Monday 12 January 2015

በቂሊንጦ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ

10653596_722906117794325_2186365328621114192_n

በቂሊንጦ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ፡፡
በቂሊንጦ ከሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መሃል የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለአዲሱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ ድጋፋቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ በወህኒ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

አመራሮቹ ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኘው ለአቶ በላይ ፍቃዱ እውቅና ሰተው በሌላ በኩል በአንድነት ስም በተጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለተመረጡት የፓርቲው ሰዎች እውቅና መንፈጋቸውን ተከትሎ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከሃምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

0 comments:

Post a Comment