Tuesday, 9 August 2016

Huge protest in Washington DC against the regime in Ethiopia

Ethiopians in the United States staged huge protest in the capital Washington DC. Protesters denounced the killing of peaceful protesters in Ethiopia by the regime forces and they extend unwavering solidarity to the Ethiopian people struggle for freedom. August 9, 2016

Monday, 8 August 2016

Sunday, 7 August 2016

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የመጨረሻዉን ጦርነት በጎንደር ህዝብ ልይ ከፈተ! (ጎንደር ሕብረት)


አጥፍቶ ለመጥፋት በጭፍን የሚጓዘዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር፤ የመቃብር ጉድጓዱን በጎንደር በመቆፈር ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያን ህዝብ ላይ ጦርነት መክፈት ሃላፊነት የጎደለዉ የእልቂት ዘመቻ ነው። እንደ ኢትዮጵያዊነት፤ ስህተትን ቆሞ ከማሰብ ይልቅ፤ ሥራዓቱን መሸከም ያንገፈገፈውን ሕዝብ በጥይት መረፍረፍ፤ የራሱን ዘረኛ ስርዓት ዉድቀት ከማፋጠን ሌላ አንድም የሚፈይደዉ ነገር የለም። በታሪክ እንዳየነው፤ ህዝባዊ መዓበልን የሚያቆመው ምንም ኃይል እንደሌለ ሁሉ፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ያለ ጥርጥር ያሸንፋል። ሃላፊነት የጎደለዉ ዘራፊዉ ወያኔ ከ800,000 በላይ የጎንደር ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ወደ ትግራይ በጉልበት የተከለለውን የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የጎንደር መሬት እና የህዝቡንም የአማራ ማንነት አስቸኳ ምላሽ እንዲያገኝ ጠይቆ፤ በስርዓቱ ላይ ያለዉን ጠንካራ ተቃዉሞ ባሰማ ማግስት፤ የአገር መሪ ነዉ ተብሎ ለይስሙላ የተቀመጠዉ ጠቅላይ ሚኒሲተር፤ የሚሊዮን ህዝብ ጥያቄ ዋጋ የለዉም ብሎ በወያኔ ተገዶ ሲናገር፤ መንግስት እንደሌለ ይፋ ማረጋገጫ ሆኗል።

 ዛሬ በጎንደር ህዝብ ላይ የተከፈተዉ፤ ጦርነት በትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የተቀነባበረ፤ በምድርም ሆነ በአየርም ጥቃት ሰንዝሮ የህዝብ ወገን የሆነዉን ኮሎኔል ደመቀን አፍኖ ለመዉሰድ ሌተ እና ቀን ሲሳራ የዋለ ያደረው መሰሪ ተንኮል ውጤት ነው። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ፤ የጎንደሬው ብቻ ሳይሆን፤ የወልቃይት ጠገዴን መሬት ጎንደሬነት፤ ሕዝቡም አማራ መሆኑን መሰረት አድርጎ ጠንክሮ የታገለ እና ትግሉን የመራ፤ የማንነት ምሳሌ የሆነ ቆራጥ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ነው። በመሆኑም፤ ይህን ጀግና፤ ለወያኔ አሳልፎ ላለመስጠት የሚደረገውን ግብግብ፤ የጎንደሬው ብቻ መስሎ የሚታየው ዜጋ ካለ፤ ነገም በአገሪቱ ያሉትን ጀግኖቻችን፤ እየተነጣጠልን አሳልፈን ልንሰጣቸው እንደምንችል ለወያኔ የልብ ልብ መሥጠት መሆኑን ተገንዘበን፤ ትግሉን ከጫፍ እስከ ጫፍ አቀጣጥለን፤ የወያኔን ፍፃሜ እንድናውጅ ጥሪያችን እናቀርባለን።

በመጨረሻም፤ ንብረት ማውደም፤ ድልድይ ማፍረስ፤ የአገራችንን ቋሚ ንብረቶች ማውደም የወያኔ ቋሚ ባህሪ እንጂ፤ የጨዋው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህሪ አይደለም! በመሆኑም በየትኛውም አገራችን ዙሪያ ትግሉን የምትመሩ ድርጅቶችም ሆነ ሰልፉን አቀነባባሪ ኮሚቴዎች፤ የወያኔን እና ደጋፊዎቹን ንብረት፤ ከጊዚያዊ አገልግሎት ውጭ ማድረግ እንጂ፤ ቋሚ ውድመት ማድረስ፤ ወያኔ ሲያልፍ ለአገራችን እና ለሕዝባችን በቀጣይነት አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለውን መሰረት መናድ ነው እና ጥንቃቄ ይደረግበት ዘንድ እናሳስባለን።


ወቅታዊ መፈክሮቻችን!!

1. መለዮ ለባሾች ሆይ! የበሰበሰውን ከፋፋይ ሥራዓት ለማስቀጠል ወንድሞቻችሁን መጨፍጨፋችሁን አቅማችሁ፤ ወደ ካምፓችሁ ተመለሱ!! ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ኮኔረል ደመቀና ታፍነዉ የተወሰዱ የኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ!

2. በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እነ አንዷለም አራጌ እነ በቀለ ገርባ እና የሃይማኖት አባቶች ባስቸኳይ ይፈቱ!

3. በጾረና፤ በሱማሌ፤ በሱዳን የሰፈረዉ የሰራዊት ደሞዙ በአብዛኛ ወራት ሳይከፈለዉ የቆየዉ ገንዘብ በአስቸኳ ተጠቃሎ ይከፈለዉ!

4. 60 በላይ የታሰሩ፤ የቅማንት ማንነት አስከባሪ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ ይፈቱ!!

5. የአማራና ኦሮሞ የትግራይ ያልሆኑ መለዮ ለባሽ ሰራዊት አባላትን በአፈና አስሮ የማሰቃየት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!

6. በአማራ ክልል የታሰሩ 180,000 እስረኞችና በአለፉት ስድስት ወራት 10,000 በላይ የታሰሩ የኦሮሞ ወንድም እና እህቶቻችን ያለምንም ቅደመ ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ!

7. ሕዝባዊ እንቅስቃሴዉ በሰፊዉ ለወያኔ ፋታ ሳይሰጥ በየቀኑ እና በተከታታይ ያለምንም ማቋረጥ ይቀጥል!

8. ከህዝብ አብራክ የወጣዉ ሰራዊት የህዝብ አጋር ሁኖ በመቆም የህዝብ የበላይነትን ያረጋግጥ!

9. የሰባቱ የጎንደር አዉራጃ የታጠቀ የህዝብ ሃይል ጎንደር ከተማን በሃላፊነት ይቆጣጠር!

መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጾታ ሃይማኖት እድሜ ሳይለይ ያለዉን ሁሉ ለለዉጥ የቆመዉን ሃይል በመመገብ፤ በማጠጣት እንዲሁም አስፈላጊዉን ሁሉ በማቅረብ የትግሉ ተሳታፊ እንዲሆን ከልብ የመነጨ ጥሪያችን እናቀርባለን!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ጎንደር ሕብረት

Saturday, 6 August 2016

Protests in more than 200 cities in Oromia, Ethiopia

The following video footage contains protests from only four cities in Oromia region, more than 200 protests are underway in different cities including Addis Ababa, Ethiopia.

The regime forces are firing live bullets against peaceful protesters, so far more than 50 casualties are reported. It could be far more by the end of the day according to activists.

The regime in Ethiopia also reportedly shuts down social media and internet services in most cities.

Friday, 5 August 2016

እነ በቀለ ገርባ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተድርጓል


*‹‹ይህ ህገ መንግስት በሦስት ዳኞች ውሳኔ አይፈርስም፤ ህገ መንግስቱ የኔም ነው፡፡ የመጠበቅ ኃላፊነት አለብኝ›› በቀለ ገርባ

በኦሮሚያ ክልል ከተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ለእስር ተዳርገው የሽብር ክስ የቀረበባቸው የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ተከሳሾች ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተድርጓል፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሐምሌ 29/2008 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ግንቦት 26/2008 ዓ.ም ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ የተሰጠውን ብይን በንባብ ያሰማ ሲሆን፣ መቃወሚያቸው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ሆኗል፡፡

ተከሳሾቹ በመቃወሚያቸው ተፈጸመ የተባለው ወንጀል የተፈጸመው ኦሮሚያ ክልል በመሆኑ ጉዳያቸው በኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት መታየት ይገባዋል በሚል የሥረ ነገር የዳኝነት ስልጣንን (Judicial jurisdiction) በተመለከተ ያቀረቡትን መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ የጸረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 31 የሽብር ክሶችን የማየት ስልጣን የፌደራሉ ፍ/ቤት መሆኑን እንደሚደነግግ በመጥቀስ መቃወሚያቸው ውድቅ መደረጉን በብይኑ ላይ አመልከቷል፡፡

የቀረበባቸው ክስ የክስ አቀራረብ ደረጃን ያላሟላና ግልጽነት የሌለው መሆኑን በሚመለከት ላቀረቡት አቤቱታ ፍ/ቤቱ ክሱ በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን ገልጾ የተከሳሾች የወንጀል ተሳትፎ ደረጃን በተመለከተ ግን በማስረጃ መስማት ወቅት የምናየው ይሆናል በማለት ፍርድ ቤቱ መቃወሚያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡

መንግስት በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከመልካም አስተዳደር ችግር የመነጨ መሆኑን አምኖ ይቅርታ የጠየቀበት ጉዳይ ስለሆነ በዚህ ምክንያት እኛን በወንጀል የሚያስጠይቀን የህግ አግባብ የለም በሚል በተከሳሾች የቀረበውን መቃወሚያም ‹‹…ንብረት ማውደምና የሰው ህይወት ማጥፋት…››ን ጠቅሶ አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ በህግ መታየት እንዳለበት ፍ/ቤቱ መገንዘቡን ጠቅሶ መቃወሚያውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ፍ/ቤቱ ሌሎች የተከሳሾች መቃወሚያዎችንም እንዳልተቀበላቸው በብይኑ ላይ ገልጹዋል፡፡

ተከሳሾች ብይኑን ተከትሎ ያሰሙት ተቃውሞ

ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ብይን በንባብ ከተሰማ በኋላ ሀሳባቸውን ለመግለጽ እጃቸውን በማውጣት ችሎቱን ጠይቀዋል፡፡ ችሎቱ በበኩሉ ‹‹ጊዜ የለንም፣ አሁን ልንሰማችሁ አንችልም›› በማለት የተከሳሾችን አቤቱታ ሊያልፈው ሞክሯል፡፡ ሆኖም አቶ በቀለ ገርባ ከተቀመጡበት በመነሳት ‹‹ዜጎች ነን፣ በትልቅ ወንጀል ተከሰናል፡፡ አድበስብሶ ማለፍ አይቻልም፡፡ ፍርድ ቤቱ በግልጽ ሀሳባችንን እንድንናገር ካልፈቀደ ማን ሊፈቅድልን ነው? ስለሆነም እንናገር ስሙን፡፡ የማትሰሙን ከሆነ ግን ውሳኔያችሁን እዚያው እስር ቤት ልትልኩልን ሲገባ እዚህ መቅረባችን ትርጉም የለውም›› በማለት ማሳሰባቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ አቶ በቀለ እንዲናገሩ ለመፍቀድ ተገድዷል፡፡

በዚህም አቶ በቀለ ገርባ ፍ/ቤቱ በሰጠው ብይን ላይ በተለይ የዳኝነት ስልጣንን በተመለከተ ጥያቄ አዘል ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
‹‹ህገ መንግስቱ የፌደራል ፍ/ቤት በክልልም ማቋቋም አለበት ይላል፡፡ አሁን የተሰጠው ውሳኔ ግን ይህን ያልተገነዘበ ነው፡፡ ይሄ ህገ መንግስት በሦስት ዳኞች ውሳኔ ሊፈርስ አይችልም፡፡ ህገ መንግስቱ የእኔም ነው፤ የመጠበቅ ኃላፊነት አለብኝ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉም እንዲጠብቀው አደራ እላለሁ፡፡

በህገ መንግስቱ መሰረት በክልል በቋቋም የነበረባቸው የፌደራል ፍ/ቤቶች አልተቋቋሙም፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ የክልል ፍ/ቤቶች በውክልና ሊዳኙ በተገባ ነበር፤ ይህ አልሆነም፡፡ እናም ይህ የክልሎችን ስልጣን መሻር ነው፡፡ የዛሬውን ውሳኔያችሁን ኤርትራን ከፌደረሽኑ ለመገንጠል ከተደረገው ውሳኔ ታሪክ ጋር ነው የማገናኘው፡፡ ይህ ህገ መንግስት በብዙዎች ደም ነው የተጻፈው›› በማለት በእጃቸው የያዙትን ህገ መንግስት ወደ ዳኞች እያሳዩ ተናግረዋል፡፡

አቶ ደጀኔ ጣፋ በበኩላቸው ‹‹ውሳኔው ክልሎች ያገኙትን ስልጣን የነጠቀ ነው፡፡ እኛ የምንታገለው ህግን ለማስከበር ነው፡፡ ለዚህም የኦሮሞ ህዝብ ከጎናችን እንዲሆን ጥሪ አስተላልፋለሁ›› ብለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰብሳቢ ዳኛው አቶ ታደለ ተገኝ ‹‹እኛ አቤቱታ ነው የምንሰማው፡፡ መልዕክት ማስተላለፍ አይቻልም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ይህን የዳኛውን ንግግር ተከትሎም አቶ በቀለ ገርባ ‹‹የሰጣችሁት ውሳኔኮ ፖለቲካዊ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ሌሎችም ተከሳሾች አቤቱታና ጥያቄዎች እንዳሉዋቸው ቢገልጹም ፍ/ቤቱ ጊዜ የለንም በሚል ለማስተናገድ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ በሌላ በኩል ግን ችሎቱ መሰየም ከነበረበት ሰዓት እጅግ ዘግይቶ ከቀኑ 9፡30 ነው የተሰየመው፡፡ በዚህም ዳኛው ጊዜ የለንም ሲሉ ተከሳሾች ዳኞች ራሳቸው ዘግይተው መሰየማቸውን አስታውሰዋቸዋል፡፡

ፍ/ቤቱ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለነሐሴ 5/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቅቋል፡፡ የችሎቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ተከሳሾች በህብረት የተቃውሞ መዝሙር በኦሮምኛ አሰምተዋል፡፡ ‹‹ህዝባችን እየሞተ፣ እየተበደለ እንዴት ዝም እንላለን…እንታገላለን እንጂ ዝም አንልም…›› የሚል ይዘት ያለው የተቃውሞ መዝሙሩን ከችሎት ወጥተው መኪና ውስጥ እስኪገቡ ድረስ ሲዘምሩት ተደምጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት

Thursday, 4 August 2016

በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት በፌደራል ደረጃ በሽብር የተከሰሱ የ136 ሰዎች ዝርዝር

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ከህዳር ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞና የመብት ጥያቄ ምክንያት በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰደው እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች ተገድለዋል፤ በሺዎች ታስረዋል፤ ተሰደዋል፣ ሲያልፍም የገቡበት ያልታወቁ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህ እውነታ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተሰሩ ሪፖርቶች ገሃድ የወጣ ድርጅታችን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጅክትም ሲዘግበው የነበረ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክትም በህዝባዊው ተቃውሞ የተነሳ መንግስት ግድያ የፈጸመባቸውን ዜጎች ዝርዝር በጥናት ላይ ተመስርቶ ይፋ አድርጓል፡፡ በተቃውሞው ሂደት መንግስት በወሰደው የኃይል እርምጃ ህይወታቸውን ካጡት ዜጎች በተጨማሪ በርካቶች አደባባይ ወጥተው የመብት ጥያቄያቸውን በማሰማታቸው ወደእስር ቤት ተግዘዋል፡፡ እስረኞቹ በክልልና በፌደራል እስር ቤቶች ታጉረው ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት በፌደራል መንግስቱ በሚተዳደሩ እስር ቤቶች የሚገኙትንና ክሳቸው ሽብር የሆኑትን ሰዎች ዝርዝር ከዚህ ቀጥሎ ይፋ አድርጓል፡፡ ዝርዝሩ ከሽብር ውጭ ባለ ወንጀል የተከሰሱትንና ለእስር ተዳርገው ክስ ያልተመሰረተባቸውን እስረኞች አይጨምርም፡፡ በዝርዝሩ ላይ የተካተቱት ተከሳሾች ከህዳር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ከተነሳው የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ ወዲህ ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ሳይመሰረትባቸው በፌደራል ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) በእስር ላይ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ አብረዋቸው ታስረው ቆይተው ክስ ከተመሰረተባቸውና ቀጥሎ ስማቸው ከተዘረዘሩት ሰዎች ለመገንዘብ ቢቻልም፣ ሙሉ ስማቸውና ቁጥራቸው በውል ባለመታወቁ ለጊዜው እዚህ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም፡፡ በዘጠኝ መዝገቦች የተከፈተው የሽብር ክስ ተከሳሾች ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡
በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ (እነ በቀለ ገርባ)

1. በቀለ ገርባ
2. ደጄኔ ጣፋ
3. አዲሱ ቡላላ
4. ጉርሜሳ አያኖ
5. አብደታ ነጋሳ
6. ገላና ነገረ
7. ጭምሳ አብዲሳ
8. ጌቱ ግርማ
9. ፍራኦል ቶላ
10. ጌታቸው ደረጄ
11. በየነ ሩዶ
12. ተስፋዬ ሊበን
13. አሸብር ደሳለኝ
14. ደረጄ መርጋ
15. የሱፍ አለማየሁ
16. ሂካ ተክሉ
17. ገመቹ ሸንቆ
18. መገርሳ አስፋው
19. ለሚ ኤዴቶ
20. አብዲ ታምራት
21. አብደላ ከመሳ
22. ሀራኮኖ ቆንጮራ፣ ናቸው፡፡

በእነ ደስታ ዲንቃ መዝገብ

23. ደስታ ዲንቃ
24. ለማ ባይ ጉተማ
25. ዋዩ ቤካ
26. አብደታ ባትሪ
ያለ አባሪ ክስ የቀረበበት
27. ዮናታን ተስፋዬ

በእነ ሐብታሙ ሚልኬሳ የክስ መዝገብ

28. ሐብታሙ ሚልኬሳ ጫሊ
29. ረዳት ሳጅን ጫላ ፍቃድ አብደታ
30. ጌትነት ለሚ ኃይሎሴ
31. በከልቻ ቁፋ ቤኛ
32. ለሜሳ አብቹ ዱሬሳ
33. መኮነን ገቢሳ ገደፉ
34. ፀጋዬ ጋዲሳ ኡባ
35. አቦንሳ አኩማ ሆንዳራ
36. ረዳት ሳጅን ቤኩማ ታደሰ ፊንዳ
37. ዲንሳ ፋፋ ድርባ
38. አልኩ አቦና መኩሪያ
39. እሸቱ ደባ ነገዎ
40. ታደሰ ነገኦ ገመዳ
41. ኡምኔሳ በዳሳ ሚዴቅሳ
42. ሮቢሌ አብዲሳ ክቲላ
43. በቀለ ተሬሳ ረጋሳ
44. ነገሰ በርሲሳ ደበሌ
45. ካሳሁን ሙሊሳ ሙለታ
46. አብዲ ታሪኩ ዴረሳ
47. ደጀኔ ፋይሳ ጠፋ
48. ታሪኩ ቦኪ ደበላ
49. አብዲሳ ቦካ ቱጅባ
50. እምሩ ነገዎ ጀማ
51. መልካሙ ታደለ ቢዬ
52. ረዳት ሳጅን ተስፋዬ አባተ ደምሴ
53. ተካልኝ ቡለቾ ገመዳ
54. ረ/ሳጅን ኩምሲሳ ዱጉማ ሚልኬሳ
55. ክንፈ መኮነን ተሰማ
56. ኪንስታብል ገመቹ ታሪኩ እጅጉ
57. ቶሎሳ በዳዳ ደበሬ
58. ሺፈራው ግርማ ሰንበታ
59. ቢኒያም ጫላ ገረሱ
60. ስንታየሁ መኮንን ገዳ

በእነ ኦላና ከበደ መዝገብ

61. ኦላና ከበደ
62. ወልዴ ሞቱማ
63. መገርሳ ፍቃዱ
64. አርገምሲሳ ሌንጂሳ
65. ም/ሳጅን መሰረት አቦማ
66. አብዲሳ ኢፋ
67. ዋርደር ተመስገን
68. ተካልኝ መርዶሳ
69. ቦኪ እሸቱ
70. ብርሃኑ ቦኪ
71. ማሙሽ ቦኪ
72. ፍቃዱ አዱኛ
73. መኮንን ዘውዴ
74. ወርቁ ጉርሙ
75. ገረሙ አዱኛ
76. ደረጄ ታዬ
77. ጃለታ ሰንዳፋ
78. ላቀው ሮቢ
79. እንግዳ ቁሲ
80. ቶሽሌ ተስፋ
81. ታደለ ዓለሙ
በእነ አበበ ኡርጌሳ መዝገብ
82. አበበ ኡርጌሳ
83. መገርሳ ወርቁ
84. አዱኛ ኬሶ
85. ቢሉሱማ ዳመና
86. ሌንጂሳ አለማየሁ (መከላከል ሳያስፈልገው በፍርድ ቤት ነጻ ተብሎ የተፈታ)
87. ተሻለ በቀለ (ከሽብር ክስ ወደ ወንጀል ህጉ ተቀይሮለት ተከላከል የተባለና በዋስ የተፈታ)

በእነ ተሾመ ረጋሳ መዝገብ

88. ተሾመ ረጋሳ
89. ጫላ ዲያስ
90. ኦብሱማን ኡማ
91. ኒሞና ለሜሳ
92. ከበደ ጨመዳ
93. ምረቱ ጉሉማ
94. ዴቢሳ በየነ
95. ጌታሁን ደስታ
96. መንግስቱ ጉዲሳ
97. ተሰማ ሁንዴ
98. ቦንሳ (ኦብሳ) ኃይሉ
99. አሸብር ኦንቾ
100. ጃራ ኤቢሳ
101. ፋፋ ሬፋንራፋ
102. አጥናፉ ቢራሳ
103. አብዲ ታደሰ

በእነ ሀብታሙ ሀጫሉ መዝገብ

104. ሀብታሙ ሀጫሉ
106. ቶኩማ ሙሌሳ
107. ደጋጋ ብርሃኑ
108. ዮሐንስ ኡርጌሳ
109. ዴብሳ በሊና
110. አብዱርህማን አደም
111. ዮሴፍ ዲዳ
112. ተስፋዬ በቀለ
113. ዴቢሳ ኤታንሳ
114. ናኦል ሻሚሮ
115. ለታ አህመድ

በእነ ቀጀላ ገላና የክስ መዝገብ

116. ቀጀላ ገላና
117. ሰብኬበ በቀለ
118. አብደታ ወላንሳ (ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በደረሰበት ድብደባ (ቶርች) ምክንያት ታሞ ቂሊንጦ እስር ቤት የሞተ)
119. ኡርጌሳ ደመና

በእነ አሚን ዬዮ ሙመድ መዝገብ

120. አሚን ዬዮ ሙመድ
121. አብዱ የሱፍ አቡዱ ኡመር
122. አብድልዋሴ ኢብራሂም አብደላ
123. አብድልቃድር መሃመድ ኢብራሂም
124. ሸምሰዲን አህመድ ኡመድ
125.መሃመድ አልዩ ኡመር አህመድ
126. መሃመድ ሶፍያን ሀመዴ
127. አበዲ መሃመድ አደም
128. ጀማል ቶፊቅ አሜቶ
129. ፋሮምሳ ሃሚሶ ጊዞ
130. ሃሩን አዪቦ መሀመድ
131. ናስር አሚን ኢብራሂም ኡመር
132. ጀማል አልዩ መሃመድ ብተቤ
133. አህመድ ከሊፍ አሚን
134. ከልፍ መሃመድ አደም
135. ብሩ ገለቱ ጋሪ
136. ያሲን መሃመድ አደም

(በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት የተዘጋጀ)

                                                                        በቀለ ገርባ

ኢትዮጵያውያን በእስራኤል የኪዳነምህረት ቤ/ክ የኢሕአዴግን ባንዲራ አውርደው የኢትዮያውያንን ባንዲራ ሰቀሉ

ባለፈው ሳምንት በጎንደር የተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ ሕዝቡ ምንም አይነት ምልክት የሌለበትን ባንዲራ ይዞ አደባባይ ከወጣ በኋላ በ እስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚገኘው የኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ላይ የተሰቀለውና መሀሉ ላይ ምልክት ያለበት የኢህአዴግን ባንዲራ አውርደው ምክንም አይነት ምልክት የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ሰቀሉ:: ቪዲዮውን ይመልከቱ