
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ንግግር ለማድረግ ተጋብዘው ሲመለሱ የግንቦት ሰባት አመራር እና ሊቀመንበር
ከሆኑት ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ታይተዋል በሚል ለእስር የተዳረጉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከሶስት ወር የማእከላዊ
ምርመር ቆይታ በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ የክስ ፋይሉ በዶ/ር መረራ ስም የተከፈተ ሲሆን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
ሁለተኛ ተከሳሽ ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ሶስተኛ ተከሳሽ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ ሶስቱም ተከሳሾች የተከሰሱት በወንጀለኛ
መቅጫ ህጉን የተለያዩ አንቀጾች በመተላለፍ ሲሆን አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሽ የሆኑት የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቪዥን
( ኢሳት) እና ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ( ኢኤም ኤን) ተቋማቱ
በሽብር ህጉን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር መረራ የአስቸኳይ ጊዜ...