Thursday, 2 January 2014

ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ (ሄኖክ የሺጥላ)

ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ
ብቸኛው ልቤ ሰው  በመውደዴ
ነው  ያለው ኣረጋሃኝ ወራሽ ኣሁን እንደ ሱ ልፋትና ጥረት ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የት በደረሰ። ለነገሩ ይሄ ትውልድ የተሰራውን ሁሉ በመናድ : የተጣፈውን ሁሉ በመካድ ነው የሚታወቀው። እኔ እንኳ በዘመኔ ስንት ኣየሁ። ኣሁን ማን ይሙት ኣደይ ትርሃስ በፍራሽ መዋጥ ለሁለት ዕየከፈሉ ያጸኑት ሹሩባ የሚረሳ ሆኖ ነው “ቢዮንሴ ሄር ስታይለር ምናምን ምንምን በሚል ሰጋቱራ ሃገሩን ያጥለቀለቅነው።” እስኪ ኣሁን ምን ትውልድ ኣለ። ድሮ ቡና እንኩዋ እስከ ሶስተኛ ነበር የሚጠጣው፤ ኣሁን ግን ኢኮኖሚው በ ፲፩ ፐርሰንት ኣድጎ ቡና እንኩዋ የሚያቆመው ሰባተኛ ምናምን ላይ ነው።   
በውነት ፕሮፌሰር ኣልማርያም እንደሚሉት ይሄ ትውልድ ኣቦ ሸማኔ ሳይሆን ኣቦል ሸማኔ ነው። ኣያቶቻችን ለኣድዋ ጦርነት ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሲሉ፤ መለከት: ጥሩንባ ሲነፉ  ነው  ታሪክ የሚነግረን። ዛሬ ግን የመለከት እና የ እንቢልታ ሪሚክስ  በየ ስርጣ ስርጡ ሺሻ መንፋት ሆኖዋል ግብራችን። የሰሞኑ መፈክር ኪንግ ኣብደላ ሼም ኦን ዩ፤ ሼም ሼም ሼም፤ ነበር ኣይደል፤ ምነው ሺሻው ተረሳ ታዲያ፤  ኣጎቶቻችን  ባርነት ና  ውርደት ብቻ ሳይሆን ሱሰኝነቱንም ኣወረሱን።
እንግሊዚኣዊው  ጋዜጠኛ ና ጠሃፊ Grham Hancook The sign and the Seal ( The Quest for The Lost Arc of the Covenant)  በሚለው መጥሃፉ ላይ The Ethiopian slept a thousand years forgetting the world by whom they were forgotten by  ይ ላል :: በነገራችን ላይ የላይኛውን የኣነባበብ ዘዬ ( style ) ኣንድ ነገርን ኣስታወሰኝ :: ባንድ ወቅት በስድስት ኪሎ (university ) ያስተምሩ የነበሩ መምህር  ስለ ጆነፍ ኬንዲ ሞት ለተማሪዎቻቸው ሲያስተምሩ ( During the time and death of Jonneif Kennedy every body was shocken ) ኣሉ በዚህን ጊዜ ኣንድ የቅዱስ ዮሴፍ ተማሪ ሳቁን ለሞአቆጣጠር ሲታገል  ያስተዋሉ እኝሁ መምህር በነገሩ በስጨት ይሉና “ምን ያስቅሃል ሾካካ!!!” ኣሉ ኣሉ። እንግዲህ ያዙልኝ ሾክን ሾካካ ከሚለው ነው የመጣው ማለት ነው።እሺ ይሁን  ሾክንስ ከሾካካ ነው እንበል፤ ኣድርባይነት፤ ባንዳነት፤ ሆዳምነት፤ ታሪክ ሸቃይነት፤ እነዚህስ?  ኣንድ ወዳጄን በጣም በስጨት ብዬ ኣረ ባክህ እኔ ኣልገባኝም ይሄ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መናቅ ከየት የመጣ ባህል ነው ስለው፤ ፈገግ ብሎ በርግጠኝነት ከቻይና ኣይደለም፤ ከቻይና ቢሆን ይህን ሁሉ ዘመን ኣብሮን ኣይቆይም ነበር፤ ማናልባት ከጣልያን ይሆን እንዴ ኣለኝ ። ወይ ኢትዮጵይ፤ ልጆችሽ  ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም የሚለውን ዘፈን  በየ ስብሰባው እና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ደጋግመው በማቀንቀናቸው ዘፈኑ ራሱ ሰልችቶት ልጆቼ ሃያ ሶስት ኣመት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ተዘፈንኩላችሁ በሉ ኣሁን ሌላ ዘፈን ፈልጉ፤ እናንተን እንዳየሁዋችሁ ከሆነ ፤ እኔን እንደ ልደት ዘፈን በሻማ ከባችሁ ከማልቀስ ውጪ  ምንም የምታመጡ ኣይመስለኝም፤ እ ና ጡረታዬን ጠብቁልኝና እስኪ ደሞ ይቺ የቀረችው ጊዜዬን እፎይ ብዬ ልኑር ኣለ ኣሉታዲያ ምን ይዋጠን፤ ኣንቺም ዜሮ ዜሮ እንዳንል ዘፋኙ እንጀራው ላይ የቅንድብ ጠጉር ተገኝቶበት ገበያውን ገደለው፤ ምን ይበጀን፤ ምን ይሻለን።  ከማቀንቀን ውጪ ሌላ ነገር ለማድረግ ዛሬም በቅጡ የተዘጋጁ ኣይመስልም፤ በየ ዝግጅቱ ላይ ኣበው ኣባቶቻችንን በ ፩ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ከማሰብ ውጪ ሰምሮላቸው የተሻለ ነገር ሲያደርጉ ዛሬም ኣናይም።
ወደ ግራሃም ሃንኩክ ልመለስ…ኣዎ “ The Ethiopian Slept…. A 1000 years forgetting the world by whom they were forgotten by.”
( ይህንን ፈረንጅኛ በኣማርኛ ብናራምደው ወይም ወደ ኣማርኛ ብንቀዳው) ኢትዮጵያዊያኖች ኣለምን ረስተው ኣለምም እነሱን ረስታ ለሺ ኣመተታት ኣንቀላፉ)ማለት ይሆናል።  ታዲያ የዚህን ሰውዬ ኣባባል የነብይ ግብር ለመስጠት ኢስቲመስል ድረስ ዛሬ ሃገሪቱ ኣልጋ በኣልጋ ሆናላች። ኣዎ ለኢሃዲግ መራዡ ( ይቅርታ መራሹ መንግስት ኣልጋ ባልጋ) ከዚህ ካለሁበት ኣማሪካም ይሁን ከኣውሮጳና ከሩቅ ምስራቅ ሃገራት ለሳምንታት ተንፍሰው መምጣት ለሚፈልጉት  ኣቦ ሸማኔዎችም ኣልጋ በኣልጋ ።ኣንቺ ሃገር ያለው ዘፋኝ ማን ነበር። ማንስ ቢሆን ምን ዋጋ ኣለው።
ታላቁ የኢሃዲግ መንግስት ከሚከበርበትና ከሚወደስበት የቀለበት መንገድ በተጨማሪ (ግድቢ ኣደይ ሃዳስ (የእማማ  ሃዳስ ግድብ) ( ለመሃል ኣገር ሰው ይስማማ ዘንድ የህዳሴውን ግድብ እየተባለ የሚነገረውን  ሳይጨምር…) ከሚታወቅበት ኣንዱ እንቅልፍን ያለ ገደብ መፍቀዱ ነው።  በነገራችን ላይ ያባይ ቦንድ የብዙ ኣባወራዎችን ትዳር በማፍረሱ ያባይ ቦንብ የሚል ስም ሊሰጠው እንደሆነ ጥቃት ያደረሱትም ጥቃት የደረሰባቸውም እየተናገሩ ነው:: የዚህ ያባይ ቦንብ የሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑት ሰዋች እንደሚሉት ከሆነ ኣማሪካ ቢሆን disability  ክሌም ኣርገን እንደ ኣካፋ ዝቆ በሚያነሳ ኣውቶብስ ፈልሰስ እያልን እንኖር ነበር፤  እኛ ግን ከጥቃታችን ሳናገግም፤ ተገድቦ የት ያደርሰናል ያልነው ኣባይ ጉሮሮዋችንን ገድቦ ይስረቀረቃል ብለዋል። ለነገሩ ኣባይ ኣፍ የለውም እንጂ ቢጠይቁት የደደቢት ድርዬዎች ሃንግ ኣረጉኝ ብሎ ለኣውሽና ቦርከና ይናገር ነበር። ምን ያረጋል ታዲያ ኣባይ እንኩዋን ኣፍ ማደሪያ የለውም። ኣባይ በስምሽ ስንት ታሪክ ተሰራ። ትገርሚያለሽ፤ በቃ ግንዱ ኣልበቃ ብሎሽ የዲያስቦራን ዶላር ትጠርጊ ጀመር፤ ለነገሩ ኣንቺ ምን ታረጊ፤ ሆዶ ነው ቁም ነገረኛ ያረገሽ እዚህ ዛሬ ከኛ ጋ ተቃውሞ ማታ ደሞ እትዮጵያ ደውሎ፤ እንዴት ነው ቦንዱ፤ ግድቡ እያለቀ ነው፤ ምን ይጠበቅብኛል ጌቶች የሚለው፤ ይሄ ሁለት ቢላ ህዝብ ኣባይዬ በናትህ በጣና ይሁንብህ፤ ይህንንማ ውስክስክ ላፍልኝ፤ መቅኖ ኣስቀረው፤ ኣላርፍ ያለ ዲያስፖራ ያባይ ቦንድ ይገዛል ኣሉ።
የጎጃም ገበሬ እንኩዋ  ዛሬ ቦንድ ካልገዛህ ኣባይ ኣጠገብ ዋንሽን መንፋት ኣትችልም ሊባል እንደሆነ ሰምቼኣለሁ፤ ዋሽንቱስ ይሁን፤ ቢያንስ ውሃ ሽንት ይፍቀዱላቸው።
በኣባይ ቦንድ መሸወዳቸው የገባቸው ኣንዳንድ ግለሰቦች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው  ሲናገሩ እንደሰማነው ከሆነ “ቦምብን በቦንድ ስምስም መንግስት ሲያስታጥቀን ዝም ብሎ የተመለከተው ሰማያዊ ፓርቲ ይጠየቅልን ብለዋል።”   ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው መንግስትም ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ኣፍራሽ ድርጊቱ ካልተቆተበ ኣሸባሪ ተብሎ   ከነ ግንቦት ሰባትና መሰል ድርጅቶች ተርታ ሊፈረጅ እንደሚችል ኣስምሮበት ኣልፉዋል ይልቁንም ሰማያዊ ፓርቲ በኣባይ ቦንድ እና በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ ኣስተያየት ከመስጠት ታቅቦ፤ ልማታዊ ጉዳዮች ላይ ቢያተኩር በማለት የመንግስት ቃል ኣቀባይ የሆኑት ኣቶ ኣከሌ ተናግረዋል ( ኣከሌ ያልኩበት ምክንያት ከመለስ ሞት ወዲህ ሰው ኣጥፊ ብቻ ሳይሆን ኣላፊና ጠፊ እንደህነ ስለተረዳሁ ነው)፤ ኣያይዘውም ሰማያዊ ስሙ ከኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ጋም የተያያዘ ስለሆነ፤ የህገመንገስት የበላይነት እና የእምነት እኩልነት በሰፈነበት ሃገር ፓርቲያቸው ኢሃዲግ እንዲህ ኣይነት መድሎ ስለማይቀበል፤ ሰማያዊ በሚለው ላይ ተቀጽላ ጨምሮ ( ሰማያዊ ኣል ረካት) ብሎ እንዲያስተካክለው ኢናሳስባለን፤ ይህ ባይሆን ግን ፤ ህገ መንግስቱ በሚፈቀደው መሰረት፤ ህጋዊ እርምጃ እንደምንወስድ እናሳስባለን። ።  በነገረችን ላይ ይሄ የኣሸባሪነት ህግ ከመጠን በላይ መናፈስ በጀመረበት ዘመን የልጅ ልጃቸውን ማየት የቻሉ ኣያት፤ ልጃቸው እማ ልጄን ማን ልበልው ብላ ለጠየቀቻቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፤ ማንስ ብትይው ምን ዋጋ ኣለው፤  ገና ሳይወልድ እኮ ነው መንግስት ስም ያወጣለት፤ ስለዚህ ኣድጎ ግራ ከሚገባው ኣንድ ፊቱን ኣሸብር በይው ኣሉዋት። ኣረ እቴ፦
በነገራችን ላይ የጎጃም ገበሬ ነው ኣሉ፤ ስለ ኣዲሱ የ ኣደይ ሃዳስ ግድብ  ወይም ህዳሴ ግድብ ከጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፤ እናንተ የኢትዮጵያን ባህልና ወግ ለመናድ ስትታገሉ፤ ኣባይ ደሞ የኣማራ ኣፈርን ሲንድ፤ ነው የማወቀው፤ እንግዲህ ዛሬ ኣባይ ከዚህ ጸያፍ ድርጊቱ ታቅቦ፤ እንደ ሴተኛ ኣዳሪ እዚህም እዚያም ከማስካካት እናንተ ባበጃችሁለት ቦይ ለመንዶልዶል መወሰኑ ጥሩ ጅምር ነው፤ ዋናው ቁም ነገር ግን መንግስት ከዚህ ግድብ ምን ይማራል ነው፤ ይህ የሺህ ኣመት ቦዘኔ፤ ጨርቄን ማቄን ሳይል፤ ጉዋዙን ጠቅሎ  እዚሁ የተፈጠረበት ሃገር ለመስተር መሞከሩ፤ መንግስትን ምን ያስተምረዋል፤ የገዛ ሃገራቸውን ኣንጡራ ሃብት ለባ፤ኣዳን የሚቸበችቡ ኣሻጥረኞች ከዚህ ምን ይማራሉ ነው። ብሎ ኣስተያየቱን ሰትቶ ኣልፎዋል።
ሲታረስ ሳያምር ሲታጨድ ሳያምር
ዋራን ኣሳመረው የድንጋይ ቤት ክምር
ያለው ማን ነበር
ሲነገር ሳያምር ሲወራ ሳያምር
ደለል ሻኛ ሆነው የጭቃ ቤት ክምር
ብለን ለኣባይ መሳ ግጥም ገጥመን እንለፋ።
እና ስለ እንቅልፍ ተመልሰን እናውራ….
እናላችሁ  መተኛት ለሚፈልግ ከምግብና መጠጥ ሌላ ሁሉም ይሞዋላለታል። እንኩዋን ሰዉ ዛፍ እንኩዋ እንቅልፍ ለምዱዋል። መወዛወዝ የል፤ ቅርንጫፍ ማፋጨት የለ፤ ዘነበ ኣልዘነብ የለ፤ ከሰው ጉንጭ ውስጥ ገብቶ ለጥ። ማ ወንድ ነው የዘንድሮን ዛፍ የሚቀሰቅሰው። ስሙስ ቢሆን ኣሱም እንደ ቢዮንሴ ሄር ስታይለር …ተቀይሮ። ድሮ ኣባቶቻችን ሰለ ዛፍ ሲያወሩ፤ ዝግባ፤ ዋንዛ፤ ቀርቀሮ፤ ጥድ፤ የባህር ዛፍ፤ ወይራ፤ ኣር ስንቱ፤ የዘንድሮ ዛፍ ለስለስ ያለ ስም ነው ያለው፤ ለስለስ ያለ እጅም ነው የሚይዘው። የዘንድሮ ዛፍ ምንጣፍ ተነጥፎለት ነው ቤት የሚገባው እንጂ በኣህያ ጀርባ ተጭኖም ኣይደል። ከትግራይ ውጭ በኣራቱም ማእዘናት ይበላል፤ ኣወዳይ ወይም በፈረንጅኛው  ( I will die)
ገለምሶ፤ በለጬ ፤ ጉራጌ ገለመኔ ነው ስሙ። የዚህ የእንቅልፋም  ትውልድ ቀርቀሮና ዝግባ።  ይሄ ትውልድ በእውነትም እንቅልፋም ነው።
ደጉ መንግስቴ በክርስትና ስሙ ( የዘመናት ብሶት የወረሰው፤ ወይም የወረረው)  ( በዳቦ ስሙ ባለ ራኦዩ መንግስቴ)…  የኣቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ኣፍርሶ (ነቅሎ)፤ ቁልቁል ሲንደረደር በተኛበት ቤቱ የፈረሰበት ሰው ነው ኣሉ እንዴ ይሄ ባቡር ሳይገባ ገጭቶ የጨረሰን ሲገባ ምን ልንሆን ነው ኣለ ኣሉ። ሲገባማ ምን ችግር ኣለው፤ ያባልነት መታወቂያ ከያዝክ እንቅልፍህን ትራንሰፈር ታደርገው ዘንድ በርህ ላይ ቆሜ እየጠበቑ ነው የሚል ኣይመስልሕም።
ባለ ራአይ ስል…. የቀድሞ የሳውዝ ኣፍሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኔልሰን ማንዴላን የቀብር ስነ ስርኣት በተሌቪዥን ሲከታተል የነበረ  ኣንድ ታጋይ (በሃደግ)ለማንዴላ እንደኛ ባለ ሯዩ መሪ የጎዳና ተዳዳሪዎችና ሴተኛ ኣዳሪዎች ያላለቁሱለት ለምንድን ነው ኣለ ኣሉ። ስላልወለዳቸው እናም ስላላገባቸው ልበልህ። ምን ልበል እኛ በህግ የተመዘገበ፤  ህገ መንግሱ የሚያውቃት ልጃቸው ቢሊየነሩዋን ሰማኸል መለስን ነበር፤ ታዲያ ጆቢራው ሲሞት ባንዴ (ባሌ ባሌ፥ ኣባቴ ኣባቴ ባዩ መብዛቱ) ድሮም  ሾፌርና   የእንትን ወንድ ይሉ ነበር ዘመዶቼ::
ማን ነበር ሎዚች ጦላ ሎጦሞቆ ሴት ሙተኛት ነበር ያለው። ኣይ ሃገር፤ ቡና ቤት ኣረጉሽ፤ ኣይ ትውልድ ቁመን ኣየንሽ።
ሲታረስ ሳያምር ሲታጨድ ሳያምር
ዋራን ኣሳመረው የድንጋይ ቤት ክምር
ያለው ማን ነበር
ሲፈጥረው ሳያምር
ሲገለው ሳያምር
ክ ፋት ግብር ሆነው የደደቢት ንስር።
ብዬ ለኣባባ መልስ እኔ ወዲ ሃድጊው  በጎዳ ልጆች ስም ግጥም ባበረክትስ።
ቸር ይግጠመን

0 comments:

Post a Comment