Thursday, 7 May 2015

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበት ሁኔታ ለህይወታቸው አስጊ ነው ተባለ

andargachew new picture
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በከፍተኛ ህመም በመሰቃየት ላይ ሲሆኑ እስካሁን በዶክተሮች ለመጎብኘት አልቻሉም።
አያያያዛቸው የከፋ መሆኑን በማስመልከት የእንግሊዝ መንግስት አስቸኳይ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መጻፉንም ምንጮቻችን ገልጸዋል።


አቶ አንዳርጋቸው ያለፉትን ተከታታይ ወራት ጸሃይ የሚባል ነገር ሳያዩ ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው አሳልፈዋል; ከህመማቸው ጋር በተያያዘም ምግብ መመገብ በእጅጉ ቀንሰዋል።

በከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው፣ አያያዛቸው አስከፊ እንደሆነ በቅርቡ ለጎበኙዋቸው የእንግሊዝ አምባሳደር መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ይህንን ተከትሎም የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠንከር ያለ ደብዳቤ መጻፉን የአዲስ አበባ ምንጮች ገልጸዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ በአፋጣኝ የማይለወጥ ከሆነ፣ በህይወታቸው ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል ያስጠነቀቁት የእንግሊዝ ባለስልጣናት፣ አቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር ድጋፍ እንዲያገኙ፣ በመደበኛ እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩና በጠያቂዎች እንዲጎበኙ ፣ ሃኪሞች እንዲያዩዋቸውና ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ደብዳቤ መጻፋቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ገዢው ፓርቲ ከአቶ አንዳርጋቸው የረባ መረጃ ለማግኘት ባለመቻሉ_የስነ ልቦና ጫና በማሳረፍና ህክምና በመከልከል ለመጉዳት ማሳቡን ምንጮች ገልጸዋል።

የእንግሊዝ ባለስልጣናት በሂደት ስለሚወስዱት እርምጃ ግልጽ ባያደርጉም፣ ጉዳዩን በቀላሉ እንደማያዩት ለኢህአዴግ ሹሞች እንደገለጹላቸው ታውቋል።

አቶ አንዳርጋቸው በየመን የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፈው ከተሰጡ በሁዋላ፣ ገዢው ፓርቲ ሁለት ጊዜ በቴሌቪዥን አቅርቧቸዋል። ተቆራርጦ የተላለፈውን ቪዲዮ ተከትሎ ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ትችት ሲቀርብብት ቆይቷል።
ኢህአዴግ አቶ አንዳርጋቸውን ህዝብ ሊጎበኛቸው በሚችል እስር ቤት አለማሰሩና ሰብአዊ መብታቸውን ሁሉ መግፈፉ የገዢውን ፓርቲ የፍርሃትና የበቀል ደረጃ፣ እንዲሁም ራሱ ላወጣው ህግ እንኳን የማይገዛ መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ገዥው ፓርቲ ኦሮሚያ ውስጥ ምርጫውን ጀምሮታል ተባለ

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ከአሁኑ እንደጀመረው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎች መራጮችን በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ እያደራጁ ‹‹ኦህዴድ/ኢህአዴግን መርጫለሁ›› በሚል እያስፈረሙና ፎርም እያስሞሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ ተደራጅተው ‹‹ኦህዴድን መርጠናል›› ብለው እንዲፈርሙ የተደረጉ ዜጎች ፎርሙን ከሞሉበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ መሪዎቻቸው እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ መሪዎችም ኢህአዴግን ከአሁኑ መርጠዋል ተብለው የተደራጁ ዜጎችን ስምና የምርጫ ካርድም ለኦህዴድ/ኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች እንደሚሰጡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ካድሬዎች ግንቦት 16 ቀን በፊት የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ለሴልና ለኔትወርክ መሪዎች የሚሰጡትን ዜጎች ቤት ለቤት እየዞሩ እያስፈረሙ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ ተደራጅተው ኦህዴድ/ኢህአዴግን ከአሁኑ እንደመረጡ በፊርማቸው አረጋግጠዋል የተባሉት ዜጎች ግንቦት 16/2007 ዓ.ም በሚደረገው ምርጫ እንደማይሳተፉ የታወቀ ሲሆን አብዛኛዎቹ በግዳጅና በማስፈራሪያ እየሞሉ እንደሚገኙ ተገልጾአል፡፡

የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ እንዲሁም የመራጮች ስምና ፊርማቸው እየሰፈረበት ከግንቦት 16 በፊት እንደመረጡ ተደርጎ ዜጎች እንዲሞሉት የሚደረገውና ከስር የሚታየው ቅጽ ካድሬዎች በአርሲ ዞን በቆጅ ወረዳ ቤት ለቤት ሲያስሞሉ የተገኘ ነው፡፡


ፍ/ቤቱ በ‹‹በሁከትና ብጥብጥ›› ለተጠረጠሩ 17 ሰዎች ዋስትና ሲፈቅድ፣ በሰማያዊ አባላት ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል


ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስታችኋል፤ ተካፍላችኋልም›› በሚል ፖሊስ ካሰራቸው ሰዎች መካከል ፍርድ ቤት 17ቱን በ3000 ብር የሰው ዋስ እንዲለቀቁ ሲወስን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ደግሞ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዛሬ ሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ሌሎች በዕለቱ የተያዙ ሰዎችን በተመለከተ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በሦስት መዝገቦች ስር እንደየተሳትፏቸው አደራጅቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ከአሁን በፊት በሦስተኛው መዝገብ ላይ የተካተቱትን ሙሉ ለሙሉ መልቀቁን መግለጹ ይታወቃል፡፡ በሁለተኛው መዝገብ ላይ የተካተቱት 17 ሰዎች ደግሞ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲወጡ ተወስኗል፡፡


አንደኛው መዝገብ ላይ በእነ ወይንሸት ሞላ መዝገብ 5 ሰዎች የተካተቱ ሲሆን አራቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ጸጋየ እና ማስተዋል ፈቃዱ ናቸው፡፡ በዚሁ መዝገብ ላይ ፖሊስ የፓርቲው አባል እንደሆነች የሚገልጸው፣ እሷ ግን አባል አለመሆኗን የገለጸች ቤተልሄም አቃለወርቅ ተካትታለች፡፡ በዚሁ በአንደኛው መዝገብ ላይ የተካተቱት 5ቱም ተጠርጣሪዎች ዛሬ በዋለው ችሎት ተጨማሪ 3 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡


5ቱም ተጠርጣሪዎች ፖሊስ እስካሁን የተሰጠው የምርመራ ጊዜ በቂ መሆኑንና ቋሚ አድራሻ ያላቸው መሆኑን በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤቱን የጠየቁ ሲሆን፣ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎች ምስክሮችን ያሸሹብናል፣ ያስፈራሩብናል በሚል ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡ ፖሊስ ዋስትና ሲቃወም ‹‹ተጨማሪ አባላትን መያዝ ይቀረናል›› ሲል የገለጸ ሲሆን፣ ‹አባላት› ሲል ምን ለማለት እንደፈለገ ለፍርድ ቤቱ ግልጽ አላደረገም፡፡


በሌላ በኩል አሁን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች እንደገለጹት ጠዋት ፍርድ ቤት የ3000 ብር የሰው ዋስ የፈቀደላቸው 17 ሰዎች በፖሊስ ይግባኝ እንደተጠየቀባቸውና  ወደ ፍርድ ቤት መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

Wednesday, 6 May 2015

The mass exodus of Ethiopians and their suffering is attributable to bad governance and wrong policies of the Ethiopian regime

Afar People’s Party, Press release
Afar People’s Party's logo
We are very much saddened and shocked by inhuman and barbaric act of terror on innocent Ethiopians committed by ISIS in Libya. First of all, we would like to express our deeply felt condolences to all the families affected by this barbaric terrorist action. The evil act of ISIS represents neither the faith of Islam that the Afar People practice and the Allah we worship nor the human values that we share with entire human race. Slaying innocent Ethiopians who left their beloved ones and country to seek a better future can’t be justified by any religious motivation or political ideology. It is simply a cruel and barbaric act of terror that every human being should denounce and prevent from happening again.

Our Ethiopian compatriots are facing the traps of xenophobia in South Africa, exposed to war crimes in Yemen, inhuman treatment and deportation in Saud Arabia and elsewhere in the Middle East; and now a raw slaughter in Libya.

The root causes for amassed exodus and our national degradation are emanating from an increasing social- and economic inequality and violation of human rights and dignity. It is merely the outcome of cumulative dysfunctional policies of the current EPRDF/TPLF regime that outplayed the legal framework of its own constitution. About 64% of Ethiopia’s population is under the ages of 24 year.

The increasing youth unemployment rate, the shrinking democratic space in the country, and losing the hope on future are the main driving factors for youth to leave their country for unknown future. In contrast, the regime is bragging over the double digit economic growth; while suffocating non-economic requirements for economic growth and human development such as independent public institutions, the rights of civil society organization, human rights and freedom of expression and others aspects of accountabilities related to biased policy implementations.

The current biased policy which is based on ruling in the interest few elites with rampant corruption and promoting political and economic exclusion of the majority cannot be considered as sustainable development. Those who praise what is going on in Ethiopia as democratic improvement should revisit their sources as well as should be held accountable for prolonging the agony of the Ethiopian people.

The coming 2015 election is nothing more than a showcase for international political consumption. However, in reality is about to consolidate more economic- and political power; narrowing the political space and crashing the political opposition groups. Thus a chance for national reconciliation, inclusive political dialog and public participation on future direction of our country seems to be utterly unlikely.
  • The APP, condemns not only the terrorists outside our country but also state run terrorism carried out in Ethiopia which contributes to the suffering of our people inside and outside by the negligence and bigotry of the ruling party.
  • We believe that our destiny and our better future is in our hands and we need to unify our struggle more than ever to fight injustice until our social values and our national dignity is restored.
  • We call on all international community to take the case of Ethiopia seriously, before an intensified civil war and collapse. The conflict and collapse of Ethiopia undoubtedly will cause a huge turmoil internally and beyond its borders.
Afar People’s Party

አስተዳደሩ ሰማያዊ ፓርቲ መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ማድረግ እንደማይችል ገለጸ

• ‹‹ተቀባይነት የሌለው ተልካሻ ምክንያት ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ህዝባዊ ስብሰባ እውቅና እንደማይሰጠው ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ አስተዳደሩ በላከው ደብዳቤ ‹‹መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ከመሆኑም በላይ በርካታ የተከማዋ ነዋሪ የሚተላለፍበት እና የከተማው ነዋሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር›› ነው ሲል ለህዝባዊ ስብሰባው እውቅና እንደማይሰጥና ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባውን መስቀል አደባባይ ማድረግ እንደማይችል ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ አስተዳደሩ የሰጠው መልስ ‹‹ተቀባይነት የሌለው ተልካሻ ምክንያት ነው›› ሲል  ገልጾአል፡፡ ኃላፊው አክሎም ‹‹አደባባዩ የተሰራው እንደዚህ አይነት ተግባራት ሊከናወኑበት ነው፡፡ ኢህአዴግ ሲጠራ ትራፊክ ተጨናነቀ ተብሎ አያውቅም፡፡ ሰማያዊ ሰልፍና ስብሰባ ሲጠራ ግን እንዲህ አይነት ተልካሻ ምክንያት ያቀርባሉ፡፡ በመሆኑም ይህን ተልካሻ ምክንያት ሰማያዊ ፓርቲ አይቀበለውም›› ብሏል፡፡

ከትራፊክ መጨናነቅ ባሻገር አስተዳደሩ ሰማያዊ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ የፀጥታ ኃይል ለመመደብ እንደሚቸገርም የገለጸ ሲሆን አቶ ዮናታን ተስፋዬ በበኩሉ ‹‹ለጥበቃ የለንም ያሉትን የፀጥታ ኃይል ንፁሃንን ለመደብደብ ሲያሰማሩ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ አሁንም የጥበቃ ኃይል የለንም የሚሉት ስብሰባውን ለማስተጓጎል ነው፡፡ ያኔ ግን ሰላማዊ ዜጎችን ለመደብደብ ይልኩታል፡፡ በመሆኑም የአስተዳደሩ ውሳኔ በምክንያት ያልተደገፈና ተቀባይነት የሌለው ነው›› ብሏል፡፡

Saturday, 2 May 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ቤት ተበረበረ

• የሰማያዊ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ለ‹ምርመራ› ተወስዷል

ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ሳይጀመርና ከሰልፉ በኋላ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ቤት ተበረበረ፡፡

ካሳንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ትናንት ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ቀርበው የ6 ቀን ቀጠሮ ከተሰጠባቸው በኋላ ምሽት ላይ ቤታቸው መበርበሩንና ንብረቶቻቸው መወሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

በብርበራው ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በሰላማዊ ሰልፍና በሌሎች አጋጣሚዎች የሚለብሱት የሰማያዊ ፓርቲ አርማ ያለበት ቲሸርት፣ የምርጫና ሌሎች ቅስቀሳ ወረቀቶችም ለ‹ምርመራ› ተወስደዋል፡፡ 


ቤታቸው ለሰዓታት የተበረበረባቸው ወይንሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ጸጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ማስተዋል ፍቃዱ ሲሆኑ ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ወረቀቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ አርማ ያለበት ቲሸርት፣ ሲዲዎች፣ አርማ የሌለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ (በተናጠል አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የሆነ)፣መጽሐፎች እና ሌሎችም ህጋዊ ሰነዶች እንደተወሰዱባት ገልጻለች፡፡ ዳንኤል ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አርማ ያለበት ቲሸርት፣ በአንድ ላይ ያስጠረዛቸው የፋክትና የአዲስ ጉዳይ እትሞች፣ ሲዲዎችና ካሴቶች ተወስደውበታል፡፡ በተመሳሳይ ኤርሚያስ ጸጋዬ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሰነዶች፣ ሲዲዎች፣ ማስታወሻ ደብተሮችና ሌሎችም ህጋዊ ሰነዶች ተወስደውብኛል ብሏል፡፡


Friday, 1 May 2015

Detail of Rights Violation on Zone9 Bloggers and Journalists

It is now solid one year since the arrest of Zone9 blogger and journalists. there had been 27 court hearings, 86 days of interrogation at the notorious “Meakelawi” interrogation center before they moved to their current detention place in “Kality” and “Kilinto”. during their stay they faced many rights violation. This rights violation had also been reported for the united nations working group for arbitrary detention.

On the commemoration of their arrest the summary of the rights violation was made public for readers and followers of the case for the last one year. attached is the summary of the rights violation of all 9 detainees.

Rights Violation in Meakelawi PDF

all 9 detainees.