Tuesday 29 April 2014

የታሰሩት የሰማያዊ አመራሮችና አባላት በደል እየደረሰባቸው ነው

(EMF) ባለፈው ሳምንት ሰማያዊ ፓርቲ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅሥቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ አመራሮችና አባላት በእስር ቤት ውስጥ መሆናቸው ይታወቃል። እነዚህ በቅስቀሳው ወቅት ፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ ያሰራቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እስር ቤት ውስጥ በደል እየደረሰባቸው መሆኑንም ተናግረዋል። ዮናታን ተስፋዬ ይህን በተመለከተ እንዲህ ብሏል።
የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች
የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች

በየካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት አባላትና አመራሮች ትናንት ምግብ እንዳይገባላቸው በመከልከሉ ጾማቸውን አድረዋል፡፡ በተመሳሳይ በቤተሰብና በአባላት እንዳይጠየቁም እየተከለከሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከሌሎች እስረኞች በተለየ በር በጊዜ እንደሚዘጋባቸው፣ እንዳይጠየቁ እንደተከለከሉና ሌሎችም በደሎች እየደረሱባቸውመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ እየተበደሉ መሆኑን ለፖሊሶች በሚናገሩበት ወቅትም ‹‹እኛ ምን እናድርጋችሁ! ታዘን ነው! እናንተን ያሰራችሁ ሌላ አካል ነው፡፡ እኛ አይደለንም!›› የሚል መልስ እደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡


0 comments:

Post a Comment