Sunday, 23 August 2015

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ የሰማያዊ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በድጋሜ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ ትናንት ነሀሴ 16/2007 ዓ.ም ጉባኤውን የጀመረው ፓርቲው በዛሬው ሁለተኛና የማጠቃለያ ውሎው የፓርቲውን ሊቀመንበር፣ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላት ምርጫን አድርጓል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በድጋሜ ለቀጣዩ ሦስት አመታት ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡ ሲሆን፣ አምስት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አባላትም በጉባኤው ተመርጠዋል፡፡ ጉባኤው የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም መርጧል፡፡  ለፓርቲው ሊቀመንበርነት ቀደም ብለው ፓርቲውን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ራሳቸውን...

Thursday, 20 August 2015

ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ነፃ እንዲለቀቁ ወሰነ

ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡  በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ ማቀድ ተግባረት›› ላይ መረጃ ስላልተገኘበት አንቀፁ ወደ 7/1 ላይ በተመለከተው ላይ ተቀይሮ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡ በዚህ አንቀፅ ለግንቦት ሰባት በመመልመል ተግባር ተሰማርቷል በሚል እንደተከሰሰም ተገልጾአል፡፡...

Wednesday, 19 August 2015

የዛሬው የዞን 9 ጦማሪያን የፍርድ ቤት ውሎ

በሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት) በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና አቤል ዋበላ በዛሬው ዕለት ‹ክሳቸውን መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ አያስፈልጋቸውም› በሚል የመጨረሻ ውሳኔውን ለመስማት በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር፡፡ በዕለቱ የተሰየመው ችሎት ‹‹ሰነዱ ሰፊ ነው ብዙ ማንበብ ይጠይቃል በዚህም ምክንያት ችሎቱ የክስ መዝገቡን አይቶ ባለመጨረሱ ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል» በማለት ቀጠሮው መተላለፉ በዳኛው የተነገረ ቢሆንም የፀረ ሽብር ክሶችን የሚያየው 19ኛ ወንጀል ችሎት ነሃሴ 15 ቀን ይዘጋል ተብሎ አስቀድሞ በዳኞች ተነግሮ የነበረ ቢሆንም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ለነሃሴ 18 የብይን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። 481 ቀናትን በእስር ያሳለፉት...

Tuesday, 18 August 2015

እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ግንቦት 7ን ለመቀላቀል መንቀሳቀሳቸውን አመኑ

እነ ብርሃኑ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ ‹‹ድርጊቱን ፈጽመናል፣ ጥፋተኞች ግን አይደለንም›› በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር   ከግራ ወደ ቀኝ – ፍቅረማርያም አስማማው፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ እና እየሩሳሌም ተስፋው የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን በማቋረጥ ኤርትራ ከሚገኘው ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀ የሽብር ቡድን ጋር ለመቀላቀል ሲጓዙ ድንበር አካባቢ ማይካድራ ላይ እንደተያዙ በመግለጽ በመንግስት የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡ ዛሬ ነሐሴ 11/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ ‹‹በክሱ...

Sunday, 16 August 2015

“አንገነጠልም – ትግላችን የኦሮሞ ሕዝብ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው” ብ/ ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ከአስመራ

ከሁለት ሳምንት በፊት አራት የኦነግ ድርጅቶች ወደ አንድ መምጣታቸውን ይህን ተከትሎ ከአውስትራሊያ የሚሰራጨው ሲቢኤስ ራድዮ ብ/ጄ ኃይሉ ጎንፋ፤ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር – ኦነግ (በአባ ነጋ ጃራ የሚመራው) ምክትል ሊቀ መንበር፤ ስለ ኦነግ ዳግም መሰባሰብ አነጋግሯቸዋል:: ጄነራሉ ተበታትነን ምንም አናመጣም ብለዋል:: “ኦነግ የሚለውን ስያሜ በባለቤትነት እኔ ነኝ ብሎ የሚወስደው ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል:: ያድምጡት:: ...

Thursday, 13 August 2015

የኤልያስ ገብሩ ቆይታ ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር (ዝዋይ እስር ቤት)

በኤልያስ ገብሩ ታገሉ! ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት) ተመስገን ደሳለኝ ስለሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድም ሀሳቡን ሰንዝሯል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቦሌ አካባቢ ብርዱ ጠንከር ያለ ነበር፡፡ ከቦሌ ብራስ ወደሚሊኒየም አዳራሽ በሚወስደው ቀጭን መንገድ ላይ ወንዱም ሴቱም በፍጥነት ይራመዳል፡፡ ከታክሲ በሁለቱም አቅጣጫዎች የወረዱ ሰዎች ወደመደበኛ ሥራቸው ለመግባት ብሎም የግል ጉዳያቸውን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበር – ከትናንት በስትያ ሰኞ (ነሐሴ 04 ቀን 2007 ዓ.ም) ጥዋት 1፡45 ሰዓት፡፡ እኔ እና ወዳጄ አቤል ዓለማየሁ ወደከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደሚገኘው ዝዋይ እስር ቤት አምርተን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን እና ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ...

Wednesday, 5 August 2015

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለ3ኛ ጊዜ አቶ አንዳርጋቸውን አላቀረበም

‹‹ቤተሰቦቼ አሸባሪ ተብለው ቤት የሚያከራያቸው አጥተዋል፤ ልጆቼ በረንዳ ላይ ወድቀዋል፤ ቤተሰባችን ተበትኗል›› ም/ኢንስፔክተር ሙልዬ ማናዬ ረታ (7ኛ ተከሳሽ) በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) ዋስ እንዲሆኑ ለዛሬ ሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የደረሰው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ፅጌና ፋሲል የኔዓለም...

Monday, 3 August 2015

በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተጠቀሱ 18 ተከሳሾች ከ22 እስ ከ 7 አመት ፈረደባቸው

22 አመት የተቀጡት ፍርድ ቤቱ በሽብር ወንጀሉ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው ያላቸው አቡበክር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ እና ከሚል ሸምሱ ናቸው ። ችሎቱ በመዝገቡ የተጠቀሱ 5ኛ፣ 7ኛ፣ 8ኛ፣ 11ኛ እና 15ኛ ተከሳሾችን፥ በድሩ ሁሴን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሃመድ አባተ፣ አቡበክር አለሙ እና ሙኒር ሁሴንን እያንዳንዳቸውን በ18 አመት ጽኑ እስራት ቀጥቷቸዋል ። ሼህ መከተ ሙሄ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ ሼህ ሰኢድ አሊ፣ ሙባረክ አደም እና ካሊድ ኢብራሂም የ15 አመት ጽኑ እስራት ተወስኖባቸዋል ። እንዲሁም ሙራድ ሽኩር፣ ኑሩ ቱርኪ፣ ሼህ ባህሩ ዑመር እና የሱፍ ጌታቸውን በ7 አመት ጽኑ እስራት ቀጥቷቸዋል ። ተከሳሾችም ይሁን ከሳሽ አቃቤ ህግ የቅጣት አስተያየት...