Wednesday, 5 March 2014

የማለዳ ወግ … ሰቆቃ መከራው የጠናበት የሳውዲ ስደተኛ …

* ኢትዮጵያ አየር መንገድና የግምሩክ ባለስልጣን በሳውዲው ስደተኛ ላይ ጣሉ
* ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ የሚሔዱ ዜጎች እንግልት ጋብ አላለም
በአለም ተበትኖ በስደት ከሚኖረው ከፍተኛ ቁጥር ካለው ኢትዮጵያዊ መካከል እንደ ሳውዲው ስደተኛ ከዚህም ከዚያ የሚቀጠቀጥ ፣ ከላይ ከታች ሰቆቃና መከራው የበዛ ስደተኛ ያለ አይመስልም ። ይህንን ያስባለኝ ከሳምንት በፊት በሳውዲ ሪያድና ጅዳ ሆነው ወደ ኢትዮጵያን ካርጎ የሚያመላል ሱ መስሪያ ቤቶች የተላለፈው ደብዳቤ ማናቸውም በሰማያዊ ፕላስቲክ በርሚል እና በተመሳሳይ እቃ መያዣዎቸ ተዘጋጅተው ሊላኩ የተዘጋጁትን ጨምሮ ወደፊት የሚልላኩ ያገለገሉ እቃዎችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደማይቀበል ይፋ አድርጓል።Nebiyu Sirak
ይህው የተሰራጨው ስለ እገዳው ዘርዘር ያለ መረጃ ሰጥቷል። ከሳውዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ እቃወችን በፍጥነት ለማጓጓዝና ለማድረስ እንዲረዳ በሚል በኢትዮጵያው አየር መንገድ የሳውዲ አረቢያ የመንና የኢራቅ ዋና ሃላፊ አቶ አብድልአዚዝ ስሩር የወጣው ማሳሰቢያ ኢትዮጰያውያን በሰማያዊ ፕላስቲክ በርሚል እና በተመሳሳይ እቃ መያዣዎቸ ተዘጋጅተው ሊላኩ የተዘጋጁትን ጨምሮ ወደፊት የሚልላኩ ያገለገሉ እቃዎችን እንደማይቀበል ያትታል። ደብዳቤው በማከልም አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ የደረሰበትን ምክንያት ሲያስረዳ በሚላኩ በጉምሩክ መስሪያ ቤቱ እቃዎች ሲከፈቱ በዝናብ የበሰበሱ እና በመሳሰሉት የተበላሹ አልባሳትና ያገለገሉ እቃዎች ሽታ ለጉምሩክ ሰራተኞች የአስም በሽታ ጠንቅ ከመሆናቸው ባለፈ አካባቢውን በአስከፊ ጠረን መበከላችው በምክንያትነት ያቀርባል። በአየር መንገዱ አርማ እና የሃላፊው ፊርማ ያረፈበት ይህው ድብዳቤው መልዕክቱን ሲደመድም በፕላስቲክ ኮንቴነር ያገለገሉ ልብሶችና ያገለገሉ ማናቸውንም የቤት መገልገያ ቁሳቁሶችን ከየካቲት 22 ቀን 2006 ወይም March 1, 2013 ጀምሮ እንደማይቀበል በጥብቅ አስታውቋል ።
ይህንኑ አስገራሚ ማሳሰቢያ ከሳምንት በፊት እንደደረሰኝ በካርጎዎች አካባቢ ስላለው ሁኔታና የካርጎ መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ያላቸውን አስተያየት ጨምሮ የነዋሪዎችን አስተያየት ለማሰባሰብ ሞከርኩ ። ርቄ ሳልሔድ አንድ ጎረቤቴ በዚህ ዙሪያ ያለውን አስተያየት ጥይቄው እንዲህ ነበር ያለኝ ” የሳውዲ ስደተኞች ሰቆቃ መከራው የሚደርስብን በሳውዲዎች አይደለም ። በሳውዲዎች ከሃገር ልቀቁ ከተባልን ጀምሮ እቃችን በካርጎ ለመላክ ካርጎ አስገባን ። ብዙም ሳይቆይ ካርጎ ተዘጋ። የተዘጋው ለአንድና ለሁለት ወር ቢሆን ጥሩ ነበር ። ለሰባት ወራት ተዘግቶ ከተከፈተ ወር ሁለት ወር አልደፈነም ። አንጋፋው አየር ምንገዳችን በራሱ ስህተት ካርጎውን ዘግቶ ከርሞ አሁን ደግሞ ያገለገለ እቃ አንቀበልም ይለናል። እኛ እኮ በደል እየደረሰብን ያለው በራሳችን መንግስት መስሪያ ቤቶችና ሹሞች እኮነው! ! … ” ሲል የሰጠኝን አስተያየት ይዠ በፕላስቲክ በርሚል እና በተለያዩ ያገለገሉ የተገፋው ስደተኛ እቃዎች ወደሚገኙባቸው ካርጎዎች አቅንቸ በእቃ ግምጃ ቤቶቻቸው የታጨቁትን እቃዎች ለመመልከትና የጉዳዩ ባለቤቶችን ለማነጋገር ሞክሬያለሁ ። …
በቀጣይ እናወጋዋለን !
ነቢዩ ሲራክ

0 comments:

Post a Comment