
በላይ ማናዬ
‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ
ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ
ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››
ይህን
ያለው ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር ነጋን ካወኩት ወዲህ እንደዛሬ በኃይለ
ቃል ሲናገር ሰምቼው አላውቅም፤ ወይም ትዝ አይለኝም፡፡ ዛሬ (ህዳር 19/2007 ዓ.ም) እኩለ ቀን ላይ
እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሁሉ እንደማንኛውም ቀን አልነበረም፡፡ በር ላይ ስደርስ
በርከት ያሉ የአንድነት ፓርቲ...