:::: MENU ::::

Tuesday, 21 October 2014

የዛሬው የፍርድ ቤት ቆይታ

የዛሬው የፍርድ ቤት ቆይታ

(ከዞን ዘጠኝ)

ኤዶም እና ማህሌት
ኤዶም እና ማህሌት

በዛሬው ዕለት በጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ እና በዞን ዘጠኝ ጦማሪት ማኅሌት ፋንታሁን የእስር ቤት አያያዝ ጉዳይ በተመለከተ በጠያቂዎቻቸው እና በራሳቸው ላይ የሚደርሰውን ወከባና ማሸማቀቅ፣ ከቤተሰብ ውጪ እና ካስመዘገቧቸው ሰዎች ውጪ እንዳይጠየቁ መከልከላቸውን እንዲሁም፤ በተጠርጣሪነት እያሉ በእስር ቤት ውስጥ አሸባሪ እያሉ የስም ማጥፋት እንደሚደርስባቸው በገለጹት መሰረት በተደጋጋሚ ማረሚያ ቤቱ ሃላፊ ለፍርድ ቤት መጥቶ እንዲያስረዳ ተጠይቆ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዛሬው እለት በነኤዶም የቀረቡትን ቅሬታዎችና በደሎች የማረሚያ ቤቱ ተወካይ የካዱ ሲሆን በፍርድ ቤት ውስጥ የነበሩትን እና በደሉ የደረሰባቸውን ጭምር ያበሳጨ መልስ ነበር፤ ዳኛው እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮችን በቸልታ እንደማይመለከትና በድጋሚ እንደዚህ አይነት ጥፋቶች እንዳይከሰቱ በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ በሰዓቱ ቀርበው የነበሩት በቂሊንጦ የሚገኙት ጦማሪንና ጋዜጠኞች በዘላለም ክብረት አማካኝነት መጽሃፍ እንዳይገባ መከልከሉን ተቃውመው ሃሳባቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበው የነበረ ቢሆንም ዳኛው የዛሬው ቀጠሮ በቃሊቲ ጉዳይ ብቻ በመሆኑ የነሱን ጉዳይ እንደማይመለከቱና ጉዳያቸው እንዲታይላቸው ከፈለጉ ማመልከት አንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በፎቶው ላይ ከፊት የሚታዩት ጋዜጠኛ ኤዶም እና ጦማሪት ማህሌት ሲሆኑ፤ ሌሎቹም የዞን ዘጠኝ ተከሳሾች ከነሱ ኋላ ይታያሉ














በፎቶው ላይ ከፊት የሚታዩት ጋዘጠኛ ኤዶም እና ጦማሪት ማህሌት ሲሆኑ፤ ሌሎቹም የዞን ዘጠኝ ተከሳሾች ከነሱ ኋላ ይታያሉ

0 comments:

Post a Comment