
ክብሮም ብርሃነ (መቐለ)
ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የአረና ትግራይ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አብርሃ ደስታ በሽብር ተጠርጥሮ በተከሰሰበት ልክ በወሩ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ በፌስ ቡክ አይቼ እኔም እንደ ዜጋና እንደ አድናቂው የሚቀርቡለትን የድራማ ክስ ለመስማት ጓጉቼ ፍ/ቤቱ ስደርስ እንደ እኔ አብርሃ ደስታን በአይናቸው ለማየትና የክሱን ድራማ ለማወቅ እንዲሁም ለቆራጡ ወጣት ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የሞራል ድጋፍ ለመስጠት የተሰባሰቡ የተለያዩ የክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲሁም የወጣቱ ፖለቲከኛ አድናቂዎች ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተደማምረው ያልገመትኩት የሕዝብ ብዛት በቡድን በቡድን ሰብሰብ ብለው የአብርሃ ቆራጥነትና...