ዋሽንግተን ዲሲ— ወጣቱ ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “ከዐሜን ባሻገር” የተሰኘ መጽሐፉን እሁድ ጥር 22
ቀን 2008 ዓ.ም በሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ብላክ በርን ሴንተር አስመርቋል። ከምርቃት ዝግጁቱ በኋላ ለአሜሪካ ድምፅ
በሰጠው ቃለምልልስ፤ ስለመጽሐፉ ርእስ ስያሜ ተጥይቆ፤ "አሜን ብለን ስንቀበላቸው የቆየናቸው የታሪክ፣ አልፎ አልፎም
የፖለቲካ አስተያየቶች፣ ስለ አኗኗራችን በተቋሞች፣በትምሕርት ቤት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ወይም ደግሞ
መንግሥታዊ ባልሆኑ በተለያዩ ተቋሞች አማካኝነት የሚቀርቡልንን የተዛቡ አስተያየቶች ተደጋግመው ስለተነገሩ ብቻ
“አሜን” ብለን የተቀበልናችውን አስተያየቶች የሚሞግቱ መጣጥፎችን ለመጻፍ ነው የሞከርኩት፡፡ በዛ ምክንያት ነው
“ከዐሜን ባሻገር”ያልኩት" ብሏል፡፡
አያይዞም፤ "አሜን ብለን ከምንቀበላቸው እውነታ ባሻገር ያለው ምን ይመስላል? የሚለውን ለማሳየት የሞከርኩት፡፡ እነዚህን ሐሳቦች ልንሞግታቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም አብሮ መኖራችንን ይሸረሽሩታል፡፡ ለሕልውናችን አስጊ ናቸው፡፡ ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለዚህ እነሱን የሚሞግቱ ነገሮችን ለመጻፍ ሞክሬያለሁ፡፡ አውዳሚ የምላቸውን ሐሳቦች ለመፋለም ሞክሬያለሁ"ይላል፡፡

0 comments:
Post a Comment