Friday 6 March 2015

አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ፤ ሰማያዊ ፓርቲ የሙዚቃ ስራውን እንዲጠቀም ፈቀደ

ከሁለት ወራት በኋላ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን “ምርጫ” ተከትሎ፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሚዲያዎች ላይ የቅስቀሳ ስራዎች እንዲያቀርቡ መባሉ ይታወቃል። ሆኖም ሰማያዊ ፓርቲ ሰሞኑን ለምርጫ ቅስቀሳ የተጠቀመበት ሙዚቃ፤ “የአርቲስቱን ፈቃደኝነት ስላላካተተ አይተላለፍም” ተብሎ ታግዷል። ዛሬ እንዳረጋገጥነው ከሆነ፤ የዘፈኑ ባለቤት ድምጻዊ ብርሃኑ ተዘራ ሰማያዊ ፓርቲ ሙዚቃውን እንዲጠቀም መፍቀዱን ገልጿል።

ድምጻዊ ብርሃኑ ተዘራ የተጫወተው ሙዚቃ ግጥም ከዚህ የሚከተለው ነው።


ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ (ኢብኮ) ለሰማያዊ ፓርቲ የላከው ደብዳቤ ነው።
ወገኔ ተው ስማኝ አገሬ
አንድነት ይበጀናል ዛሬ።
መቼም አይሻርም ኢትዮጵያዊነቱ
መኖር ግን አይሻም ያለ ነጻነቱ
እኮ ማነው ሰጪ፣ ማነውስ ከልካይ፤
ሰው እንዳሻው ቢሆን፣ በአገሩ ላይ።
አይደለም አየሩ፣ አይደለም ተራራው፤
ሲርብ የሚያበላው፣ አገር ማለት ሰው ነው።
ለሆዱ ያደረ፣ ወዳጁን የረሳ፤
ነጻነት ምኑ ነው፣ ቢነገር ቢረሳ።
አገሩን አይለቅም፣ መቼም ካልከፋው፤
የራሱ ካልደላው፣ የሰው የራስ ነው።
የልቡን መናገር፣ መኖር ሲያቅተው፤
ያኔ ነው፣ ባገሩ የተሰደደው።
….
አውጥቼ አውርጄ፣ በድፍን ጨረቃ፤
ኢትዮጵያዊነቴን፣ መርጫለሁ በቃ።

አዲሱን ነጠላ ዜማ አስመልክቶ ጃኪ ጎሲ፣ አብዮት እና ፋሲል ደሞዝ ከማጀብ ጀምሮ አስፈላጊውን ትብብር ሲያደርጉለት እንደቆዩ በመግለጽ ድምጻዊ ብርሃኑ ተዘራ አመስግኗቸዋል።
አዲስ የተለቀቀውን የነብርሃኑ ተዘራ ቪዲዮ ከዚህ በታች መከታተል ይችላሉ።

0 comments:

Post a Comment