Thursday 15 June 2017

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ አቀረበ

አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ይሰራ የነበረው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ 2003ዓም ሰኔ ወር ላይ ከሌሎች 4 ሰዎች ጋር (ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ ዘሪሁን /እግዚአብሄር እና ሂሩት ክፍሌ) የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን ተላልፈሃል ተብሎ ክስ ተመስርቶበት የነበረ መሆኑን እና 14 አመት የእስር ቅጣት እንደተወሰነበት የሚታወስ ነው።

ቅጣቱ ከተላለፈበት በኋላ ጥፋተኛ መባሉን በመቃወም ጠቅላይ /ቤት ይግባኝ ቢልም መዝገቡ በይቅርታ ጉዳይ እየታየ መሆኑ ተገልፆለት በወቅቱ ይግባኝ ማለት ሳይችል ቀርቷል። ከእርሱ ጋር የይቅርታ ጥያቄ ያቀረቡ የስዊድን ጋዜጠኞች እና በተመሳሳይ መዝገብ የምትገኘው ሂሩት ክፍሌ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፤ የጋዜጠኛ ውብሸት የይቅርታ ጉዳይ ግን እስካሁን ድረስ ተፈፃሚ አልሆነም።

በመሆኑም በቅርቡ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስረአት ህጉ አንቀፅ 191 ስር በተመለከተው መሰረት የይግባኝ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ ፈቃድ ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ በማስገባት ጠቅላይ /ቤት ይግባኙን አቅርቦ ነበር። የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርአት ህጉ አንቀፅ 196 (1) እና (2) የተፈረደባቸው ብዙ ሰዎች ሆነው አንዱ ብቻ ይግባኝ ያቀረበ እና የተጠቀመ [ከእርሱ ጋር አብራ የተከሰሰችው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ከጋዜጠኛ ውብሸት ጋር ተመሳሳይ የቀረበባት እነወዲሁም የስር /ቤት 14 ዓመት ከፈረደባት በኋላ በይግባኝ ወደ 5 አመት እንደተቀነሰላት ይታወቃል።] እንደሆነ ሌሎቹም ይግባኝ እንዳሉ እንደሚቆጠር እንደሚደነግግ በመጥቀስ ነው ይግባኙን ያቀረበው። ይግባኙን የተመለከተው ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኙን አቤቱታ ሳይቀበለው ውድቅ አድርጎበታል። ጋዜጠኛ ውብሸትም ይግባኝ ሰሚ ችሎት መሰረታዊ የህግ ስህተት በመጣስ ይግባኙን እንዳልተቀበለው በመግለፅ ያቀረበው አቤቱታ ዛሬ ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ነበር። ዳኞች ጉዳዩን መርምረው ብይኑን ሰኔ 12/2009 ቀን እንደሚያደርሱ እና ውሳኔውን ከመዝገብ ቤት ከማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ 2007 “የነፃነት ድምፆችእናሞጋች እውነቶችየተሰኙ መፅሐፍት ለንባብ ያበቃ ሲሆን በመጪው ሰኞ ሰኔ 12/2009 ቀን ከታሰረ 6ዓመት ይሞላዋል።


ምንጭ-  የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት

                                                                  ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ

0 comments:

Post a Comment