
ምርጫውን ተከትሎ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ
ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ገልጾአል፡፡ ትናንት ሚያዝያ 21/ 2007 ዓ.ም በምስራቅ
ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ የሆነው አቶ ሳሙኤል አወቀ በደህንነቶች ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ኃላፊው
ገልጾአል፡፡ አቶ ሳሙኤል ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት ሁለት ደህንነቶች አፍነው
በመውሰድ ከሌሎች አራት ደህንነቶች ጋር በመሆን ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመውበታል፡፡ ደህንነቶች ‹‹እንፈልግሃለን!››
ብለው ከወሰዱት በኋላ ‹‹ለምን አርፈህ አትቀመጥም?›› እያሉ ድብደባ እንደፈፀሙበትም አቶ ሳሙኤል
ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ የደ/ጎ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢና...