
አውራምባ
ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ይሰራ የነበረው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በ2003ዓም ሰኔ ወር ላይ ከሌሎች 4 ሰዎች ጋር (ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር እና ሂሩት ክፍሌ) የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን ተላልፈሃል ተብሎ ክስ ተመስርቶበት የነበረ መሆኑን እና የ14 አመት የእስር ቅጣት እንደተወሰነበት የሚታወስ ነው።
ቅጣቱ
ከተላለፈበት በኋላ ጥፋተኛ መባሉን በመቃወም ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢልም መዝገቡ በይቅርታ ጉዳይ እየታየ መሆኑ ተገልፆለት በወቅቱ ይግባኝ ማለት ሳይችል ቀርቷል። ከእርሱ ጋር የይቅርታ ጥያቄ ያቀረቡ የስዊድን ጋዜጠኞች እና በተመሳሳይ መዝገብ የምትገኘው ሂሩት ክፍሌ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፤ የጋዜጠኛ ውብሸት የይቅርታ ጉዳይ ግን እስካሁን ድረስ...