
(በጌታቸው ሺፈራው)
በአማራ
ክልል በነበረው ህዝባዊ እምብይተኝነት ሰበብ የ"ሽብር ክስ" የተመሰረተባቸው እነ ንግስት ይርጋ ዓቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ማስረጃ መሰረት ይከላከሉ ወይም በነፃ ይሰናበቱ የሚለውን ለመበየን ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበር ቢሆንም ብይኑ አልተሰራም ተብሎ ብይኑን ለመስራት ለ3ኛ ጊዜ ለህዳር 1/2010 ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል።
1ኛ
ተከሳሽ ንግስት ይርጋ በስም ካስመዘገበቻቸው የቤተሰብ አባላት ውጭ እንዳትጠየቅ፣ እንዲሁም ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ባለው አንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ እንድትጠየው ገደብ የተጣለባት መሆኑን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቤቱታ አቅርባ እንደነበር ይታወሳል።
ሀምሌ
21/2009 ዓም በዋለው ችሎት ፍርድ ቤት በቤተሰብ፣...