Friday 27 March 2015

ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት ህወሓትን ከዱ



የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት፣ ኢህአዴግን መክዳታቸው ተሰማ። ወ/ሮ አበባ ኢህአዴግን የከዱት በቅርቡ ለስብሰባ በሄዱባት ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መሆኑ ታውቋል።

ወደ ሀገራቸው እንደማይመለሱና እዛው አሜሪካ ጥገኝነት እንደሚጠይቁ ቅርባቸው ለሆኑ ሰዎች እንደተናገሩ የሚነገርላቸው ወ/ሮ አበባ ገ/ህይወት፤ ከድርጅት ጉዳይ ኃላፊነታቸው በተጨማሪ በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች ላይ ኃላፊ እንደነበሩ ታውቋል። ግለሰብዋ ተደራራቢ ኃላፊነት የያዙት ከምርጫ ዘጠና ሰባት ወዲህ እንደሆነ ይነገራል።

የህወሓት የበላይነት ባንሰራፋበት በአሁኑ ጊዜ የተባሉትን ብቻ የሚያደርጉና ትዕዛዝ ፈጻሚ ባለሥልጣናት የሎሌነት ስራ እየዋለ ሲያድር እያንገፈገፋቸው ስለሚሄድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እራሳቸውን ለማውጣት አቆብቁበው እንደሚገኙ የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ። በአገር ውስጥ ያሉትና የመሰደድ ዕድል ያላገኙት የህወሓት ተፅዕኖ ያንገፈገፋቸው ባለሥልጣናትም ቢሆኑ የሥርዓቱን አስከፊነት የሚያመላክቱ መረጃዎችን ራሳቸውን በመደበቅ ይፋ እያወጡ እንደሆነ እነዚሁ የፖለቲካ ታዛቢዎች ጠቁመዋል።

0 comments:

Post a Comment