
(ይሄይስ አእምሮ፣ ከአዲስ አበባ)
ከጥቂት ሣምንታት ወዲህ በተለይ የኢትዮጵያን የወያኔ መንግሥት በሚቃወሙ የሚዲያ ማዕከላት ዘንድ ዋና መነጋገሪያ ሆኖ የሚገኘው በሳዑዲ የኢትዮጵያውያን መንገላታትና መሰቃየት እንዲሁም ከኢሰብኣዊነትም በወረደ ሁኔታ በግፍ መጨፍጨፍ ነው፡፡ ዜጎቻችን በአካፑልኮ ቤይ የመዝናኛ ሥፍራ ሲንሸራሸሩ ከርመው የመጡ ይመስል ይህ ምስል በኢትዮጵያው የወያኔ ሚዲያ በአስደሳች መልክ እየቀረበ ቢሆንም ትክክለኛውን መረጃ ከአማራጭ የዜና ምንጮች እንደወረደ እንደምንከታተለው ከሆነ ግን ከሀገርና ከሕዝብ ኅልውና አኳያ ነገሩ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ከአንድ ጨለማ ውስጥ ብርሃን እንደሚጸነስ ሁሉ ከዚህ አስከፊ ገጠመኝ ውስጥ የፈነጠቀው የሕዝብ አንድነት ግን በሌላ ወገን ተስፋችን እንዲያንሠራራ አድርጓል፡፡...