ጋዜጠኞችና ጦማሪያኑን የሚዳኙት የመሐል ዳኛ በራሳቸው ፈቃድ ከችሎቱ ራሳቸውን አገለሉ
ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ለ የካቲት 11 ተቀጠሩ፡፡ በ26/05/2007 ዓ.ም. የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ ይቀየሩልን ሲሉ በፅሁፍ ያቀረቡት አቤቱታ የግራና የቀኝ ደኛው ውድቅ ሲያደርጉት የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ በራሴ ፈቃድ ከችሎቱ እራሴን አንስቻለሁ ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ታዳሚ ገልፀዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሰባተኛ ተከሳሽ ጦማሪ አቤል ዋቤላ ትላንት ከፍርድ ቤት ወደ ማረሚያ ቤት በሚመለስበት ወቅት እጅህ በካቴና ለምን አልታሰረም ብለው የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች እጄን በውሻ ሰንሰለት አስረው አሳድረውኛል ብሎም ዛቻና ዘለፋ ደርሶብኛል እንደዲሁም ማአከላዊ ታስሬ እያለሁ በደረሰብኝ ድብደባ ጀሮዬ ላይ ጉዳት ስለደረሰ ለማደዳመጥ ጀሮዌ ላይ የማረገውን ድምፅ ማዳመጫ መሣሪያ በማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች ተነጥቂያለሁ ሲል እንባ በተናነቀው ንግግር ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ ተወካይ ለምን ይህ እንደተደረገ እና ያደረገውን ሰው በፅሁፍ እንዲያቀርብ ለየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም እንዲያቀርብ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ሦስቱ ጋዜጠኞች እና ስድስቱ ጦማሪያን ደኛው ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ አግባብ አይደለም ያለው ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ አንቀፅ 2519 መሠረት የ500 ብር ቅጣት ይቀጡ የነበረው በስሜታዊነት ነው በማለት መቀጫውን ውድቅ አድርጓል፡፡ በየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃል በአዲስ የመሀል ዳኛ መሠረት ይሰማል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡
Source:: Zehabesha
0 comments:
Post a Comment