Wednesday, 8 November 2017

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከተከሰሱበት ክስ በነፃ ተሰናበቱ !!

በባለፈው አመት አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፋችኋል ተብለው በተመሰረተባቸው ክስ 9 ወር ያህል ታስረው እንደነበር የሚታወስ ነው። በተመሰረተባቸው ክስ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 3 ወንጀል ችሎት እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና (በይግባኝ) አሲዘው ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ብይን የተሰጠ ሲሆን፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ከአገር እንዳይወጡ ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ተጨማሪ ትእዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።

ከእስር ከተፈቱ ከሦስት ወር በኋላ በዛሬው እለት ጥቅምት 29 ቀን 2010 . በተከሰሱበት ክስ ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም ፣ፍርድ ቤቱ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ የተከሰሱበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተሻረ በመሆኑ በወንጀለኛ ሕግ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ከተከሰሱበት ክስ በነፃ የተሰናበቱ ሲሆን በሕጉ ላይ እንደተገለጸው " የተሻረ ሕግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖር እና በዚህ ህግ እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ ይቅረጣል" በማለት በሕግ ተደንግጎ ይገኛል። በዚህም መሰረት አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ በነፃ የተሰናበቱ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለዋስትና ያስያዙት ገንዘብ እንዲመለስ እና ከሃገር እንዳይወጡ የተጣለው ገደብ እንዲነሳ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል




Saturday, 4 November 2017

“በጉሽ ጠላ እየተገፋ ስልጣን ለቅቄያለሁ ማለት አይሰራም” ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ተመስርቶ ሳይውል ሳያድር ስልጣን መረከብ አለበት

በጉሽ ጠላ እየተገፋ ስልጣን ለቅቄያለሁ ማለት አይሰራም
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ


ተመስገን ዛሬ ቀዳሜ ጥቅምት 25/10 ከወጣው ሸገር ታይምስ መፅሄት ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ ላይ የተወሰደ።

ተመስገን ደሳለኝየመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በስቸኳይ ይቆቆምብሎ ከተናገረው መካካል

ሀላፊነት የሚሰማቸው እና የሕዝብ አመኔታ ያላቸው የሀገር ሽማግሌዎች፣ ልሂቃን፣ ምሁራን፣ አክቲቪስቶችንያሰባሰበ ‹‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ›› ተመስርቶ ሳይውል ሳያድር ሥልጣኑን መረከብ አለበት፡፡ ይሄ ሃሳብ 1983 ወያኔ ወደ አዲስ አበባ ሲንደረደር አዛውንቱ ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን /ማርያም አቅርበውት ከነበረው ‹‹የሽማግሌ መንግሥት›› ጋር ይመሳሰላል፡፡ ፕሮፍ ለነፃነት ታግለናል ብላችሁ እንደተንደረደራችሁ ስልጣን መያዝ አግባብ አይደለም፡፡ የሽማግሌ መንግስት ይቋቋም ሁሉም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ፓርቲ ተወዳድሮ ተአማኝና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ስልጣን ለሚይዝ አካል ይስጥ ብለው ነበር፡፡ መለስ ዜናዊና ጠመንጃ ነካሽ ጓደኞቹ ግን የታገሉት ለግል ስልጣን ስለነበር መንግስታዊ ኃላፊነቱን ይዘው ባለፉት 26 አመታት የአገሪቱን ኢኮኖሚ አደቀቁ፤ ህዝባችንን በሀይማኖትና በብሔር ከፋፍለው እነሆ እንዳንተማመን አደረጉ፡፡

ተመስገን ስለአብዮቱከተናገረው መካካል

እኔና ጓዶቼ የታመንለት አብዮት እንደ ብሉይ አብዮት ጠብመንጃ ያነገበ አይደለም፡፡ በቀዘቃዛው ጦርነት ዘመን እንደነበረው አይደለም፡፡ የእኛ መንገድ በፊሊፒንስ ከተካሄደው 1986 (..) የቀለም አብዮት ጋር የሚጋመድ ነው፡፡ የቀለም አብዮት ላይ ጠመንጃ የለም፤ መንግስት እንደሚለውም ጭራቅ አይደለም፡፡ በታሪክ ፀሀፊዎች የመጀመሪያው የቀለም አብዮት የተባለው የቢጫ አብዮት የሚል ስም የተሰጠው ፊሊፕንስ ውስጥ የተካሄደው ነው፡፡ ፈርዲናንድ ማርቆስ የተሰኘው አምባገነን መሪ በስልጣን ተሸንፎም ስልጣን አለቅም አለ፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን አሰረ፡፡ ያኔ ወጣቶቹ መዲናዋን ማኒላን አጥለቀለቋት፡፡ መሪው ታንክ ቢያዘምትባቸውም ቢጫ አበባ ይዘው ለታንከኞቹና ለወታደሮቹ አጠለቁላቸው፡፡ ባለታንከኞቹ ከወጣቱ ጋር ተቀላቀለው ስርዓቱን ቀየሩ፡፡ ታሪክ ፀሀፊዎች የወጣቶቹን ቢጫ አበባ አይተው ‹‹ቢጫ አብዮት›› ብለው ጠሩት፤ የብርቱካን፣ የቡልዶዘር፣ የቬልቬት….. አብዮት እየተባለ ቀጠለ፡፡ ሆንግኮንግ ላይ ወደ አደባባይ የወጡ ሰዎች ዝናብ በመዝነቡ ጃንጥላ ይዘው ወጡ፤ ክስተቱን የተከታተሉ ፀሀፊዎችም ‹‹የጃንጥላ አብዮት›› ሲሉ ሰየሙት፡፡ እኛ ሀገር ደግሞ ‹‹የስካርፕ አብዮት›› ሊባል ይችል ይሆናል፤ ማን ያውቃል?

ታሪኩ ደሳለኝ

Thursday, 2 November 2017

Congressman urges House to vote on Ethiopian resolution

Representative Mike Coffman of Colorado today urge the House of Representative to vote on H. Res. 128, a resolution supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia.

“I am disappointed that the house has not yet scheduled a floor vote on House Resolution 128. I note that on two prior occasions, a vote was tentatively scheduled. In both of these instances it’s my understanding the vote was postponed due to pressure from the Ethiopian government who curbs human rights abuses against their own people but fail to deliver,” the Congressman said speaking on the House floor this morning.

He said the ongoing human rights crisis in Ethiopia is extremely troubling him, to the resolutions and other co-sponsors, to the many Americans of Ethiopian heritage and to numerous human rights groups. He encouraged the House leadership to schedule a vote and members to vote in favor of the Resolution.

Representative Coffman said he believes the United States could take actions to influence changes in Ethiopia. “The resolution does not simply highlight the Ethiopia’s government increasing authoritarian acts but also encourages the united states to support efforts to improve democracy and governance in Ethiopia. I believe that the united states can take actions that will positively influence the ethiopian government and use our existing institutions to further democracy and effective governance in Ethiopia,” Coffman said.

Coffman said the Ethiopian regime, instead of making the required changes, has resorted to hiring a D.C lobby firm and engaged in public affairs works. He said he was aware that the Ethiopian regime has threatened to stop security cooperation with the U.S. should the House proceed with the Resolution.

“I am dismayed rather than solving their problems and moving towards becoming a more democratic government, the Ethiopian government has chosen to hire a D.C. lobbying firm…..The issue the Ethiopian government needs to address is the repression of democracy and its citizens in Ethiopia. The solution to whatever negative perception it has in the halls of the U.S. congress is not a public affairs one but rather what concrete steps are taken — are being taken against democracy in Ethiopia.”

The Representative from District 8 of Colorado who works closely with the Ethiopian community on promoting democracy and human rights in Ethiopia also expressed his disappointment that the House has not yet scheduled a vote on the Resolution.


Tuesday, 31 October 2017

ንግስት ይርጋ በማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣት ገለፀች

(በጌታቸው ሺፈራው)

በአማራ ክልል በነበረው ህዝባዊ እምብይተኝነት ሰበብ "ሽብር ክስ" የተመሰረተባቸው እነ ንግስት ይርጋ ዓቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ማስረጃ መሰረት ይከላከሉ ወይም በነፃ ይሰናበቱ የሚለውን ለመበየን ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበር ቢሆንም ብይኑ አልተሰራም ተብሎ ብይኑን ለመስራት 3 ጊዜ ለህዳር 1/2010 ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል።

1 ተከሳሽ ንግስት ይርጋ በስም ካስመዘገበቻቸው የቤተሰብ አባላት ውጭ እንዳትጠየቅ፣ እንዲሁም ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ባለው አንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ እንድትጠየው ገደብ የተጣለባት መሆኑን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4 ወንጀል ችሎት አቤቱታ አቅርባ እንደነበር ይታወሳል።

ሀምሌ 21/2009 ዓም በዋለው ችሎት ፍርድ ቤት በቤተሰብ፣ የሀይማኖት አባት፣ የትዳር ጓደኛ እና በጠበቃዋ የመጠየቅ ህገ መንግስታዊ መብት እንዳላት፣ የሰዓት ገደብም እና ልዩ ክልከላ ሊደረግባት እንደማይገባ ወስኖ ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ሳያከብር ቀርቷል።

ፍርድ ቤቱ ነሃሴ12/2009 የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለምን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እንዳላከበረ ኃላፊዎቹ በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ ለዛሬ ጥቅምት 21/2010 ዓም ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ዛሬም አልቀረቡም።

1 ተከሳሽ ንግስት ይርጋ ፍርድ ቤቱ የላከው ትዕዛዝ ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት መድረሱን ገልፃ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች እየጠሩ ለምን ማረሚያ ቤቱን ትከሻለሽ? ከማን በልጠሽ ነው? እያሉ በተደጋጋሚ እንዳስጠነቀቋት ለፍርድ ቤቱ ገልፃለች። ሆኖም ፍርድ ቤቱ "የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ፈፅመዋል አልፈፀሙም የሚለውን ካጣራን በኋላ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል አልሰጡም የሚለውን የምናጣራ ይሆናል" ብሎ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል ብላ ያቀረበችውን አቤቱታ አልተቀበለውም።

6 ተከሳሽ ያሬድ ግርማ ማዕከላዊ እስር ቤት የምርምር ስራዎቹን ወስዶ እንዳልመለሰለት፣ በዚህ ጉዳይ ያቀረበው አቤቱታም መልስ እንዳላገኘ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል። ፍርድ ቤቱ በሌላ መዝገብ ምስክር ሊያሰማ መሆኑን በመግለፅ የሌሎች ተከሳሾችን አቤቱታ ሳይቀበል ቀርቷል። 5 ተከሳሽ በላይነህ አለምነህ " ለዚህ ቀን የተቀጠርነው የራሳችን ሰዓት ተመድቦልን ነው። በሌላ መዝገብ ምስክርነት አለ ልንባል አይገባም" ሲል ፍርድ ቤቱ አካሄዱን እንዲያስተካክል ቢያሳስብም ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አልተቀበለውም። "ቢያንስ ችሎቱ ያለንን ሀሳብ እንድናስረዳ ዕድል ይፍጠርልን" ቢልም ፍርድ ቤቱ በድጋሜ አቤቱታውን ሳይቀበለው በሌላ መዝገብ ወደያዘው ምስክርነት ገብቷል።

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ንግስት ይርጋን "ንግስቲ" እያለ በመጥራቱ የንግስት ይርጋ ጠበቃ 1 ተከሳሽ ስም "ንግስት" ተብሎ እንዲስተካከል ጠይቀዋል። በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ የተከሰሱት ንግስት ይርጋ፣ አለምነህ ዋሴ፣ቴዎድሮስ ተላይ፣አወቀ አባተ፣ በላይነህ አለምነህ እና ያሬድ ግርማ ናቸው።

                                                                                ንግስት ይርጋ

“I am worried Ethiopia will explode:” MEP Ana Gomes

(ESAT) A member of the European Parliament who is a fervent critic of the TPLF said current political developments in Ethiopia could lead to conflict with tremendous consequences to the Horn of Africa.

Speaking to ESAT on the phone, the Portuguese politician said she fears that the ongoing conflicts in various parts of the country will go out of hand with serious ramifications to the region and even to Europe.

Ana Gomes, who was an observer for the rigged 2005 election in Ethiopia, said the 2015 election in the country was a farce and no one came to observe it. As a result, the MP said the Ethiopian regime has no legitimacy. She wonders why the U.S. and EU still continue support the regime.
“It is really shocking to me that powers such as the U.S. and the EU and its member states know very well that TPLF has no legitimacy and democratic bases in Ethiopia and still continue to support under the pretext that it is an ally against terrorism,” Gomes said.

She said recent resignation by officials of the government and members of the army show that there is “tremendous fragmentation” and “lack of coherence with in the TPLF.”

“It shows that the situation is fast unravelling.”

“Those in U.S. and Europe used excuses to turn a blind and have neglected the democratic aspiration of the people of Ethiopia. The fact that they have supported and turn a blind eye to the totalitarian regime of the TPLF is going to provoke an uncontrolled explosion in Ethiopia. I am very very worried for Ethiopia as well as the Horn of Africa and Europe too because it has an implication for Europe,” Gomes added.

Speaking about Bereket Simon, who recently announced his resignation, and an official whom she dealt with during the 2005 election, the Member of Parliament described him as “cynical, cruel and despicable.”

“After Meles, he was the most despicable character i had to deal with.
He has a murky character. He could be operating from behind. I had always been extremely suspicious about him.”.

She also talked about Dr. Tedros Adhanom, the Ethiopian Director General of the WHO who was recently under fire for nominating Zimbabwe’s Robert Mugabe. She said Dr. Tedros is “a member the TPLF and responsible for crimes committed by the criminal organization.”

She advised that change in Ethiopia will occur if Ethiopians come together and take matters in their own hands.

“They should not expect someone else come and make changes in the country.”


Bekele Gerba released on bail

The supreme court of Ethiopia released on bail Bekele Gerba, one of the key opposition leaders incarcerated for over a year and half on charges of terrorism, which were later reduced to criminal charges.

Bekele was among 20 others who were imprisoned in April 2015 at the height of protests in the Oromo region accused of inciting the unrest, uprising and civil war, charges Gerba vehemently denies.

The Ethiopian regime has a long record of charging opponents citing the much criticized terrorism proclamation to stifle dissent. It is not clear if the regime was trying to quell the growing opposition across the nation against its rule, especially in the Oromo region of the country, by releasing Gerba.

Bekele Gerba, who was the deputy chairman of the Oromo Federalist Congress, served almost five years between 2011 and 2015 when he was accused of being a member of the Oromo Liberation Front that was outlawed by the regime. He was arrested again on terrorism charges in April 2015 at the climax of protests in the Oromo region.

Bekele Gerba

Thursday, 26 October 2017

Two political prisoners beaten to death by prison officers

Co-defendants told a court in Addis Ababa that two inmates were beaten to death by prison officers at a maximum security prison outside the capital.

A defendant told the court that Alemaye Wake Mamo and Mohammed Chane were beaten to death by the superintendent of the notorious Qilinto prison, named Asefa Kidane.

Journalist Getachew Shiferaw wrote on his blog that Bisrat Amare, the defendant who exposed the killings to the court pleaded to the judges to transfer him to another prison saying he feared for his life.

Amare reminded the court that one of the deceased, Wake Mamo had previously demanded to the same court to be transferred to another prison as he feared for his life. Amare said now that he had exposed the crime, he feared he would face the same fate. But the court ignored his plea and sent him to Qilinto.

Several political prisoners were killed by prison officers in Ethiopia’s notorious prisons.
Alemayehu Gerba, a university student, died in a hospital after he was shot by prison officers.
Gadisa Hirpa, a political prisoner, was beaten to death at the Kaliti prison for smuggling in a cell phone.

Colonel Demisew Anteneh and Colonel Alemu Getnet were shot by prison guards two years ago but later survived.

Prison guards indiscriminately shot and killed over 20 inmates at Qilinto as they tried to escape from a fire that broke out at the prison in September 2016. The political prisoners that appeared today before the court were accused of starting the fire.

                                                                      Qilinto prison