Thursday 8 June 2017

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ (ከመስከረም 28 2ዐዐ9 ዓ.ም) ጀምሮ በዜጎች ላይ የሚፈፀም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ ይቁም!



የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በዜጐች ላይ የተፈፀሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ይፋ አደረገ። ሰመጉ ሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2009 ባወጣው 142 ልዩ መግለጫው በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለይም በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች የተፈፀሙና ሰመጉ ምርመራ አከናውኖ በቂ መረጃ እና ማስረጃ ያሰባሰበባቸውን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፋ አድርጓል።

በዚህ ልዩ ሪፖርት በዜጐች ላይ የተፈፀሙ ህገወጥ ግድያዎች፣ ማቁሰል፣ድብደባ፣ ማሰቃየት፣ የጅምላ እስር እና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተካተዋል። ይህ 142ኛው ልዩ ሪፖርት በተጠቀሱት ክልሎች በሚገኙ 18 ዞኖች፣ 42 ወረዳዎች እና ክፍለ ከተሞች የተፈፀሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ብቻ የሚያካትት ነው። በልዩ ሪፖርቱ ማጠቃለያም ሰመጉ መንግስት ተገቢውን እውቅና፣ የመሥራት ነፃነት፣ ድጋፍና ጥበቃ እንዲያደርግለት ጠይቋል።

ሙሉውን ሪፖርት ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

0 comments:

Post a Comment