
አቶ በቀለ ገርባ የ እስር ጊዜያቸውን ጨርሰው መፈታታቸው ተሰማ:: አቶ በቀለ ዛሬ ተፈተው እቤታቸው ከገቡ በኋላም እንደገና ደህንነቶች “ያልተጣራ ነገር” አለ ብለው
እንደገና ወስደው ለሰዓታት ካሰሯቸው በኋላ መልሰው ሞጆ ላይ ለቀዋቸዋል::
የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ “የአቶ በቀለ አፈታት ድራማ” በሚል በዘገበው ዘገባው ላይ የሚከተለውን ጽፏል::
*ዛሬ መጋቢት 21 2007 ዓም አቶ በቀለ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚፈቱበት ቀን ነው።
*ጠዋት ላይ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀናን ጨምሮ የአቶ በቀለ መፈታትን ለማየት ወደ ዝዋይ እስር ቤት አቀኑ
*አቶ በቀለ ተፈቱ:: ቤተሰባቸውን በእቅፋቸው አድርገው በደስታ እንባ ታጅበው መነፋፈቃቸውን ገለጹ። ከዚያ ጉዞ ወደ ቤት…
*በድንገት የህወሓት...