ላለፉት 24 አመታት በርካታ የመኢአድ አመራር አባላት እንደታሰሩ፣ እንደተገደሉ፣ እንደተሰደዱ የሚታወቅ ነው። በቅርቡ እንኳን የመኢአድ ም/ፕሬዘዳንት እና የስሜን ቀጠና ም/ሃላፊ አቶ ዘመነ ምህረት፣ የስሜእን ጎንደር የመኢአድ ሃልፊ መምህራ ጥጋቡ ሃብቴ መታሰራቸው ይታወቃል። ይህን በሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለሕዝብ መናገሩን ነው ፣ ኢቢሲ የስነ ምግባር ኮዱን መጣስ ነው በሚል እገዳ ያደረገበት።
የአንድነት ፓርቲን ሙሉ ለሙሉ ታግዲ ለተለጣፊው ቡድን የተሰጠ ሲሆን፣ ሰምያዊና መኢአድ ደግሞ አሁን እያየን እንዳለው ከሌሎች ፓርቲዎች በተለየ ጫና እየተደረገባቸው ነው።
በተያያዘ ዜናም በርካት የመኢአድ አመራሮች በምርጫው ላለመሳተፍ በግላቸው እየወሰኑ ሲሆን፣ በፓርቲ ደረጃም ተመሳሳይ ዉሳኔሊወሰድ ይችላል የሚል ግምት አለ።
0 comments:
Post a Comment