Tuesday 21 April 2015

በአዲስ አበባ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፣ ሰልፈኛው በሊቢያ የኢትዮጵያውያንን መገደልና መንግስት ያሳየውን ቸልተኛነት በመቃወም ላይ ነው


በሊብያ አሸባሪዎች በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝና መንግስት ነኝ ባዩ ወያኔ ያሳየውን ቸልተኛነት ለመቃወም በአዲስ አበባ ህዝቡ ነቅሎ አደባባይ ወጥቷል።
ይሁንና ፖሊስ እንደተለመደው ሰልፉን ለመበተን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፣  ፖሊስ ሰልፈኛውን በዱላ መደብደብ ጀምሯል።
ሰልፉ ከፖሊሶቹ ቁጥጥር በላይ ሆኗል፣ በርካታ ህዝብ እየጮኸ እና እያለቀሰ ሰልፈኛውን መቀላቀሉን ቀጥሏል።
ሰልፈኞቹ ከሚያሰሙት መፈክሮች መካከል፣
 ‹ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የለም!››
‹‹መንግስት የሌለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው!››
‹‹የወንድሞቻችን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም!››
‹‹የወንድሞቻችን ደም ውሃ አይደለም!››
ሰልፈኛው በተለይ ወጣቱ በቁጭት ለሟቾቹ ትኩረት ያልሰጠው መንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰማ ነው!
‹‹ሌባ! ሌባ!ሌባ! ሌባ!ሌባ! ሌባ!››
ሰልፉ ቀጥሏል፣ ፖሊስ ሰዎች ሰልፈኛውን እንዳይቀላቀሉ ጥረት እያደረገ ነው።

0 comments:

Post a Comment