Patriotic Ginbot 7
Chairman Professor Berhanu Nega speaking at Ethiopian National Movement public
meeting in Oslo, Norway.
...
Sunday, 30 July 2017
የፓርላማ አባላት በድንገት ከዕረፍት ተጠሩ
ዋዜማ
ራዲዮ- የሙስና ተጠርጣሪዎች ቁጥር
በየዕለቱ እያሻቀበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ለእረፍት የተበተኑ የፓርላማ አባላት በሚቀጥለው ሳምንት መጀመርያ ወደ መዲናው ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ በምክትል አፈጉባኤዋ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡
ፓርላማው
በዚህ ጥድፊያ ለምን እንደተጠራ ባይታወቅም ምናልባት ከሰሞኑ ያለመከሰስ መብቱ የሚነሳ ባለሥልጣን ይኖር ይሆን የሚለውን ግምት አጠናክሮታል፡፡ በሰኔ መጨረሻ የተበተነው ፓርላማ ለመጨረሻ ጊዜ የተመለከተው ጉዳይ ሰኔ 22 ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ይገባኛል የሚለውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ ሲሆን ‹‹በቂ የመወያያ ጊዜ ያስፈልጋል›› በሚል ጉዳዩን ወደ 2010 ማዛወሩ ይታወሳል፡፡
ፓርላማው
በመጪው ዓመት የመጀመርያ ወር የመጨረሻ ሳምንት ሥራውን እንደሚጀምር ቢታወቅም አሁን በፍጥነት እንዲሰበሰብ ጥሪ መደረጉ በርካታ መላምቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለምዶ አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት በእረፍት ጊዜያቸው ወደመረጣቸው...
Saturday, 29 July 2017
H. Res. 128, Supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia
On July 27, 2017, the full
House Foreign Affairs Committee voted to advance a resolution, authored by Rep.
Chris Smith (R-NJ), highlighting the human rights violations of the Ethiopian
government, and offering a blueprint to create a government better designed to
serve the interests of the Ethiopian people.
The resolution, which passed without objection, also calls on the U.S. government to implement Magnitsky Act sanctions, targeting the individuals within the Ethiopian government who are the cause of the horrific abuses.
The State Department’s...
የአቶ አባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ሳሌም ከበደ በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ (ዘ-ሐበሻ)
አቶ
አባይ ፀሐዬ የተለያዩ ጀኔራሎች ጋር በመደወል “ከዚህ ጉድ አድኑኝ” እያሉና ጫና ለማድረግ እየሞከሩ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል። እንደ እነሱ አገላለፅ፣ የሙስና ወንጀሉ አጣሪዎቹ አባይ ፀሃዬ በህግ እንዲጠየቅ የወሰኑ ቢሆንም የፓርላማ አባል በመሆኑና ያለመከሰስ መብቱ እስኪነሳ እየተጠበቀ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
“የቤት
ብርበራ ትእዛዝ የወጣበት ቢሆንም የፓርላማ አባል ነኝ ብሎ ለጊዜው አስቁሟል” በማለት ውስጥ አዋቂዎቹ ተናግረዋል፡፡ ጉዳዮ እስኪጣራ አቆየሁት እንጂ የውስጥ አዋቂዎቹ የአባይ ፀሐዬ ባለቤት ወ/ሮ ሣሌም ከበደ መታሰሯን የጠቆሙኝ በትላንትናው ዕለት ነበር፡፡ ይህን ሲሉኝ የሪፖርተር ጋዜጣ የወ/ሮ ሳሌም ከበደ ስምን አልተካተተም ነበር፡፡
ከተወሰነ
መዘግየት፥ ማዘግየት በኋላ ግን በድህረገፁ ላይ አካትቷል፡፡
ሪፖርተር
በሙስና ታሰሩ ብሎ ስማቸውን የዘረዘራቸው ሰዎች የሚከተሉት ናቸው
ከ1.1
ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ...
Wednesday, 26 July 2017
“ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም” ሌንጮ ለታ ከህብር ሬዲዮ-ሃብታሙ አሰፋ ጋር
<...ተቃዋሚዎች ራሳችንን
ማታለል የለብንም። በአስቸኳይ ከኢህአዴግ ተቃራኒ የሆነ ሀይል መፍጠር አለብን። እነሱ ስልጣን ላይ ሲወጡ ሁለት ስትራቴጂ ነድፈው ነው። ከቻሉ ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻሉ እስር በእርስ አጋጭተው አገሪቱን በትነው ወደ መጡበት መሄድ ነው። በአስቸኳይ አማራውም ሌላውም ብሄር የተወከለበት ...ሁል ጊዜ ከወያኔ የሚመጣ ነገር መጠራጠር አለብን። እነሱ በሚሰጡን አጀንዳ መነታረክ የለብንም የአዲስ አበባም ጉዳይ ቢሆን እነሱ አማራና ኦሮሞውን ለማጣላት ያመጡት ነው። ያ ባይሆን እና የተሻለ ነገር ቢያስቡ ኖሮ ከተማዋን ...>
አቶ
ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኦዴግ) ሊቀመንበርና የኢትዮጵአ አገራዊ ንቅናቄ ከፍተኛ
አመራር ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያድምጡት)
...
Friday, 14 July 2017
‹‹ለ12 ቀናት ቀዝቃዛ ባዶ ሲሚንቶ ወለል ላይ እንድተኛ ተደርጌያለሁ›› የኦፌኮ አመራር አቶ ደስታ ዲንቃ

ስም፡–
ደስታ ዲንቃ ጎሴ
ዕድሜ፡-
42 አመት
አድራሻ፡-
ኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ዙሪያ ዞን ሱሉልታ ወሰርቢ ቀበሌ
አሁን
በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ቂሊንጦ እስር ቤት
ለእስር
የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብር ተከስሼ (በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ህዝባዊ የመብት ጥያቄ ወቅት አመጽ አነሳስተሃል፣ አደራጅተሃል በሚል)
በይፋ
የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- በ25/09/08 ዓ.ም በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ቀርቦብኝ ጉዳየን እየተከታተልሁ ነው፡፡ አቃቤ ህግ የጸረ-ሽብር አዋጁን አንቀጽ 4 እና 3(1)/3(2)/3(4) እና 3(6)ን በመተላለፍ ክስ አቅርቦብኛል፡፡ በዚህም፣ በሌላ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ከቀረበባቸው እነ ጉርሜሳ አያኖ ጋር በመሆን ኦፌኮን እንደሽፋን በመጠቀም ከኦነግ...
የአቶ በቀለ ገርባ የሽብር ክስ ዉድቅ ተደረገ
በኦሮሞ
ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ከሽብር ጋር ተያይዞ የቀረበባቸዉ ክስ ውድቅ ተደረገ። ዛሬ ያስቻለው አራተኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ አቶ በቀለ የተከሰሱበት ጉዳይ በመደበኛ የወንጀል ክስ እንዲታይ መበየኑን ጠበቃ አመኃ መኮንን ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል።
በፀረ-ሽብር አዋጁ አንቀፅ 3 የሽብር ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፤ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላላም ክሳቸው በሽብርተኛ ቡድን ውስጥ መሳተፍ ወደሚል ተቀይሮ ተከላከሉ ተብለዋል። ከነዚህ ሌላ አምስት ተከሳሾች ሰባተኛ ዘጠነኛ ፤ አስረኛ አስራ ሦስተኛ ና 22ተኛ ተከሳሾች ምንም መከላከል ሳያስፈልጋቸዉ በነፃ እንዲሰናበቱ የሚል ዉሳኔ ተላልፎአል።
ቀሪ ተከሳሾች ከፀረ ሽብር ድርጅቶች ግንኙነት በማድረግና በመሳተፍ የሚል ሲሆን ይህንን የሚያስረዳ መረጃ በመኖሩ በዚሁ በቀረበባቸዉ ክስ እንዲከላከሉ መወሰኑን ችሎቱን...
«ማእከላዊ ውስጥ ሴትነቴን ተመስርተው ጥቃት ፈጽመውብኛል» አክቲቪስት ንግስት ይርጋ

በይፋ
የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- የሽብር ክስ ሲሆን (‹‹ህዝባዊ አመጾችን››) በማደራጀትና በሰልፎቹም በመሳተፍ ‹‹የሽብር ቡድኖችን ተልዕኮ በመቀበል ለማስፈጽም መንቀሳቀስ›› የሚል ነው፡፡ የተጠቀሰው የህግ ክፍል ደግሞ የጸረ-ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3፣ 4 እና 6 ላይ የተመለከቱትን ድርጊቶች በመተላለፍ ወንጀል ከሌሎች አምስት ሰዎች ጋር በአንደኛ ተከሳሽነት ነው የተከሰስሁት፡፡
የክስ
ሂደቱን የሚያየው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልድታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡
በእስር
በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡
1. በማዕከላዊ
ወንጀል ምርመራ እስር ቤት በቀዝቃዛና በጨለማ ክፍል ውስጥ ለረጅም ቀናት አስረውኛል፡፡
2. ያለማንም
ጠያቂ፣ ያለሁበት ሁኔታ...