ ግጨው በተባለው ቦታ ከወያኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ጋር ባደረገው እረጅም ሰዓት የፈጀ ውጊያ 22 በመግደልና 29 ደግሞ በማቁሰል በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል የቆሰሉ ወታደሮችም ዲቪዥን ወደሚገኘው ሆስፒታል እንደተጓጓዙም የሪፖርተራችን መረጃ ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም ህዳር 17 ቀን 2009 .. በዚሁ በአማራ ክልል ዳንሻ አካባቢ ልዩ ስሙ ማይለሚን በተባለው ቦታ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው ውጊያ 12 በመግደልና 14 በማቁሰል የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝ ሹማምንቶችን ቅስማቸውን የሰበረ አንፀባራቂ ድል እንዲሁም የወገንን አንጀት ያራሰ ድል መጎናፀፉን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል፡፡

በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች የህብረተሰቡን ድጋፍ እያገኘና ህዝብን ከጎኑ ማሰለፍ የቻለው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ባደረጋቸው ተከታታይ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎች የሃገርና የወገን ደራሽነቱን ያስመሰከረበትን ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡንና ይዞት የተነሳው አላማም በሃገራችን ላይ የተንሰራፋውን አምባገነናዊ ስርዓት ገርስሶ በመጣል ሃገርና ህዝብን መታደግ በመሆኑ የአካባቢ ነዋሪ ማህበረሰብም ከፍተኛ አቀባበልና ድጋፍ እያደረገለት ይገኛል፡፡


Tuesday, 29 November 2016

የብሪታኒያ ሌበር ፓርቲ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ለሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥሪ አቀረበ

የብሪታኒያው አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለሃገሪቱ ዜጎች መብት መከበር የገቡትን ቃል በማክበር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ የሃገሪቱ ሌበር ፓርቲ ጥሪውን አቀረበ።

በአቶ አንዳርጋቸው ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው ፓርቲው፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ ለማድረግ የፊርማ ድጋፍ የማሰባባሰቢያ ዘመቻ እንደሚያካሄዱም ይፋ አድርጓል። ላለፉት ሶስት ወራት የብሪታኒያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው እንዳይጎበኙ ተደርጎ መቆየቱን ያወሳው ሌበር ፓርቲ፣ የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት አሳስቧል።

በቅርቡ የተሾሙት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቦሪስ ጆንሰን ስልጣናቸውን በተረከቡ ጊዜ የብሪታኒያ ዜጎች ጥቅም መከበር ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ እንደሆነ የገቡትን ቃል በተግባር ማሳየት እንዳለባቸው የፓርቲው መግለጫ አመልክቷል።


የኢትዮጵያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ለሶስት ወር ያህል ጊዜ በብሪታኒያ ተወካዮች እንዳይጎበኙ ጥሎት የሚገኘው እገዳ በብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ ልዩ ትኩረት ስቦ እንደሚገኝም ለመረዳት ተችሏል።
የብሪታኒያው ሌበር ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይን አስመልክቶ ለሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ደብዳቤ በመጻፍ ስጋቱን እየገለጸ መሆኑንም አክሎ አስታውቋል።


የቀድሞው የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊሊፕ ሃሞንድ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉ ጊዜ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የህግ የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል።
ይሁንና ሁለቱ ወገኖች የደረሱት ስምምነት እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ሊደረግ አለመቻሉን የሌበር ፓርቲው በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል።


አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቦሪስ ጆንሰን ከተለያዩ አካላት እየቀረበ ያለውን ስጋት ግምት ውስጥ በማስገባት ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አፋጣኝ ምላሽን እንዲሰጥ ፓርቲው አክሎ አሳስቧል።


የብሪታኒያው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና የአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይን በመከታተል ላይ የሚገኘው ሪፕሪቭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ለደህንነታቸው ስጋት እንዳደረባቸው መግለጻቸውን በቅርቡ ይፋ ማደረጉ ይታወሳል። ይሁንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ድረስ የሰጡት ምላሽ የለም።


ኢሳት
 

Coalition renewed vow to struggle for democratic Ethiopia

Leaders of the recently established political coalition held a public meeting in Stockholm, Sweden, on Sunday where they renewed their commitment to work for the formation of an all inclusive democratic system in Ethiopia.

The leaders of the Ethiopian National Movement, who officially launched the coalition in October at a signing ceremony in Silver Spring, Maryland, have also noted that the issues of ethnicity in Ethiopia would be resolved once and for all when there is a system in place that respects the rights of every individual.

The four parties making the coalition are the Oromo Democratic Movement (ODF), Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy, Afar People’s Party and Sidama People’s Democratic Movement.

Prof. Berhanu Nega, co-chair of the coalition and representing PG7, said on the occasion that the parties have come together as one because they believe in the formation of one and united Ethiopia, where political problems in the country could only be resolved through a democratic system.

Nega said the coalition does not claim to represent all ethnic groups in the country as they were not given the mandate by the people. But he said that any political organization could join the coalition if it accepts the sovereignty of Ethiopia and believes in the formation of a democratic system.

Leenco Laata, also co-chair of the coalition and representing ODF, said on his part that it was high time political groups come under one umbrella as individual efforts by separate entities did not bear fruit as seen in the last 25 years.   

Dr. Konte Musa, representing the Afar People’s Democratic Party (ADP) noted on his behalf that the people of Afar do not put the sovereignty of Ethiopia for negotiation. He said they formed the ADP in a bid to draw attention to the plight of the people and region of Afar under the TPLF tyrannical rule.
A fundraising drive was also held on the occasion in support of the new coalition.


Monday, 28 November 2016

አቶ ዮናታን ተስፋዬ የቀረበበትን ክስ ለመከላከል ታዋቂና በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች በምስክርነት ተጠርተዋል

*አቶ በቀለ ገርባና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከማ/ቤት ቀርበዋል፤ ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉን ያሰረው አካል ሳያቀርበው ቀርቷል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በፌደራል አቃቤ ህግ የቀረበበትን ሽብር ክስ እንዲከላከል የተወሰነበትን ክስ ለመከላከል የኦፌኮ ፕሬዚደንትና ም/ፕሬዚደንትን ጨምሮ ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸውና ታዋቂ ሰዎች በምስክርነት ተጠርተዋል፡፡


አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ህዳር 19/2009 ዓ.ም መከላከያ ምስክሮችን ለማስደመጥ በተያዘለት ቀጠሮ መሰረት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቧል፡፡ አቶ ዮናታን በጠበቃው አማካኝነት የምስክሮችን ዝርዝር ለፍ/ቤት ያስረዳ ሲሆን፣ ከምስክሮቹ መካከል አብዛኞቹ ሲገኙ ሦስቱ ብቻ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተከላከል የተባልሁበትን ክስ በመከላከያ ምስክርነት ቀርበው ያስረዱልኛል ያላቸውን 10 ምስክሮች ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡ እነዚህም ወላጅ አባቱ ቀሲስ ተስፋዬ ረጋሳ፣ ታናሽ እህቱ ገዳምነሽ ተስፋዬ፣ የቅርብ ጓደኛው ኤፍሬም ታያቸው፣ የኦፌኮ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ የህግ ምሁሩ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም፣ በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የፍልስፍና መምህሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ጋዜጠኛና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ እና አቶ ሙላቱ ገመቹ ናቸው፡፡
ከእነዚህ መከላከያ ምስክሮች መካከል ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና ጋዜጠኛና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ በዛሬው ቀጠሮ አልቀረቡም፡፡ በእስር ላይ የሚገኘው በፍቃዱ ኃይሉን ጨምሮ ዛሬ ያልቀረቡት እንዲቀርቡ፣ የቀረቡትም ተጨማሪ መጥሪያ ሳያስፈልጋቸው በቀጣይ ቀጠሮ እንዲቀርቡ ታዝዟል፡፡

ተከሳሹ በዚህ መሰረት አብዛኞቹ ምስክሮቹ መገኘታቸውን ችሎት ፊት አቅርቦ በማስረዳት፣ ምስክሮቹን አግኝቶ ስለሚመሰክሩበት ጉዳይ ለመነጋገር ጊዜ እንደሚፈልግ በመግለጽ ተለዋጭ ቀጠሮ ጠይቋል፡፡ ከምስክሮች መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹የፍ/ቤት መጥሪያ በእጄ አልደረሰኝም፡፡ ጠዋት ትፈለጋለህ ተብዬ በጽ/ቤት ተጠርቼ ነው የመጣሁት፡፡ ስለምመሰክርበት ጉዳይ አሁን ገና ነው የሰማሁት፡፡ የሙያ ምስክርነት እንድሰጥ ስለተጠራሁ ትንሽ የዝግጅት ጊዜ እንዲኖረኝ በተለዋጭ ቀጠሮ ምስክርነቴን እንድሰጥ ይፈቀድልኝ›› ሲል ከተከሳሹ አቤቱታ ጋር የተጣጣመ ማሳሰቢያ ለችሎቱ አሰምቷል፡፡

አቃቤ ህግ በበኩሉ ዛሬ የቀረቡት ምስክሮች እንዲመሰክሩ እንዲደረግለት ጠይቋል፡፡ ሆኖም ፍ/ቤቱ በተከሳሽ የቀረበውን ማሳሰቢያ በመቀበል ምስከሮቹ ተሟልተውና ስለሚመሰክሩበት ጉዳይ ተረድተው ሲቀርቡ ምስክርነታቸውን ለመስማት በሚል ለታህሳስ 26 እና 27/2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከሰው ምስክሮች በተጨማሪ ሦስት የሰነድ ማስረጃዎችን ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

በዛሬው ዕለት ለምስክርነት ከቃሊቲ እስር ቤት የቀረበው የ18 አመት ፍርደኛ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሙሉ ጥቁር ሱፍ ከጥቁር መነጽር ጋር ለብሶ እጆቹ በካቴና ታስረው በከፍተኛ ጥበቃ ፍ/ቤት ሊቀርብ ችሏል፡፡ በቃሊቲም ሆነ በቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች የእስረኛ ዩኒፎርም ለብሰው የቀረቡ ቢሆንም እስክንድር ነጋ ብቻ በተለየ በሱፍ ልብስ መቅረቡን ለመመልከት ተችሏል፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ከፍ/ቤት ግቢ በመኪና ሊጫኑ ሲወሰዱ በካቴና የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግ በፈገግታ ታጅቦ ‹‹አይዞን እንበርታ!›› የሚል ቃል ሰላምታ ላቀረቡለት ሁሉ ተናግሯል፡፡

ምንጭ:- የኢትዮጲያ ሰዕባዊ መብቶች ፕሮጀክት

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በስዊድን የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን ገለጸ

በቅርቡ በ4 የፖለቲካ ድርጅቶች የተመሰረተው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ትናንት እሁድ በስቶክሆልም ከተማ የተሳካ ስብሰባ ማድረጉን ገልጿል። የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መሪ አቶ ሌንጮ ለታ እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ ስብሰባው በስቶክሆልም /ስዊድን የንቅናቄው አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ ንግግር ተከፍቷል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ሰፊ ንግግር፣  ሁሉም የንቅናቄው አባል ድርጅቶች ኢትዮጵያን እንደ አንድ ሉአላዊ አገር የሚቀበሉ መሆናቸውን እና ችግሮቻቸውን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት እንዳለበት ስምምነት ላይ የደረሱ በመሆኑ ተቀራርበው ለመስራት ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።

አገራዊ ንቅናቄው የድርጅቶች እንጅ የብሄር ውክልና የለውም ያሉት ፕ/ር ብርሃኑ ፣ ማናችንም ቢሆን ህዝበ ውሳኔ ተካሂዶ የህዝብ ውክልና ባልያዝንበት ሁኔታ የብሄሮችን ውክልና ታሳቢ ያደረገ ጥምረት ልንፈጥር አንችልም ብለዋል። ማንኛውም ድርጅት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከተቀበለና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት ፈቃደኛ ከሆነ በጥምረቱ ውስጥ ገብቶ መስራት እንደሚችሉ ፕሮፌሰሩ በዝርዝር አስረድተዋል።

አቶ ሌንጮ በበኩላቸው ለብቻ የሚደረገው ትግል የትም እንደማያደርስ የ25 አመታት ጉዞ ምስክር ነው ብለዋል። ምዕራባውያንም ቢሆኑ ፍላጎታቸው እንድንሰባሰብ ነው ያሉት አቶ ሌንጮ፣ ይህ ጥምረት ረጅም ርቀት ይሄዳል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ደግሞ “ የአፋር ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ነው “ ያሉ ሲሆን፣ በብሄር ለመደራጀት የፈለጉት አካባቢያቸው ትኩረት እንዲያገኝ እንጅ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ስትመሰረት የብሄር ፖለቲካው ያከትማል ብለዋል። ከኖርዌይ ለስብሰባ ስዊድን የተገኘው አትሌት ሙሉጌታ ዘውዴ  ለውድድር ለብሶት የነበረውን የአንዳርጋቸው ጽጌ ምስል የያዘ ቲሸርትና የተሸለመውን ዋንጫ ለንቅናቄው አበርክቷል።

በዝግጅቱም ከፍተኛ ገቢ መገኘቱን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

Sunday, 27 November 2016

በጎጃምና በጎንደር ከ19,847 በላይ ወጣቶች ሲታሰሩ በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖችደግሞ ከ734 የጦር መሣሪያ ተገፏል

• በጎጃምና በጎንደር 19,847 ወጣቶች መታሰራቸው ተገለጸ፤
• በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖች 734 የጦር መሣሪያ ተገፏል

የመንግሥትን ፍርሀት መሸሻና መደበቂያ የሆነውን አስቸኳዋይ ጊዜ አዋጅ የቂም መወጣጫ ያደረጉት የብአዴን የወረዳ ባለሥልጣናት አስካሁን በቻግኒ ከፍጠኛ ቁጥር ያለው ወጣት በቀበሌ ጽ/ቤቶች ታጉሮ እንደሚገኝ መረጃዎች አመለከቱ።

ይህ ከፍተኛ ዘግናኝ ድርጊት የፊድራሉ መንግሥት ሪፖርት ካደረገው ውጭ ሆነው ቁጥር ባለሥልጣናቱ በቀበሌ ሊቀ መናብርቶቻቸው አማካኝነት የአማራን የለውጥ ኃይል ሞራላዊ ጉዳት እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማጥፋት በማለም እየተንቀሳቀሱሰ ሲሆን በዞን ደረጃ በአዊ ዞን በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች 4967 ወጣቶች ከማንድ ፖስቱ እውቅና ውጭ በአካበቢ ካድሪዎች ታስረው ወራት አልፏቸዋል። ይህንን ግፍ ላለማየት በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በመሰደድ ላይ ናቸው።

በምዕራብ ጎጃም 2941፣ በምስራቅ ጎጃም 871፤ በደቡብ ጎንደር 3441 እንዲሁም በሰሜን ጎንደር 4167 ወጣቶች በየቀበሌው የመገኝታቸው ዜና መረጃ የታፈነ ሲሆን የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ እንኳን ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ገልጧል።
ይህ በዚህ እንዳለ በአማራ ክልል ከሚገኙ 25489 መደበኛ እስረኞች ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጨመሩትን 19847 ወጣቶችን መመገብ አልቻልኩም ሲል የክልሉ ማረሚያ ቤት ተቃውሞውን ገለጸ። በክልሉ ለአንድ ታሳሪ በቀን 9.30 ብር ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በጀት የተመደበላቸው ሲሆን እስረኞችም በቂ ምግብ ባለማግኘታቸው እንደተራቡ ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙርያ እና በአዊ ዞን በዚገም አካባቢ የመሣሪያ ገፈፋ ተጀምሯል። እስካሁን በምዕራብ ጎጃም በተካሄደው የሌሊት ገፈፋ 534 እንዲሁም በአዊ ዞን ደግሞ 200 ክለሽ እና ቤለጅግ ተገፏል። መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሚኒሻዎችን እያስታጠቀ መሣሪያ እየገፈፈ የሚገኝ ሲሆን ያልተገፈፉ ዐማሮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
ከአማራ ፖሊስ በተገኝው መረጃ መሰረት ገፈፋው በደቡብ እና ሰሜን ጎንደር አጠናክሮ ለመቀጠል የመከላከከያ አደረጃጀት ተፈጥሯል።

(ሙሉቀን ተስፋው)

Thursday, 24 November 2016

ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ለትግራዩ መንግስት ጦር እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን ሰዋ | ከአውሮፓ ነበር ሊዋጋ የሄደው

በሰሜን ጎንደር ከአማራ ታጋዮች በተጨማሪ ውጊያ እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 በአርማጭሆ አብደራፊ ባደረገው ውጊያ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርዬ) በሕወሓት ወታደሮች በተከበበት ወቅት እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን በያዘው ጠመንጃ ማጥፋቱ ተሰማ::

በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ግንባሮች የአማራ ገበሬዎች እና የአርበኞች ግንቦት 7 የሕወሓትን መንግስት እየተዋጉት ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ኮማንደር የነበረው ሻለቃ መሳፍንት በአብራፊ የሄደውን አርበኞች የግንቦት 7 ጦር ሲመራ እንደነበር  ምንጮች ያስታወቁ ሲሆን የህወሓት ጦር በሜካናይዝ ደረጃ ቢከበውም ራሱን አጥፍቷል::

ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ወደ ኤርትራ ሄዶ አርበኞች ግንቦት 7ን የተቀላቀለው የተደላደለ ኑሮውን ከአውሮፓ ሉክዘምበርግ ትቶ ነው::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በሰሜን ጎንደር እያደረኩት ባለሁት ውጊያ የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት ለጊዜው የመሸግኩበትን ቦታ በሄሊኮፕተር ቢደበድብም መክቻቸዋለሁ ሲል መግለጫ አዉጥቶአል::

Wednesday, 23 November 2016

38 እስረኞች በቂሊንጦ እስር ቤት እሳት በማስነሳት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው


(ኢሳት) ከሳሽ አቃቢ ህግ 38 ተከሳሾች ከጥር ወር 2008 ዓም ጀምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ግንቦት ሰባትና፣ በአልሸባብ የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈጸም በእስር ቤቱ በተለያዩ ወንጀሎች በእርማት ላይ ያሉ እስረኞችን በድብቅ በመመልመል አመጽ ለመፍጠር መረጃን ሲለዋወጡ ነበር ሲል በክሱ አመልክቷል።

ይሁንና ተከሳሾቹ ሽብርተኛ ከተባሉት ድርጅቶች ጋር በእስር ቤት እያሉ በምን መልኩ ግንኙነት ሲያደርጉ እንደነበር የሰጠው ዝርዝር መረጃ የሌለ ሲሆን፣ 38 ግለሰቦች 10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውም በክሱ መካተቱን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘግበዋል።

በነሃሴ ወር በቂሊንጦ እስር ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በትንሹ 23 እስረኞችን መሞታቸው ይታወሳል። በእለቱ በእስር ቤቱ ያለ ትጥቅ በጥበቃ ላይ የነበረ አንድ የጸጥታ ባልደርባ የእስር ቤቱ የጸጥታ ሃይሎች የእሳት ቃጠሎውን ተከትሎ የተኩስ ዕርምጃ ሲወስዱ እንደነበር ለአዲስ ስታንዳርድ መጽሄት እማኝነት መሰጠቱ ተዘግቧል። መንግስት በበኩሉ እስረኞቹ ከአደጋው ለማምለጥ በሞከሩ ጊዜ በተፈጠረ መረጋገጥ ህይወታቸው አልፏል ሲል ማስተባበያ መስጠቱ ይታወቃል።

38 እስረኞች ላይ ክሱን የመሰረተው አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ አመጽ ማነሳሳት እንዲችሉ በውጭና ሃገር ውስጥ ከሚገኙ አባላትና ማረሚያ ቤት ውስጥ ከሚገኙ ታራሚዎች ገንዘብ ሲያሰባስቡ እንደነበር በክሱ አመልክቷል። ተከሳሾቹ በእስር ቤት ውስጥ እያሉ በምን ሁኔታ ገንዘብን ሲቀበሉ እንደነበር የታወቀ ነበር የሌለ ሲሆን፣ ግለሰቦቹ የአመጽን ድርጊት ይመራሉ ተብለው ለመለመሏቸው ታራሚዎች ክፍያ ሲፈጽሙ ነበር ተብለዋል።

በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ ከኢሳት ጋር ቃለ-ምልልስን ያደረጉ የሟች እስረኛ ቤተሰቦች የቤተሰብ አባሎቻቸው የሞቱበት ሁኔታ እንዳይታወቅ አስከሬን በልዩ መንገድ ታሽጎ እንደተሰጣቸው አስታውቀዋል።
በእስር ቤቱ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው ከቃጠሎው በፊት በእስር ቤቱ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበርና እስረኞቹ በዚሁ የተኩስ አደጋ መሞታቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ሲገልፅ እንደነበር የሚታወስ ነው።


Monday, 21 November 2016

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አናንያ ሶሪ ታሰሩ – ከ15 ሺህ ሰው በላይ በኮማንድ ፖስቱ ታስሯል

በሶሻል ሚድያ ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትና በተደጋጋሚ በትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ሲጎሳቆሉ የቆዩት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ መታሰራቸው ተሰማ::  ከሳምንት በፊት የዞን 9ና የውይይት መጽሔት ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ በኮማንድ ፖስቱ ትፈለጋለህ ተብሎ መያዙ የሚታወስ ሲሆን አናንያ እና ኤልያስም እንዲሁ በተመሳሳይ ተይዘዋል::

ሁለቱ ጋዜጠኞች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ማዕከላዊ ታስረው ይገኛሉ:: ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በቅርቡ በትግራይ ነጻ አውጪው የፕሮፓጋንዳ ራድዮ ፋና ቀርቦ ስርዓቱን ሲሞግት የነበረ ጋዜጠኛ እንደነበር ይታወሳል::

በተመሳሳይም የቀድሞው የአንድነት አመራር የነበረው ዳንኤል ሺበሺም በኮማንድ ፖስቱ እየተፈለገ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

መንግስት በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩት ወገኖች ቁጥር 11 ሺህ ነው ብሎ ይናገር እንጂ የታሰሩት ቁጥር ከ15 ሺህ እንደሚበልጥ ምንጮች አረጋግጠዋል::

Thursday, 17 November 2016

Internet freedom in Ethiopia is the fourth worst in the world

Ethiopia’s internet is among the least free in the world. According to a new index released by the nonprofit Freedom House, Ethiopia ranked ahead of only Iran, Syria, and China, out of 65 countries in terms of access to the internet, censorship, and freedom of information. It ranked the worst of any country in Africa.

Anti-government protests have gripped the country over the last year, gaining extra global attention when Ethiopian marathoner Feyisa Lilesa held his hands up, crossed at the wrist– an anti-government gesture used by protesters– at the Olympics. In response, Ethiopian authorities have intermittently shut down mobile phone and internet connections. They have also blocked social media like Facebook, WhatsApp, and Twitter.

Last month, a six-month state of emergency was declared, making it illegal to post or access information about the protests on social media as well as communicate with “outside forces.” Social media is also used to implicate dissidents and critics. Charges against protesters and opposition leaders often rely on evidence taken from social media, according to Freedom House.

Ethiopia’s heavy-handed approach to the internet goes further back than this last year. The country has passed counter-terrorism laws over the last five years that make it easier to pressure journalists and bloggers. The blogger Zelalem Workagenehu was sentenced to five years in prison this spring for running a course on digital security that authorities said was a cover for terrorist activities. Authorities have blocked news sites reporting on topics aside from the protests, like a severe drought that has left 18 million people in need of food and water supplies.

The situation is likely to continue. Government-owned EthioTelecom has a monopoly on internet access. Only 12% of the population has internet access and few people can afford it, given mobile access costs $85 a month compared to $30 a month in neighboring countries like Uganda or Kenya. Telecommunication infrastructure in rural areas, where most of Ethiopia’s population lives, is almost entirely absent.

Nor has the government opened the sector to competition. Chinese telecom firms ZTE and Huawei have been contracted to upgrade broadband and other networks in the country. But critics worry that Chinese investment is only helping EthioTelecom maintain its hold on the sector and continue censoring and surveilling citizens.

One bright spot is the growing network of bloggers and journalists in the Ethiopian diaspora who have been using their contacts within the country provide coverage of the country.

Quartz

Wednesday, 16 November 2016

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት እንደሚታሰር ታውቋል

ፌስቡክ ላይ በጻፋቸው ጹሁፎች ምክንያት የሽብር ክስ ቀርቦበት ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ የሚገኘውና በእስር ቂሊንጦ ያለው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በሚገኝበት እስር ቤት ውስጥ ከአርብ ህዳር 2/2009 ዓ.ም ጀምሮ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለዚህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የዳረገው ህዳር 2/2009 ዓ.ም የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበራቸው እነ አቶ በቀለ ገርባ ወደ ፍርድ ቤት አንሄድም በሚል ከቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ጋር አለመግባባት ፈጥረው ድብደባ ሲደርስባቸው አቶ ዮናታን ‹‹ለምን ትደበድቧቸዋላችሁ፤ በመግባባት ቢሆን አይሻልም ወይ›› በሚል ለግልግል ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋዬ በተለይ አብሮት የታሰረው አቶ አዲሱ ቡላላ ላይ ድብደባ ሲደርስበት ‹‹ተው አትደባደቡ›› በማለቱ ‹‹ምን አገባህ›› ተብሎ በራሱም ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት ከዚያ ወዲህ በሰንሰለት ለመታሰር እንደተዳረገ ታውቋል፡፡

አቶ ዮናታን ተስፋየ ሰንሰለቱ የሚፈታለት ቤተሰቦቹ ሊጎበኙት ሲጠራ ብቻ እንደሆነም የመረጃው ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ አቶ ዮናታን መከላከያ ማስረጃዎችን ለማድመጥ ለህዳር 19/2009 ዓ.ም ተለዋጭ የፍ/ቤት ቀጠሮ ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጲያ የሰባዕዊ መብቶች ፕሮጀክት

Tuesday, 15 November 2016

Oromo Leadership Convention calls on all Ethiopians to act in concert to remove TPLF

An Oromo Leadership Convention held over the weekend in Atlanta called on all Ethiopians to “stand together and act in concert to remove the TPLF regime that has become the source of all discontent, division and disorder in the country.”

In a resolution passed at the end of the convention, which coincided with the first year anniversary of the uprising in the Oromo region, the participants also called upon the international community to support the resolution by the UN Human Rights Commission that calls for an independent investigation into “the massacre committed by the regime against the oromo and other peoples of Ethiopia at the Ireecha festival on October 2, 2016”

The convention also condemned in the strongest terms the state of emergency declared by the regime, which it said uses the martial law to “legalize its illegitimate actions.”

The convention also decided to establish an a human rights organization to assist the people victimized by what it called the inhuman acts of the TPLF regime. The convention vows to further intensify the support given to the “Oromo revolution to fight against the TPLF regime that has lost all legitimacy.”

The resolution said the participants of the convention discussed four documents in plenary and breakout sessions but it did not give details contained in those documents.

Eight Oromo political organizations, political leaders, civil society representatives, activists and scholars, among others, participated at the three day conference which was closed to media.

At least 1500 people were killed in the last one year of protests by security forces while 60,000 were detained without due process of law, according to local political organizations. Upto 600 people lost their lives at the Ireecha religious festival in October when regime forces fired shots and used teargas at the millions of party goers resulting in deadly stampede. Ethiopian regime officials insist only 55 people lost their lives at the festival.

Monday, 14 November 2016

Ethiopian Blogger Rearrested Over Comments on State of Emergency

Ethiopian police have re-arrested a blogger and human rights activist who criticized the government, especially its handling of the ongoing protests in the Oromia and Amhara regions.

Befeqadu Hailu, a member of the Zone9 blogging collective, is one of seven bloggers – one in absentia – and three independent journalists who were arrested in April last year. Three months after their arrest, all ten were charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism Proclamation.

Two police officers calling themselves security members of the command post established to implement Ethiopia’s current six-month state of emergency reportedly took Befeqadu from his house. He is now detained at a police station known as 06 in the capital, Addis Ababa.

A month ago when the government declared the state of emergency, he wrote on his blog, The Q Perspective, that he anticipated his arrest given the general description of the emergency. He feared for his life, for other activists, and journalists, as the declaration allows security forces to use their authority to detain people without a court order.

                                                        Befekadu hailu