Sunday, 17 May 2015

የትግል ጥሪ ለነጻነትና ለፍትህ :- የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህና ለነጻነት !

ገዢው ፓርቲ በሰላማዊ ፓርቲዎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረገ ነው። የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች ታስረዋል። የአንድነት ፓርቲን አግዶ እንደ ሰማያዊ ያሉትን እያዋከበ ነው። ነጻ ጋዜጦች ተዘግትዋል።

ትግሉ የሕዝብ ጉዳይ እንጂ የድርጅት ጉዳይ ባለመሆኑ፣ የድርጅት መሪዎችን በማሰር፣ ድርጅቶችንም በማገድ፣ የህዝብንም ሆነ የታጋዮችን የነፃነት ፍላጎት መግታት አይቻልም። የአገዝዙን አፍናና በትር ለመቋቋም፣ ህዝቡን ወደአንድ አደረጃጀት ለማምጣትና በተናጥል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ውጤት በሚያመጡ መልኩ ለማሰባሰብ፣ ማእከላዊነትን የጠበቀ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የግድ አስፈላጊ ነው።

ይሄንንም እንዲረዳ፣ የዘመኑን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም፣ ሰላማዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ታስቧል። ቢያንስ በትግል ፅናታቸው የምንተማመንባቸውንና በዘመናዊ የኢንተርኔት ወይም በቂ የሞባይል አጠቃቀም ክህሎት ያላቸውን ለለውጥ የሚተጉ አካላትን በማሰባሰብ፣ ለእንቅስቃሴው ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊ ኃይላት ሁሉ ዝግጁ እንዲሆኑ ከወዲሁ እንጠይቃለን። የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በቀጣይ የምንገልፅ ስለሆነ፣ ከወዲሁ በታማኝነት ለዚህ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሊመጥኑ ይችላሉ የሚባሉ የሰላማዊ ትግል ደጋፊዎችና ተባባሪዎችን በማዘጋጀትና በመመረጥ ከወዲሁ ጥረት እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡

እንቅስቃሴያችን የ«ሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህና ለነጻነት» የሚል ስያሜ ነው ያለው። እንቅስቃሴያችን የጥቂት ግለሰቦችና ወይም ድርጅቶች ሳይሆን ነጻነትና ፍትህ የጠማው የ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንቅስቃሴ ነው። እነርሱ፣ ገዢዎች ብረት ሊኖራቸው ይችላል። እኛ ግን ሚሊዮኖች ነን !! በርግጥም እኛ ከተባበረን እና ከተነሳን ነጻነታችንን የሚወስድበን ማንም አይኖርም። ለነጻነትና ለፍትህ የምንቆምበትት ጊዜው አሁን ነው። አሁን ካልተነሳን መቼ ? እኛ ካልተነሳን ማን ?

ይሄን መልእክት ሼር ፣ ላይክ በማድረግ ያሰራጩ !!!!፡ ይሄ የሕዝብ ትግል ነው። የ እንያንዳንዳችን ትግል ነው !!!!

የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህና ለነጻነት !

0 comments:

Post a Comment