Monday, 5 June 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በታጋይ ዘመነ ካሴ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጡ

(-ሐበሻ)  የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአገር አድን ንቅናቄው ጋር በጋራ በቶሮንቶ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ሕዝባዊ ሰብሰባ ከሕዝብ ለሚነሳው የታጋይ ዘመነ ካሴ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጡ::

በማህበራዊ ድረገጾች በታጋይ ዘመነ ካሴ ጉዳይ የተለያዩ ነገሮች የሚወሩ ሲሆን ሕዝብም የተለያዩ መረጃዎችን በመስማት የትኛውን ማመን እንደሚችል ግራ እንደተጋባ ከሚሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ይቻላል:: ለዚህም ይመስላል ፕሮፌሰሩ አጽንኦት ሰጥተው የመለሱት::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ታጋይ ዘመነ ካሴ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ እና ቃል አቀባይ እንደነበር ገልጸው በመኪና አደጋና በተጨማሪም ኳስ ሲጫወት በደረሰበት ተደጋጋሚ ስብራቶች በአስመራ ህክምና ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል:: በአስመራ የሚደረግለት ህክምና በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ ታጋይ ዘመነ ወደ ውጭ ሄዶ ለመታከም ድርጅቱ እንዲያሰናብተው ለአርበኞች ግንቦት 7 መጠየቁን የገለጹት ፕሮፌሰሩበድርጅታችን በመተዳደሪያ ደንብ መሰረት ማንም ሰው ድርጅቱን መቀላቀልም ሆነ መልቀቅ መብቱ ስለሆነ ጥያቄውን ድርጅቱ ተቀብሎ መሉ ወጪውን በመሸፈን ከአስመራ መንግስት ጋር በመምከር ፓስፖርት እንዲሰጠው በማድረግ ልጁ ወደ ፈለገበት ሃገር እንዲወጣ ተደርጓልብለዋል::
በልዮ ኮማንዶ ከአስመራ ሙሉ ወጪውን ችለን አወጣነውየሚሉ ወገኖች በሶሻል ሚዲያ በሚደመጡበት በዚህ ወቅት ፕሮፌሰሩ ዘመነ የት ሃገር እንዳለ ቢያውቁም መናገር እንደማይፈልጉ ለታዳሚው ማብራሪያ ሰጥተዋል::

ለታጋይ ዘመነ ካሴ ህክምና የሚውል ገንዘብ ማሰባሰብ በጎፈንድሚ እየተደረገ መሆኑን -ሐበሻ መግለጿ አይዘነጋም:: ከወራት በፊት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ አበበ ቦጋለ በታጋይ ዘመነ ካሴ ዙሪያ ከሚኒሶታ ሕዝብ ለተጠየቁት ጥያቄ የመለሱትን ምላሽ -ሐበሻ በተንቀሳቃሽ ምስል አቅርባው ነበር::

0 comments:

Post a Comment