Tuesday, 12 May 2015

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ስድስት ወር ተፈረደበት

በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም በተጠራ ሰልፍ ላይ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ስድስት ወር እንደተፈረደበት ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ጋዜጣው እንደሚለው ግንቦት 3/2007 ዓ.ም ቄራ የመጀመሪያ ፍርድቤት የቀረበው አቶ ስንታየሁ ፖሊስ በሰልፉ ወቅት ድንጋይ ወርወሯል በሚል በቀረበበት ክስ የስድስት ወር እስር ተፈርዶበታል፡፡

አቶ ስንታየሁ መቃወሚያና የክስ ማቅለያ እንዲያቀርብ ተጠይቆ ‹‹የከሰሰኝ ኢህአዴግ ነው፡፡እየመሰከሩብኝ ያሉትም ኢህአዴጎች ናቸው፡፡የወሰነብኝም ኢህአዴግ ነው፡፡በመሆኑም ፍትህ አገኛለሁ ብዬ መቃወሚያም ማቅለያም አላቀርብም›› በሚል መቃወሚም ማቅለያም ሳያቀርብ ተፈርዶበታል።

ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መንግስት አይ. ኤስ. አይ. ኤስ ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ በመቃወም የጠራው ሰልፍ ላይ በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ሰልፉ ካበቃ ከሁለት ቀን በኋላ ከቤቱ ተይዞ የታሰረው የቀድሞው የአንድነትና አሁን የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየው ቸኮል ስድስት ወር ተፈረደበት፡፡
ዛሬ ግንቦት 3/2007 ዓ.ም ቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ ስንታየሁ ፖሊስ በሰልፉ ወቅት ድንጋይ ወርወሯል በሚል ባቀረበበት ክስ ምስክሮች ያሰማ ሲሆን የስድስት ወር እስር ተፈርሶበታል፡፡ አቶ ስንታየሁ መቃወሚያና የክስ ማቅለያ እንዲያቀርብ ተጠይቆ የነበር ቢሆንም ‹‹የከሰሰኝ ኢህአዴግ ነው፡፡ እየመሰከሩብኝ ያሉትም ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ የወሰነብኝም ኢህአዴግ ነው፡፡ በመሆኑም ፍትህ አገኛለሁ ብዬ መቃወሚያም ማቅለያም አላቀርብም›› በሚል መቃወሚም ማቅለያም ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ ይህን አቋሙን በጽሁፍ እንዲያቀርብ የተጠየቀው ስንታየሁ መቃወሚያም ሆነ ማቅለያ እንደሌለው በጽሁፍ አቅርቧል፡፡
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/6899#sthash.JEdv5OzQ.dpuf

0 comments:

Post a Comment