የሶስት ልጆች አባት የሆኑት የሰሜን ለንደን ነዋሪው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሁለት ዓመታት በፊት ከየመን አየር
መንገድ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው መሰጠታቸው አይዘነጋም ፡፡የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት
ኃላፊዎችም አንዳርጋቸውን ከወራት የምስጢር ወህኒ ቤት ቆይታቸው በኋላ በቴሌቭዥን አቅርበዋቸው ነበር፡፡
ዜጋዋ ሰብዓዊ መብቶቹ ባልተከበሩበት ሁኔታ የታሰረባት እንግሊዝ በአንጻሩ በደህንነት ማኔጅመንት ዙሪያ ክራንፊልድ ዩኒቨርስቲ ለሚሰጠው የማስተርስ ትምህርት የኢትዮጵያ የደህንነት ሰዎች ስኮላርሺፕ እንዲያገኙ የ500.00 ፓውንድ ድጋፍ ማድረጓ ታውቋል፡፡546.500 ፓውንድ ደግሞ የኢትዮጵያን የሰላም አስከባሪ መከላከያ ሰራዊት የስልጠና ማዕከል ለመደገፍ በሚል ሰበብ መስጠቷን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የአንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የሚ ኃይለማርያም ሁኔታውን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት ‹‹በጣም ተበሳጭቼያለሁ ፡፡በእንዲህ አይነት መንገድ ድጋፍ ማድረጋችንም አስገራሚ ነው፡፡እነርሱ እርዳታው የሰብዓዊ መብት አከባበርን ለማሻሻል ነው ይላሉ፣ነገር ግን እንደገና ሄደው አንዳርጋቸውን ላሰረው መንግስት ድጋፋቸውን ያደርጋሉ››ብለዋል፡፡
የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ አቻው ስላደረገው ድጋፍ መረጃ የተገኘው ፍሪደም ኦፍ ኢንፎርሜሽን የተባለ ተቋም ለውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ ባቀረበው መጠይቅ ነው፡፡ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የጂቡቲና የሩዋንዳ የደህንነት ሰራተኞች ኮርሱን እየወሰዱ ነው ተብሏል፡፡
በዩኒቨርስቲው የሚሰጠውን የደህንነት ትምህርት እንዲከታተሉ የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ በማድረጉ 35 የኢትዮጵያ የደህንነት ሰራተኞች ኮርሱን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ትችሏል፡፡
የሞት ቅጣትን ለማስቀረት በመስራት ላይ የሚገኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሪፕራይቭ ኢንተርናሽናል ኃላፊ ማያ ፎ ‹‹እንግሊዛዊ ዜግነት ያለውን አንዳርጋቸውን ላሰረች አገር የእንግሊዝ መንግስት ለደህንነት ሰራተኞቻቸው ድጋፍ ማድረጉን እንግሊዛዊያን ግብር ከፋዮች በቸልታ ሊመለከቱት አይገባም››ይላሉ፡፡
ከአስር ግብር ከፋዮች ስድስቱ እንግሊዝ የምታደርገው የውጪ እርዳታ በዋናነት መቀነስ እንደሚገባው የሚያምኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡አንዳርጋቸው የተያዙ ሰሞንም የእንግሊዝ አለም አቀፍ የልማት ሃላፊ የሆኑት ጀስቲን ግሪንግ ለኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ሊሰጥ የነበረን እርዳታ ማገዳቸው መነገሩ አይዘነጋም፡፡
ባሳለፍነው ወር የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ ኢትዮጵያ አንዳርጋቸውን የያዘችበትን መንገድ በመተቸት ጉዳዩን በጥልቀት ለመመርመር መዘጋጀቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ዴይሊ ሜይል እንደተመለከታቸው የገለጻቸው የኢሜይል ልውውጦች በአቶ አንዳጋቸው ጉዳይ በእንግሊዝና በኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች መካከል መደረጋቸውን ቢያሳዩም እርዳታው አለመቋረጡ ታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ የምዕራባዊያን ቀኝ እጅ ተደርጋ መወሰዷም የእንግሊዝን ቀጥተኛ የበጀት ድጎማ ለማግኘት አስችሏታል፡፡አገሪቱ በያዝነው ዓመት 277 ሚልዩን ፓውንድ በማግኘትም ሁለተኛዋ ከፍተኛ የእንግሊዝ እርደታ ተቀባይ አሰኝቷታል፡፡
ምንጭ ዴይሊ ሜይል

0 comments:
Post a Comment