እድሜ
ልክ ተፈርዶበትና ላለፉት ሰባት አመታት በወህኒ የሚገኘው አንዱአለም አራጌ በዘፈቀደና አለም አቀፍ ህግጋትን በጣሰ መልኩ የታሰረ ነው ሲል በአስቸኳይ እንዲፈታና ለደረሰበት ጉዳትም ካሳ እንዲከፈለው ጠየቀ፡፡
ይህ
ጥያቄ ፍሪደም ሃውስ በተባለ የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ለተመድ በቀረበ ጥያቄና በተመድ በተቋቋመ 5 አባላት ያሉት ያለአግባብ የተፈጸሙ እስሮችን በሚመረምር ኮሚቴ አማካኝነት ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ አንዱአለም ለእድሜ ልክ እስራት የበቃው መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት የሆነውን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ተጠቅሞ አገዛዙን በመተቸቱና የተበየነበት የእድሜ ልክ እስራት ገለልተኛና ነጻ ባልሆነ የፍርድ ሂደት በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈታና ለደረሰበትም ጉዳት ካሳ እንዲከፈለው በወሰነው ውሳኔ መሰረት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ
5 አባላት ያሉትና በተመድ የተቋቋመው ኮሚቴ በአቶ አንዱአለም አራጌ እስራት ላይ
የሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው ፍሪደም ሃውስ አዎንታዊ ውሳኔ ሲል አንዱአለም እራሱን በመሆኑ ይልቁንም ለፍትህ በመጮሁና አገዛዙን በመተቸቱ ብቻ በግፍ የታሰረ የዘፈቀደ እስረኛ ነው ሲል በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
አቶ
አንዱአለም አራጌ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር የነበረና የሁለት
ለጆች አባት ሲሆን በእስር በቆየበት ላለፉት ሰባት አመታት ‘ያልተሄደበት መንገድና የሀገር ፍቅር እዳ’ የተሰኙ ሁለት መጽሃፍት ደርሶ ለንባብ ያበቃ መሆኑ ይታወቃል፡፡
0 comments:
Post a Comment