(ኢ.ኤም.ኤፍ) በቅርቡ በአምስት ነጻ ፕሬሶች ላይ ከተመሰረተው ክስ ጋር በተያያዘ እስካሁን አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት መብቃታቸው ታወቀ። አቃቤ ህጉ በአዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አፍሮ ታይምስ እና እንቁ አዘጋጆች ላይ ክስ መመስረቱ የሚታወስ ነው። ጋዜጠኞችን በመክሰስ እና በማሰር በአሸባሪነት ሽፋን እስከ አስራ ስድስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት መፍረድን በነእስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርእዮት አለሙ ላይ የታየ እውነት ነው። አሁንም ሌሎች ጋዜጦች ላይ የሚደረገው ጫና እየበረታ እንጂ እየቀነሰ ባለመሄዱ ነው እነዚህ ጋዜጠኞች አገር ለቀው ለመሰደድ የበቁት።
እስካሁን ስማቸው የደረሰን ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው።
1-እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት አሳታሚ)
2-ኢብራሂም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ ምክትል ዋና አዘጋጅ)
3-እንዳለ ተሽ (አዲስ ጉዳይ ከፍተኛ አጋዘጅ)
4-ሃብታሙ ስዩም (አዲስ ጉዳይ አዘጋጅና አምደኛ)
5-ቶማስ አያሌው (አፍሮ ታይምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
6-አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሄት ሳታሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር
7-ግዛው ታዬ (ሎሚ መጽሄት አሳታሚ)
8-ሰናይ አባተ ቸርነት (ሎሚ መጽሄት ዋና አዘጋጅ)
9-ዳንኤል ድርሻ (ሎሚ መጽሄት ማኔጂንግ ኤዲተር)
10-አቦነሽ አበራ (ሎሚ መጽሄት ከፍተኛ ሪፖርተር)
11-ሰብለወንጌል መከተ (ሎሚ መጽሄት ናቸው)
ከአምስቱ ተከሳሽ ጋዜጠኞች መካከል እስካሁን ያልተሰደዱት የእንቁ መጽሄት አዘጋጆች ሲሆኑ፤ የመጽሄቱ አሳታሚ አለማየሁ ማህተመወርቅ አሁንም አገር ቤት ነው።
ከተሰደዱት ጋዜጠኞች መካከል በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ ቃል የሰጠችው አቦነሽ አበራ እንዲህ ብላን ነበር። (በነገራችሁ ላይ አቦነሽ አበራ የኢትኦጵ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረች፤ ከዚያም በ1997 ከመንገድ ተይዛ ተደብድባ እና ጽጉሯን ላጭተው ያሰሯት ሲሆን፤ በተለይም የኢሳት ጋዜጠኛ የሆነው ሲሳይ አጌና እህት በመሆኗ ምክንያት ጫና እንደበዛባት ነግራን ነበር) እንዲህ በማለት ነው ሁኔታውን የገለጸችው።
“ከዚህ በፊት የሆነውን ታውቃለህ። ያን ግዜ ጭንቅላቴ ላይ ባደረሱብኝ ድብደባ ምክንያት አሁንም ድረስ አንዳንዴ በራስ ምታት ህመም እሰቃያለሁ። ሰሞኑን በሎሚ መጽሄት ላይ የተደረገው ክስ ምክንያት ብታሰር እንደገና የሚፈቱኝ አይነት አይደሉም። ታስሬ መጸጸት ስለማልፈልግ ነው ከአገር ለመውጣት የወሰንኩት። በተለይም እንደምታውቀው ታላቅ ወንድሜ ሲሳይ አጌና ኢሳት ቴሌቪዥን ላይ ጋዜጠኛ ሆኖ ስለሚሰራ፤ ከዚህ በኋላ ካሰሩኝ ብዙ ሊያንገላቱኝ ይችላሉ።” በማለት ከገለጸችልን ከሁለት ቀና በኋላ ነው አገር ለቅቃ የወጣችው።
አሁን በነዚህ ጋዜጠኞች ላይ ክስ ተመስርቶ ከአገር ከመውጣታቸው በፊት፤ ባለፈው ወር ሃምሌ ሰባት ቀን የደህንነት ሃይሎች ወደ ቢሯቸው በመምጣት ቢሮውን እንዳሸጉት ይታወሳል። በወቅቱ ስለተፈጠረው ነገር የመጽሄቱ ዋና አዘጋጅ ሰናይ አባተ ያስተላለፈውን መልእክት በዚህ አጋጣሚ መግለጹ አስፈላጊ ስለሆነ እናካፍላቹህ።
ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ምከመንግስትበተላኩኃይሎችየ‹‹ሎሚ›› መጽሔትቢሮ ‹‹ያለንግድፍቃድ›› በሚልሠበብታሸገ፡፡እነዚህከየትኛውወገንእንደተላኩያልታወቁትኃይሎችበቢሮውስጥየነበሩትንየሂሳብሠነዶች ‹‹ይዘንእንሄዳለን፣አትሄዱም›› በሚልበተፈጠረውእሰጥአገባምክንያትስልክደውለውቁጥራቸውከ20 ያላነሱየታጠቁየፌደራልኃይሎችንበመጥራትእንዲሁምበድርጅቱውስጥየሚገኙትንንብረቶችናወረቀቶችንጨምሮእንዳናወጣበመከልከልናበማስፈራራትአስቀድመውታዘውይዘውትየመጡትወረቀት “ያልታደሰንግድፍቃድ” የሚልቢሆንም፣ንግድፍቃዱየታደሰበትንማጋገጫሲመለከቱደግሞፊትለፊታችንወረቀቱንበመሠረዝ “ያለንግድፍቃድ” በሚልጽፈውአሽገውታል፡፡በወቅቱሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ምለንባብየምትበቃው ‹‹ሎሚ›› መጽሔት ወደ ማተሚያ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለች ይህ ችግር መፈጠሩ በሎሚ አባላቶች ላይ ግርታ ቢፈጥርም፣ በተወሰደው ሕገ-ወጥ እርምጃ ሳንደናገጥ ከምንገባበት አንድቀን ዘግይተንም ቢሆን በተከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ማተሚያ ቤት ልናስገባ ችለናል፡፡ በወቅቱም ቢሮአችን እንደሚታሸግ ለምን አስቀድማችሁ በደብዳቤም ሆነ በስልክ አላሳወቃችሁንምቢባሉም ‹‹የእናንተ ስፔሻል ኬዝ ነው፤ እኛ ከላይ ታዘን ነው›› የሚል ምላሽ ሠጥተዋል፡፡
…እነዚሁ ኃይሎች ከመጀመሪያው ቀን በተለየ ሁኔታ በበነጋታው ተደራጅተው በመምጣት “ሠነዶችን እንፈልጋለን” በሚል ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፌደራል ኃይሎች የታገዘ የ5 ሠዓታት ፍተሻ (ከብርበራ አይተናነስም) ከአካሄዱ በኋላ በቢሮ ውስጥ የሚገኙትን የሂሳብ ሠነዶች በሙሉ ሰብስበው ወስደዋል፡፡ ሆኖም ግን የምንፈልገው የሂሳብ ሠነዶችን ይበሉ እንጂ፣ በቢሮው ውስጥ የሚገኙትን በተለያዩ ጊዜ የታተሙ የሎሚ መጽሔቶች፣ የአፍሮ ታይምስ ጋዜጦችና በእጅ ጽሁፍ የተተየቡ ወረቀቶችን አንድ በአንድ ሲፈትሹ ተስተውሏል፡፡
…እነዚሁ ኃይሎች ከመጀመሪያው ቀን በተለየ ሁኔታ በበነጋታው ተደራጅተው በመምጣት “ሠነዶችን እንፈልጋለን” በሚል ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፌደራል ኃይሎች የታገዘ የ5 ሠዓታት ፍተሻ (ከብርበራ አይተናነስም) ከአካሄዱ በኋላ በቢሮ ውስጥ የሚገኙትን የሂሳብ ሠነዶች በሙሉ ሰብስበው ወስደዋል፡፡ ሆኖም ግን የምንፈልገው የሂሳብ ሠነዶችን ይበሉ እንጂ፣ በቢሮው ውስጥ የሚገኙትን በተለያዩ ጊዜ የታተሙ የሎሚ መጽሔቶች፣ የአፍሮ ታይምስ ጋዜጦችና በእጅ ጽሁፍ የተተየቡ ወረቀቶችን አንድ በአንድ ሲፈትሹ ተስተውሏል፡፡
ይህ ከላይ የገለጽነው ተግባር የተፈጸመው ክስ ከመመሰረቱ አንድ ወር በፊት ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ሎሚ እና አፍሮ ታይምስ ጋዜጦችን ደጋግመው ሲኮንኑ እና ሲያጣጥሉ እንደነበር ይታወሳል። አሁን የተደረገውም ክስ እስካሁን ሲደረግ የነበረው ክትትል እና አፈና ውጤት ነው።
ከአገር ከወጡ በኋላ አሁን በስደት ላይ ሆነው መቸገራቸው የማይቀር በመሆኑ፤ የሎሚ መጽሄት አዘጋጅ የሆነው ሰናይ አባተ ቸርነት ለተሰደዱት ጋዜጠኞች ወገን አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው መልእክት አስተላልፎልናል። ጋዜጠኞቹን በቀጥታ በማግኘት አስፈላጊውን እርዳታ ማድረግ ለምትፈልጉ በድረ ገጻችን ኢሜይል media.emf@gmail.com መልክታችሁን ላኩልን ወይም በስልክ ቁጥር 678 437 5597 ደውሉልን።
0 comments:
Post a Comment