ጥር 2/2008 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ ውሳኔ ከፓርቲው ተሰናብታችኋል በተባሉት እነ ዮናታን
ተስፋየ ላይ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ጥር 9/2008 ዓ.ም ውሳኔው የፓርቲውን ‹‹ሀሳብና እምነቶች የጣሰና
መሰረታዊ የክስ አቀራረብም ሆነ ውሳኔ አሰጣጥን አልተከተለም›› በሚል ውሳኔውን እንደማይቀበለው መግለጹ ደንብን
የሚጣረስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲትና
ምርመራ ኮሚሽን ጥር 12/2008 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ከህገ ወጥ ተግባሩ ይታቀብ ሲል
ገልጹዋል፡፡ በስነ ስርዓት ኮሚቴው ውሳኔ ቅር የተሰኘ አካል ካለ ይግባኝ ማለት እንደሚችል የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ይግባኝ ከቀረበለት የመመርመሩ ኃላፊነት የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን መሆኑን በመግለጽ፣ ስራ አስፈጻሚው የማይመለከተውን መግለጫ ሰጥቷል ሲል ተቃውሞውን ገልጹዋል፡፡
0 comments:
Post a Comment